የተጨነቀ ሰው ጸሎት
መዝሙረ መዓርግ
1 በሰማይ ዙፋን ላይ የተቀመጥህ ሆይ፤
ዐይኖቼን ወደ አንተ አነሣለሁ።
2 የባሪያዎች ዐይን ወደ ጌታቸው እጅ፣
የባሪያዪቱም ዐይን ወደ እመቤቷ እጅ እንደሚመለከት፣
ምሕረት እስከሚያደርግልን ድረስ፣
የእኛም ዐይኖች ወደ አምላካችን ወደእግዚአብሔርይመለከታሉ።
3 እግዚአብሔርሆይ፤ ንቀት በዝቶብናልና፣
ማረን፣ እባክህ ማረን።
4 ነፍሳችን የቅንጡዎች ስድብ፣
የትዕቢተኞችም ንቀት እጅግ በዝቶባታል።