የእስራኤል ጠባቂ
መዝሙረ መዓርግ
1 ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ፤
ረድኤቴ ከወዴት ይመጣል?
2 ረድኤቴ ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ፣
ከእግዚአብሔርዘንድ ይመጣል።
3 እግርህ እንዲሸራተት አይፈቅድም፤
የሚጠብቅህም አይተኛም።
4 እነሆ፤ እስራኤልን የሚጠብቅ፣ አይተኛም፤ አያንቀላፋምም።
5 እግዚአብሔርይጠብቅሃል፤
እግዚአብሔርበቀኝህ በኩል ይከልልሃል።
6 ፀሓይ በቀን አያቃጥልህም፤
ጨረቃም በሌሊት ጒዳት አታመጣብህም።
7 እግዚአብሔርከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፤
ነፍስህንም ይንከባከባታል።
8 እግዚአብሔርከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣
መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቃል።