መዝሙር 118

ለዳስ በዓል የቀረበ የጒዞ መዝሙር

1 እግዚአብሔርቸር ነውና አመስግኑት፤

ምሕረቱም ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።

2 የእስራኤል ሕዝብ፣ “ምሕረቱ ለዘላለም ነው” ይበል።

3 የአሮን ቤት፣ “ምሕረቱ ለዘላለም ነው” ይበል።

4 እግዚአብሔርንየሚፈሩ ሁሉ፣

“ምሕረቱ ለዘላለም ነው” ይበሉ።

5 በተጨነቅሁ ጊዜእግዚአብሔርንጠራሁት፤

እግዚአብሔርምመለሰልኝ፤ ከመጠበብም አወጣኝ።

6 እግዚአብሔርከእኔ ጋር ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?

7 ይረዳኝ ዘንድእግዚአብሔርከእኔ ጋር ነው፤

የጠላቶቼንም ውድቀት አያለሁ።

8 ሰውን መከታ ከማድረግ ይልቅ፣

በእግዚአብሔርመታመን ይሻላል።

9 በገዦች ተስፋ ከማድረግ ይልቅ፣

በእግዚአብሔርመታመን ይሻላል።

10 ሕዝቦች ሁሉ ከበቡኝ፤

ነገር ግንበእግዚአብሔርስም አስወግዳቸዋለሁ።

11 መክበቡንስ በየአቅጣጫው ከበቡኝ፤

ነገር ግንበእግዚአብሔርስም አስወግዳቸዋለሁ።

12 እንደ ንብ መንጋ ከበቡኝ፤

ነገር ግን እንደሚነድ እሾኽ ከሰሙ፤

በእርግጥምበእግዚአብሔርስም አስወግዳቸዋለሁ።

13 ተገፍትሬ ልወድቅ ተንገደገድሁ፤

እግዚአብሔርግን ረዳኝ።

14 እግዚአብሔርብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤

አዳኝ ሆነልኝ።

15 በጻድቃን ድንኳን የእልልታና የሆታ ድምፅ፣

እንዲህ እያለ ያስተጋባል፤

“የእግዚአብሔርቀኝ እጅ ብርቱ ሥራ ሠራች፤

16 የእግዚአብሔርቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አለች፤

የእግዚአብሔርቀኝ እጅ ብርቱ ሥራ ሠራች።

17 ተርፌ በሕይወት እኖራለሁ እንጂ አልሞትም፤

የእግዚአብሔርንምሥራ ገና እናገራለሁ።

18 መገሠጹንእግዚአብሔርእጅግ ገሥጾኛል፤

ነገር ግን ለሞት አሳልፎ አልሰጠኝም።

19 የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፤

በዚያ ገብቼእግዚአብሔርንአመሰግናለሁ።

20 ይህችየእግዚአብሔርደጅ ናት፤

ጻድቃን በእርሷ በኩል ይገባሉ።

21 ሰምተህ መልሰህልኛልና፣

አዳኝም ሆነህልኛልና አመሰግንሃለሁ።

22 ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣

እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ።

23 እግዚአብሔርይህን አደረገ፤

ለዐይናችንም ድንቅ ናት።

24 እግዚአብሔርየሠራት ቀን ይህች ናት፤

በእርሷ ሐሤት እናድርግ፤ ደስም ይበለን።

25 እግዚአብሔርሆይ፤ እባክህ አድነን፤

እግዚአብሔርሆይ፤ እባክህ አሳካልን።

26 በእግዚአብሔርስም የሚመጣ ቡሩክ ነው።

ከእግዚአብሔርቤት ባረክናችሁ።

27 እግዚአብሔርአምላክ ነው፤

ብርሃኑንም በላያችን አበራ፤

እስከ መሠዊያውቀንዶች ድረስ በመውጣት፣

ዝንጣፊ ይዛችሁ በዓሉን ከሚያከብሩት ጋር ተቀላቀሉ።

28 አንተ አምላኬ ነህ፤ አመሰግንሃለሁ፤

አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።

29 ቸር ነውና፣እግዚአብሔርንአመስግኑ፤

ምሕረቱም ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *