ምስጋና
1 የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና፣
እግዚአብሔርንወደድሁት።
2 ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሎአልና፣
በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጣራለሁ።
3 የሞት ወጥመድ ያዘኝ፤
የሲኦልምጣር አገኘኝ፤
ጭንቅና ሐዘን አሸነፈኝ።
4 እኔምየእግዚአብሔርንስም ጠራሁ፤
“እግዚአብሔርሆይ፤ ነፍሴን ታድናት ዘንድ እለምንሃለሁ” አልሁ።
5 እግዚአብሔርቸርና ጻድቅ ነው፤
አምላካችን መሓሪ ነው።
6 እግዚአብሔርገሮችን ይጠብቃል፤
እጅግ ተቸግሬ ሳለሁ አዳነኝ።
7 ነፍሴ ሆይ፤ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፤
እግዚአብሔርመልካም አድርጎልሻልና፤
8 አንተ ነፍሴን ከሞት፣
ዐይኔን ከእንባ፣
እግሮቼን ከመሰናከል አድነሃልና።
9 እኔም በሕያዋን ምድር፣
በእግዚአብሔርፊት እመላለሳለሁ።
10 “እጅግ ተጨንቄአለሁ” ባልሁበት ጊዜ እንኳ፣
እምነቴን ጠብቄአለሁ።
11 ግራ በተጋባሁ ጊዜ፣
“ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው” አልሁ።
12 ስለ ዋለልኝ ውለታ ሁሉ፣
ለእግዚአብሔርምን ልክፈለው?
13 የመዳንን ጽዋ አነሣለሁ፤
የእግዚአብሔርንምስም እጠራለሁ።
14 በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣
ስእለቴንለእግዚአብሔርእፈጽማለሁ።
15 የቅዱሳኑ ሞት፣
በእግዚአብሔርፊት የተከበረ ነው።
16 እግዚአብሔርሆይ፤ እኔ በእውነት ባሪያህ ነኝ፤
እኔ የሴት ባሪያህልጅ፣ ባሪያህ ነኝ፣
ከእስራቴም ፈታኸኝ።
17 ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፤
የእግዚአብሔርንምስም እጠራለሁ።
18 በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣
ስእለቴንለእግዚአብሔርእፈጽማለሁ፤
19 ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ይህን በመካከልሽ፣
በእግዚአብሔርቤት አደባባይ አደርጋለሁ።
ሃሌ ሉያ።