ለፋሲካ የቀረበ ውዳሴ
1 እስራኤል ከግብፅ ወጥቶ ሲሄድ፣
የያዕቆብም ቤት ቋንቋው ልዩ ከሆነ ሕዝብ ተለይቶ ሲወጣ፣
2 ይሁዳየእግዚአብሔርመቅደስ፣
እስራኤልም ግዛቱ ሆነ።
3 ባሕር አየች፤ ሸሸችም፤
ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ።
4 ተራሮች እንደ አውራ በግ፣
ኰረብቶችም እንደ ጠቦት ዘለሉ።
5 አንቺ ባሕር፤ የሸሸሽው አንቺም ዮርዳኖስ ያፈገፈግሽው ለምንድን ነው?
6 እናንተ ተራሮች እንደ አውራ በግ፣
ኰረብቶችም እንደ ጠቦት ለምን ዘለላችሁ?
7 ምድር ሆይ፤ በጌታ ፊት፣
በያዕቆብ አምላክ ፊት ተንቀጥቀጪ፤
8 እርሱ ዐለቱን ወደ ኩሬ፤
ቋጥኙንም ወደ ውሃ ምንጭ ለወጠ።