ለታላቁና ለመሓሪው ጌታ ምስጋና
1 ሃሌ ሉያ።
የእግዚአብሔርአገልጋዮች ሆይ፤ አመስግኑት፤
የእግዚአብሔርንስም አወድሱ።
2 ከአሁን እስከ ዘላለም፣
የእግዚአብሔርስም የተመሰገነ ይሁን።
3 ከፀሓይ መውጫ እስከ መግቢያው ድረስ፣
የእግዚአብሔርስም የተመሰገነ ይሁን።
4 እግዚአብሔርከሕዝቦች ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው፤
ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው።
5 እንደ አምላካችን እንደእግዚአብሔር፣
በላይ በዙፋኑ የተቀመጠ ማን ነው?
6 በሰማይና በምድር ያሉትንስ ለማየት፣
ራሱን ወደ ታች ዝቅ የሚያደርግ ማን ነው?
7 ድኻውን ከትቢያ ያነሣል፤
ችግረኛውን ከዐመድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤
8 ከመኳንንትም እኩል ስፍራ ይሰጠዋል፤
ከሕዝቡም ሹማምት ጋር ያስቀምጠዋል።
9 መካኒቱን ሴት በቤት ያኖራታል፤
ደስተኛም የልጆች እናት ያደርጋታል።
ሃሌ ሉያ።