ጻድቅና ቅዱስ አምላክ
1 እግዚአብሔርነገሠ፤
ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ፤
በኪሩቤል ላይ በዙፋን ተቀምጦአል፤
ምድር ትናወጥ።
2 እግዚአብሔርበጽዮን ታላቅ ነው፤
ከሕዝቦችም ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ብሎአል።
3 ታላቁንና አስፈሪውን ስምህን ይወድሱ፤
እርሱ ቅዱስ ነው።
4 ፍትሕን የምትወድ፣ ኀያል ንጉሥ ሆይ፤
አንተ ትክክለኝነትን መሠረትህ፤
ፍትሕንና ቅንነትንም፣
ለያዕቆብ አደረግህ።
5 አምላካችንንእግዚአብሔርንከፍ ከፍ አድርጉት፤
በእግሩ መርገጫ ስገዱ፤
እርሱ ቅዱስ ነውና።
6 ሙሴና አሮን ካህናቱ ከሆኑት መካከል ነበሩ፤
ሳሙኤልም ስሙን ከጠሩት መካከል አንዱ ነበረ፤
እነርሱ ወደእግዚአብሔርተጣሩ፤
እርሱም መለሰላቸው።
7 ከደመና ዐምድ ውስጥ ተናገራቸው፤
እነርሱም ሥርዐቱንና የሰጣቸውን ድንጋጌ ጠበቁ።
8 እግዚአብሔርአምላካችን ሆይ፤
አንተ መለስህላቸው፤
ጥፋታቸውንብትበቀልም እንኳ፣
አንተ ይቅር የምትላቸው አምላክ ነህ።
9 አምላካችንንእግዚአብሔርንከፍ ከፍ አድርጉት፤
በቅዱስ ተራራውም ላይ ስገዱ፤
አምላካችንእግዚአብሔርቅዱስ ነውና።