መዝሙር 82

ሙሱናን ዳኞች

የአሳፍ መዝሙር

1 እግዚአብሔር በአማልክት ጉባኤ መካከል ተሰየመ፤

በአማልክትም ላይ ይፈርዳል፤ እንዲህም ይላል፦

2 “ፍትሕን የምታጓድሉት እስከ መቼ ነው?

ለክፉዎች የምታደሉትስ እስከ መቼ ነው?ሴላ

3 ለዐቅመ ቢሶችና ለድኻ አደጎች ፍረዱላቸው፤

የችግረኛውንና የምስኪኑን መብት አስከብሩ።

4 ወገን የሌለውንና ችግረኛውን ታደጉ፤

ከግፈኛውም እጅ አስጥሏቸው።

5 “ዕውቀትም ማስተዋልም የላቸውም፤

በጨለማ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ይመላለሳሉ፤

የምድርም መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ።

6 “እኔም፤ ‘እናንተ አማልክት ናችሁ፤

ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ’ አልሁ።

7 ነገር ግን እንደ ማንኛውም ሰው ትሞታላችሁ፤

እንደ ማንኛውም ገዥ ትወድቃላችሁ።”

8 አምላክ ሆይ፤ ተነሥ፤ በምድር ላይ ፍረድ፤

ሕዝቦች ሁሉ ርስትህ ናቸውና።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *