እግዚአብሔር፣ የእስራኤል ንጉሥ የዓለም ጌታ
ለመዘምራን አለቃ፤ የቆሬ ልጆች መዝሙር።
1 ሕዝቦች ሁላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤
ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር እልል በሉ።
2 በምድር ሁሉ ላይ ታላቅ የሆነው ንጉሥ፣
ልዑልእግዚአብሔርየሚያስፈራ ነውና።
3 ሕዝቦችን ከእኛ በታች አደረገ፤
መንግሥታትንም ከእግራችን ሥር አስገዛልን።
4 ለሚወደው ለያዕቆብ ክብር የሆነችውን፣
ርስታችንን እርሱ መረጠልን።ሴላ
5 አምላክ በእልልታ፣
እግዚአብሔርበመለከት ድምፅ ዐረገ።
6 አምላካችንን አወድሱት፤ አወድሱት፤
ንጉሣችንን አወድሱት፤ አወድሱት፤
7 እግዚአብሔርየምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤
ምርጥ ዝማሬአቅርቡለት።
8 እግዚአብሔር በሕዝቦች ላይ ነግሦአል፤
እግዚአብሔር በተቀደሰ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦአል።
9 ከአብርሃም አምላክ ሕዝብ ጋር፣
የሕዝቦች መኳንንት ተሰበሰቡ፤
የምድር ነገሥታትየእግዚአብሔር ናቸውና፤
እርሱም እጅግ ከፍ ከፍ ያለ ነው።