መዝሙር 34

የእግዚአብሔር ፍትሕ ውዳሴ

እንደ እብድ ሆኖ አቤሜሌክ ፊት በመቅረቡ ተባሮ በወጣ ጊዜ የዘመረው፤ የዳዊት መዝሙር

1 እግዚአብሔርንሁል ጊዜ እባርከዋለሁ፤

ምስጋናውም ዘወትር ከአፌ አይለይም።

2 ነፍሴበእግዚአብሔርተመካች፤

ትሑታንም ይህን ሰምተው ሐሤት ያደርጋሉ።

3 ኑና ከእኔ ጋርእግዚአብሔርንአክብሩት፤

ስሙንም በአንድነት ከፍ ከፍ እናድርግ።

4 እግዚአብሔርንፈለግሁት፤ እርሱም መለሰልኝ፤

ከፍርሀቴም ሁሉ አዳነኝ።

5 ወደ እርሱ የሚመለከቱ ያበራሉ፤

ፊታቸውም ከቶ አያፍርም።

6 ይህ ችግረኛ ጮኸ፤እግዚአብሔርምሰማው፤

ከመከራውም ሁሉ አዳነው።

7 እግዚአብሔርንበሚፈሩት ዙሪያየእግዚአብሔርመልአክ ይሰፍራል፤

ያድናቸዋልም።

8 እግዚአብሔርቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እዩ፤

እርሱን መጠጊያ የሚያደርግ ምንኛ ቡሩክ ነው!

9 እናንተ ቅዱሳኑ፤እግዚአብሔርንፍሩት፤

እርሱን የሚፈሩት አንዳች አያጡምና።

10 አንበሶች ሊያጡ፣ ሊራቡም ይችላሉ፤

እግዚአብሔርንየሚሹ ግን መልካም ነገር አይጐድልባቸውም።

11 ልጆቼ ሆይ፣ ኑ፤ ስሙኝ፤

እግዚአብሔርንመፍራት አስተምራችኋለሁ።

12 ሕይወትን የሚወድ፣

በጎውንም ያይ ዘንድ ዕድሜን የሚመኝ ማን ነው?

13 አንደበትህን ከክፉ ነገር ከልክል፤

ከንፈርህንም ከሽንገላ ጠብቅ።

14 ከክፉ ሽሽ፤ መልካሙንም አድርግ፤

ሰላምን ፈልጋት፤ ተከተላትም።

15 የእግዚአብሔርዐይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው፤

ጆሮዎቹም ለጩኸታቸው ክፍት ናቸው።

16 መታሰቢያቸውን ከምድር ለማጥፋት፣

የእግዚአብሔርፊት በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።

17 ጻድቃን ሲጮኹ፣እግዚአብሔርይሰማቸዋል፤

ከመከራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል።

18 እግዚአብሔርልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፤

መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል።

19 የጻድቅ መከራው ብዙ ነው፤

እግዚአብሔርግን ከሁሉም ያድነዋል።

20 ዐጥንቶቹን ሁሉ ይጠብቃል፤

ከእነርሱም አንድ አይሰበርም።

21 ኀጢአተኞችን ክፋት ይገድላቸዋል፤

ጻድቃንን የሚጠሉ ይፈረድባቸዋል።

22 እግዚአብሔርየባሪያዎቹን ነፍስ ይቤዣል፤

እርሱንም መጠጊያ ያደረገ አይፈረድበትም።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *