አምላክ የለሽ ሰዎች
ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር።
1 ሞኝበልቡ፣
“እግዚአብሔር የለም” ይላል።
ብልሹዎች ናቸው፤ ተግባራቸውም ጸያፍ ነው፤
በጎ ነገር የሚሠራ አንድም የለም።
2 የሚያስተውል፣ እግዚአብሔርን የሚፈልግ መኖሩን ለማየት፣
እግዚአብሔርከሰማይ ወደ ሰው ልጆች ተመለከተ።
3 ሁሉም ከመንገድ ወጥተዋል፤
በአንድ ላይም ብልሹ ሆነዋል፤
አንድ እንኳ፣
መልካም የሚያደርግ የለም።
4 የእግዚአብሔርንስም የማይጠሩት፣
ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉት፣
ክፉ አድራጊዎች ሁሉ ዕውቀት የላቸውምን?
5 ባሉበት ድንጋጤ ውጦአቸዋል፤
እግዚአብሔር በጻድቃን መካከል ይገኛልና።
6 እናንተ የድኾችን ዕቅድ ለማፋለስ ትሻላችሁ፤
እግዚአብሔርግን መጠጊያቸው ነው።
7 ምነው እስራኤልን የሚያድን ከጽዮን በወጣ!
እግዚአብሔርየሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፣
ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤልም ሐሤት ያድርግ።