መዝሙር 9

በክፉ ላይ ፍርድ

ለመዘምራን አለቃ፤ በሙትላቤን ቅኝት፤ የዳዊት መዝሙር

1 እግዚአብሔርሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤

ስለ ድንቅ ሥራዎችህም ሁሉ እናገራለሁ።

2 በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም አደርጋለሁ፤

ልዑል ሆይ፤ ስምህን በመዝሙር እወድሳለሁ።

3 ጠላቶቼ ወደ ኋላ በተመለሱ ጊዜ፣

ተሰነካክለው ከፊትህ ይጠፋሉ፤

4 ፍርዴም ጒዳዬም በአንተ እጅ ናቸውና፤

ቅን ፍርድ እየሰጠህ በዙፋንህ ላይ ተቀምጠሃል።

5 ሕዝቦችን ገሠጽህ፤ ክፉዎችንም አጠፋህ፤

ስማቸውንም እስከ ወዲያኛው ደመሰስህ።

6 ጠላቶች ለዘላለም ጠፉ፤

ከተሞቻቸውንም ገለባበጥሃቸው፤

መታሰቢያቸውም ተደምስሶአል።

7 እግዚአብሔርግን ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ነው፤

መንበሩንም ለፍርድ አጽንቶአል።

8 ዓለምን በጽድቅ ይዳኛል፤

ሕዝቦችንም በፍትሕ ይገዛል።

9 እግዚአብሔርለተጨቈኑት ዐምባ ነው፤

በመከራም ጊዜ መጠጊያ ይሆናቸዋል።

10 ስምህን የሚያውቁ ይታመኑብሃል፤

እግዚአብሔርሆይ፤ የሚሹህን አትተዋቸውምና።

11 በጽዮን ለሚኖርለእግዚአብሔርዘምሩ፤

ሥራውንም በሕዝቦች መካከል በግልጽ አውሩ፤

12 ደም ተበቃዩ ዐስቦአቸዋልና፤

የጭቍኖችንም ጩኸት አልዘነጋም።

13 እግዚአብሔርሆይ፤ ጠላቶቼ የሚያደርሱብኝን መከራ ተመልከት፤

አይተህም ራራልኝ፤ ከሞት ደጅም አንሥተህ መልሰኝ፤

14 ይህን ስታደርግልኝ፣ በጽዮን ሴት ልጅ ደጅ፣

ምስጋናህን ዐውጃለሁ፤

በማዳንህም ሐሤት አደርጋለሁ።

15 አሕዛብ በቈፈሩት ጒድጓድ ገቡ፤

እግራቸውም ራሳቸው በስውር ባስቀመጡት ወጥመድ ተያዘ።

16 እግዚአብሔርበትክክለኛ ፍርዱ የታወቀ ነው፤

ክፉዎችም በእጃቸው ሥራ ተጠመዱ። ሒጋዮንሴላ

17 ክፉዎች ተመልሰው ወደ ሲኦልይወርዳሉ፤

እግዚአብሔርን የሚዘነጉ ሕዝቦችም ሁሉ እንደዚሁ።

18 ችግረኞች ግን መቼም ቢሆን አይረሱም፤

የድኾችም ተስፋ ለዘላለም መና ሆኖ አይቀርም።

19 እግዚአብሔርሆይ ተነሥ፤ ሰውም አያይል፤

አሕዛብም በፊትህ ይፈረድባቸው።

20 እግዚአብሔርሆይ፤ ድንጋጤ አምጣባቸው፤

ሕዝቦች ሰው ከመሆን እንደማያልፉ ይወቁ።ሴላ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *