የሠርክ ጸሎት
ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች የሚዜም የዳዊት መዝሙር
1 የጽድቄ አምላክ ሆይ፤
በጠራሁህ ጊዜ መልስልኝ፤
ከጭንቀቴ አሳርፈኝ፤
ማረኝ፤ ጸሎቴንም ስማ።
2 ሰዎች ሆይ፤ እስከ መቼ ድረስ ክብሬን ዝቅታደርጋላችሁ?
እስከ መቼስ ድረስ ከንቱ ነገርን ትወዳላችሁ? ሐሰትንስትሻላችሁ?ሴላ
3 እግዚአብሔርጻድቁን ለራሱ እንደ ለየ ዕወቁ፤
እግዚአብሔርወደ እርሱ በተጣራሁ ጊዜ ይሰማኛል።
4 ስትቈጡ ኀጢአት አትሥሩ፤
በዐልጋችሁም ላይ ሳላችሁ፣
ልባችሁን መርምሩ፤ ጸጥም በሉ።ሴላ
5 የጽድቅን መሥዋዕት አቅርቡ፤
በእግዚአብሔርምታመኑ።
6 ብዙዎች፣ “አንዳች በጎ ነገር ማን ያሳየናል? ይላሉ፤
እግዚአብሔርሆይ፤ የፊትህ ብርሃን በላያችን ይብራ።
7 ስንዴና አዲስ የወይን ጠጅ በብዛት ባመረቱ ጊዜ ከሚያገኙት ደስታ ይልቅ፣
አንተ ልቤን በታላቅ ሐሤት ሞልተኸዋል።
8 በሰላም እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁም፤
እግዚአብሔርሆይ፤ ያለ ሥጋት የምታሳድረኝ አንተ ብቻ ነህና።