የመከራ ተቀባዩ የጧት ጸሎት
ዳዊት ከልጁ ከአቤሰሎም በሸሸ ጊዜ የዘመረው መዝሙር
1 እግዚአብሔርሆይ፤ ጠላቶቼ ምንኛ በዙ
ስንቱስ በእኔ ላይ ተነሣ!
2 ብዙዎች ነፍሴን፣ “እግዚአብሔር
አይታደግሽም” አሏት።ሴላ
3 እግዚአብሔርሆይ፤ አንተ ግን ዙሪያዬን
የምትከልል ጋሻ ነህ፤
ክብሬና፣ ራሴንም ቀና ቀና
የምታደርግ አንተ ነህ።
4 ወደእግዚአብሔርድምፄን ከፍ አድርጌ እጮሃለሁ፤
እርሱም ከተቀደሰ ተራራው ይመልስልኛል።ሴላ
5 እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁ፤
እግዚአብሔርደግፎ ይዞኛልና እነቃለሁ።
6 በየአቅጣጫው የከበበኝን፣
አእላፍ ሕዝብ አልፈራም።
7 እግዚአብሔርሆይ ተነሥ!
አምላኬ ሆይ፤ ታደገኝ፤
የጠላቶቼን ሁሉ መንጋጋ ትመታለህ፤
የክፉዎችንም ጥርስ ትሰባብራለህ።
8 ማዳንየእግዚአብሔርነው፤
በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን።ሴላ