ሁለቱ መንገዶች
1 በክፉዎች ምክር የማይሄድ፣
በኀጢአተኞች መንገድ የማይቆም፣
በፌዘኞችም ወንበር የማይቀመጥ፣
ሰው ብፁዕ ነው።
2 ነገር ግን ደስ የሚሰኘውበእግዚአብሔርሕግ ነው፤
ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያሰላስለዋል።
3 እርሱም በወራጅ ውሃ ዳር እንደ ተተከለች፣
ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፣
ቅጠሏም እንደማይጠወልግ ዛፍ ነው፤
የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
4 ክፉዎች ግን እንዲህ አይደሉም፤
ነገር ግን ነፋስ ጠራርጎ እንደሚወስደው፣
ገለባ ናቸው።
5 ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ ፊት፣
ኀጢአተኞችም በጻድቃን ማኅበር መቆም አይችሉም፤
6 እግዚአብሔርየጻድቃንን መንገድ ይጠብቃልና፤
የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች።