ሕዝቅያስ ቤተ መቅደሱን አነጻ
1 ሕዝቅያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ። እናቱም አቡ የተባለች፤ የዘካርያስ ልጅ ነበረች።
2 አባቱ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ፣ እርሱምበእግዚአብሔርፊት ቅን ነገር አደረገ።
3 በዘመነ መንግሥቱ በመጀመሪያው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወርየእግዚአብሔርንቤተ መቅደስ በሮች ከፈተ፤ አደሳቸው።
4 ካህናቱንና ሌዋውያኑን አስገብቶ በምሥራቅ በኩል ባለው አደባባይ ላይ በመሰብሰብ፣
5 እንዲህ አላቸው፤ “እናንት ሌዋውያን፤ ስሙኝ! ራሳችሁን አሁኑኑ ቀድሱ፤ የአባቶቻችሁንአምላክየእግዚአብሔርንም ቤተ መቅደስ ቀድሱ። ርኩስ ነገርንም ሁሉ ከመቅደሱ አስወግዱ።
6 አባቶቻችን ታማኞች አልነበሩም፣በአምላካችንበእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ተውትም።ከእግዚአብሔርማደሪያ ፊታቸውን መለሱ፤ ጀርባቸውንም አዞሩበት።
7 የሰበሰቡንም በሮች ዘጉ፤ መብራቶቹንም አጠፉ። ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ዕጣን አላጠኑም፤ በመቅደሱም የሚቃጠል መሥዋዕት አላቀረቡም።
8 ስለዚህየእግዚአብሔርቊጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ወርዶአል፤ እናንተ በገዛ ዓይናችሁ እንደምታዩት ለድንጋጤ፣ ለመደነቂያና ለመዘበቻ አሳልፎ ሰጣቸው።
9 በዚህ ምክንያት አባቶቻችን በሰይፍ ወደቁ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን፣ ሚስቶቻችንም ተማረኩ።
10 አሁንም አስፈሪ ቊጣው ከእኛ እንዲመለስ፣ ከእስራኤልአምላክከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት አስቤአለሁ።
11 ልጆቼ ሆይ፤ እንግዲህ ቸል አትበሉ፤ በፊቱ እንድትቆሙና እንድታገለግሉት፣ በፊቱም አገልጋዮቹ እንድትሆኑና ዕጣን እንድ ታጥኑለትእግዚአብሔርመርጦአችኋልና።”
12 ከዚያም እነዚሁ ሌዋውያን በሥራው ላይ ተሰማሩ፤ ከቀዓት ዘሮች የአማሢ ልጅ መሐትና የዓዛርያስ ልጅ ኢዮኤል፤
ከሜራሪ ዘሮች፣
የአብዲ ልጅ ቂስና የይሃሌልኤል ልጅ ዓዛርያስ፤
ከጌድሶን ዘሮች፣
የዛማት ልጅ ዮአክና የዮአክ ልጅ ዔድን፤
13 ከኤሊጻፋን ዘሮች፣
ሺምሪና ይዒኤል፤
ከአሳፍ ዘሮች፣
ዘካርያስና መታንያ፤
14 ከኤማን ዘሮች፣
ይሒኤልና ሰሜኢ፣
ከኤዶታም ዘሮች፣
ሸማያና ዑዝኤል።
15 ወንድሞቻቸውን ከሰበሰቡና ራሳቸውን ከቀደሱ በኋላ፣ ንጉሡየእግዚአብሔርንቃል ተከትሎ ባዘዘው መሠረትየእግዚአብሔርንቤተ መቅደስ ለማንጻት ገቡ።
16 ካህናቱየእግዚአብሔርንመቅደስ ለማንጻት ወደ ውስጡ ገቡ።በእግዚአብሔርቤተ መቅደስ ውስጥ ያገኙትንም ማናቸውንም የረከሰ ነገር ወደእግዚአብሔርቤተ መቅደስ አደባባይ አወጡት። ሌዋውያኑም ተሸክመው በመውሰድ በቄድሮን ሸለቆ ውስጥ ጣሉት።
17 ማንጻቱንም በመጀመሪያው ወር፣ በመጀመሪያው ቀን ጀምረው በዚያኑ ወር በስምንተኛው ቀን እስከ መቅደስ ሰበሰብ ደረሱ፤ በሚቀጥሉትም ስምንት ቀናትየእግዚአብሔርንቤተ መቅደስ ቀደሱ፤ የመቀደሱም ሥራ በመጀመሪያው ወር በዐሥራ ስድስተኛው ቀን ተጠናቀቀ።
18 ከዚያም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ገብተው እንዲህ አሉ፤ “የእግዚአብሔርንቤተ መቅደስ በሙሉ፣ የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበትን መሠዊያ ከነዕቃዎቹ ሁሉ፣ ኀብስተ ገጹ የሚቀመጥበትን ጠረጴዛ፣ ከነዕቃዎቹ አንጽተናል።
19 ንጉሥ አካዝ ነግሦ ሳለ ታማኝነቱን ትቶ፣ ከቦታቸው ያነሣቸውን ዕቃዎች ሁሉ አዘጋጅተን ቀድሰናቸዋል፤ እነሆ፤ ዕቃዎቹበእግዚአብሔርቤተ መቅደስ መሠዊያ ፊት ለፊት ናቸው።”
20 በማግስቱም ጧት በማለዳ፣ ንጉሥ ሕዝቅያስ የከተማዪቱን ሹማምት በአንድነት ሰብስቦ፣ ወደእግዚአብሔርቤተ መቅደስ ወጣ፤
21 እነርሱም ስለ መንግሥቱ፣ ስለ መቅደሱና ስለ ይሁዳ ሰባት ወይፈኖች፣ ሰባት አውራ በጎች፣ ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶችና ሰባት ተባዕት የፍየል ጠቦቶች ለኀጢአት መሥዋዕት አቀረቧቸው፤ ንጉሡም እነዚህንበእግዚአብሔርመሠዊያ ላይ እንዲያቀርቡ የአሮንን ዘሮች ካህናቱን አዘዘ።
22 ካህናቱም ወይፈኖቹን ዐርደው ደሙን በመውሰድ በመሠዊያው ላይ ረጩት፤ አውራ በጎቹንም ዐርደው ደሙን በመሠዊያው ላይ ረጩት፤ እንደዚሁም ጠቦቶቹን ዐርደው ደሙን በመሠዊያው ላይ ረጩት።
23 ለኀጢአት መሥዋዕት የሚሆኑትን ፍየሎች በንጉሡና በጉባኤው ፊት አቀረቡ፤ እነርሱም እጆቻቸውን ጫኑባቸው።
24 ንጉሡ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኀጢአት መሥዋዕት ስለ እስራኤል ሁሉ እንዲቀርብ አዞ ስለ ነበር፣ ካህናቱ ፍየሎቹን ዐርደው ስለ እስራኤል ሁሉ ማስተስረያ እንዲሆን የኀጢአት መሥዋዕት በማድረግ ደሙን በመሠዊያው ላይ አቀረቡ።
25 ንጉሥ ሕዝቅያስም በዳዊት፣ በንጉሡ ባለ ራእይ በጋድና በነቢዩ በናታን በተሰጠው መመሪያ መሠረት ሌዋውያኑን ጸናጽል፣ በገናና መሰንቆ አስይዞበእግዚአብሔርቤተ መቅደስ መደባቸው፤ ይህም በነቢያት አማካይነት ከእግዚአብሔር የተሰጠ ትእዛዝ ነበር።
26 ስለዚህ ሌዋውያኑ የዳዊትን የዜማ ዕቃዎች፣ ካህናቱም መለከቶቻቸውን ይዘው ዝግጁ በመሆን ቆሙ።
27 ከዚህ በኋላ ሕዝቅያስ የሚቃጠለው መሥዋዕት በመሠዊያው ላይ እንዲቀርብ አዘዘ። መሥዋዕቱ ማረግ በጀመረ ጊዜም፣ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት የዜማ ዕቃዎችና በመለከት የታጀበ ዝማሬም ጀመረ።
28 መዘምራኑ በሚዘም ሩበትና መለከተኞቹም በሚነፉበት ጊዜም መላው ጉባኤ አጎንብሰው ሰገዱ፤ የሚቃጠለው መሥዋዕት እስኪጠናቀቅ ድረስም ይህ ሁሉ ቀጠለ።
29 መሥዋዕቱ ሁሉ ቀርቦ ካበቃ በኋላ፣ ንጉሡና አብረውት የነበሩት ሁሉ ተንበርክከው ሰገዱ።
30 ንጉሥ ሕዝቅያስና ሹማምቱ፣ ሌዋውያኑ በዳዊትና በባለ ራእዩ በአሳፍ ቃልእግዚአብሔርንእንዲያመሰግኑ አዘዙ። እነርሱም ውዳሴውን በደስታ ዘመሩ፤ ራሳቸውንም አጎንብሰው ሰገዱ።
31 ከዚያም ሕዝቅያስ፣ “እነሆ፤ ራሳችሁንለእግዚአብሔርቀድሳችኋል፤ አሁንም ቅረቡ፤ መሥዋዕትና የምስጋና ስጦታ ወደእግዚአብሔርቤተ መቅደስ አምጡ” አላቸው። ስለዚህ ጉባኤው መሥዋዕትና የምስጋና ስጦታ አመጡ፤ ልባቸው የፈቀደ ሁሉም የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ።
32 ጉባኤውም ያመጣው የሚቃጠለው መሥዋዕት ብዛት ሰባ ወይፈኖች፣ መቶ አውራ በጎችና ሁለት መቶ ተባዕት የበግ ጠቦቶች ናቸው፤ ሁሉም የሚቃጠል መሥዋዕት ሆነውለእግዚአብሔርየሚቀርቡ ነበሩ።
33 ለመሥዋዕት የተቀደሱት እንስሳት ባጠቃላይ ስድስት መቶ ወይፈን፣ ሦስት ሺህ በጎችና ፍየሎች ነበሩ።
34 ይሁን እንጂ ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ቈዳ ሁሉ ለመግፈፍ ቊጥራቸው እጅግ ጥቂት ነበር፤ ስለዚህ ወገኖቻቸው የሆኑት ሌዋውያን ሥራው እስኪያልቅና ሌሎች ካህናት እስኪቀደሱ ድረስ ረዷቸው፤ ሌዋውያኑም ራሳቸውን ለመቀደስ ከካህናቱ ይልቅ ጠንቃቆች ነበሩና።
35 ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋር የሚቀርበውን የኅብረት መሥዋዕትስብና የመጠጡን ቍርባን ጨምሮ የሚቃጠለው መሥዋዕት እጅግ ብዙ ነበር። በዚህ ሁኔታምየእግዚአብሔርቤት አገልግሎት እንደ ገና ተደራጀ።
36 ሕዝቅያስና ሕዝቡ ነገሩ ሁሉ እንዲህ በተፋጠነ ሁኔታ እንዲከናወን እግዚአብሔር ስለረዳቸው ሐሴት አደረጉ።