2 ዜና መዋዕል 17

የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ

1 ልጁ ኢዮሣፍጥ በእርሱ ፈንታ ነገሠ፤ በእስራኤል ላይ በረታ።

2 እርሱም በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ውስጥ ወታደር አኖረ፤ እንዲሁም በይሁዳ ምድርና አባቱ አሳ በያዛቸው በኤፍሬም መንደሮች ዘበኞች አስቀመጠ።

3 በለጋነት ዕድሜው አባቱ ዳዊት በሄደበት መንገድ ስለሄደ፣እግዚአብሔርከኢዮሣፍጥ ጋር ነበር፤ የበኣልንም አማልክት አልጠየቀም፤

4 ነገር ግን ከእስራኤል ድርጊት ይልቅ፣ የአባቱን ፈለገ፤ ትእዛዛቱንም ተከተለ።

5 እግዚአብሔርምመንግሥቱን በእጁ አጸናለት፤ መላው ይሁዳም ስጦታ አመጣለት፤ ከዚህ የተነሣም ታላቅ ብልጽግናና ክብር አገኘ።

6 ልቡምበእግዚአብሔርመንገድ የጸና ነበር፤ እንደዚሁም ማምለኪያ ኰረብታዎችንና የአሼራ ዐምዶችን ከይሁዳ አስወገደ።

7 በነገሠ በሦስተኛው ዓመት በይሁዳ ከተሞች ያስተምሩ ዘንድ ሹማምቱን ማለትም ቤን ኀይልን፣ አብድያስን፣ ዘካርያስን፣ ናትናኤልንና ሚካያን ላካቸው።

8 ከእነዚህም ጋር ጥቂት ሌዋውያን ነበሩ፤ ስማቸውም፦ ሸማያ፣ ነታንያ፣ ዝባድያ፣ አሣሄል፣ ሰሚራሞት፣ ዮናትን፣ አዶንያስ፣ ጦብያና ጦባዶንያ ነበር። ካህናቱ ደግሞ ኢሊሳማና ኢዮራም ነበሩ።

9 እነርሱምየእግዚአብሔርንየሕጉን መጽሐፍ ይዘው በመሄድ በይሁዳ ሁሉ ላለው ሕዝብ አስተማሩ፤ በይሁዳ ከተሞች ሁሉ በመዘዋ ወርም ሕዝቡን አስተማሩ።

10 በይሁዳ ዙሪያ ባሉ ነገሥታት ሁሉ ላይከእግዚአብሔርዘንድ ፍርሀት ስለወደቀባቸው ኢዮሣፍጥን አልተዋጉትም።

11 ከፍልስጥኤማውያንም አንዳንዶቹ እጅ መንሻ አመጡለት፤ ጥሬ ብርም ገበሩለት፤ ዐረቦችም ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ በግና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ ፍየል መንጋ አመጡለት።

12 ኢዮሣፍጥም እያየለ ሄደ፤ በይሁዳም ምሽጎችና የዕቃ ማከማቻ ከተሞች ሠራ።

13 በይሁዳም ከተሞች እጅግ ብዙ ስንቅና ትጥቅ ነበረው። ደግሞም በቂ ልምድ ያላቸውን ተዋጊዎች በኢየሩሳሌም አስቀመጠ።

14 እነርሱም በየቤተ ሰቦቻቸው ሲመዘገቡ እንደሚከተለው ነው፤ ከይሁዳ የየሻለቃው አዛዦች፣ አዛዡ ዓድና ከሦስት መቶ ሺ ተዋጊዎች ጋር፤

15 ከእርሱ ቀጥሎም አዛዡ የሆሐናን ከሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ ጋር፤

16 ከዚያ ቀጥሎምለእግዚአብሔርአገልግሎት በፈቃደኝነት ራሱን የሰጠው የዝክሪ ልጅ ዓማስያ ከሁለት መቶ ሺህ ተዋጊዎች ጋር፤

17 ከብንያምም ጀግናው ወታደር ኤሊዳሄ ቀስትና ጋሻ ከያዙ ከሁለት መቶ ሺ ሰዎች ጋር፤

18 ቀጥሎም ዮዛባት ለጦርነት ዝግጁ ከሆኑ ከአንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ሰዎች ጋር፤

19 እነዚህ እንግዲህ በመላው ይሁዳ በተመሸጉት ከተሞች ካስቀመጣቸው ሌላ፣ ንጉሡን ያገለግሉ የነበሩ ሰዎች ናቸው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *