2 ዜና መዋዕል 15

ንጉሥ አሳ ያደረገው ተሐድሶ

1 የእግዚአብሔር መንፈስ በዖዴድ ልጅ በአዛርያስ ላይ መጣ።

2 እርሱም አሳን ሊገናኘው ወጣ፤ እንዲህም አለው፤ አሳ፣ እናንተም ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፤ አድምጡኝ፤ እናንተከእግዚአብሔርጋር ስትሆኑ፣ እርሱም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ብትፈልጉት ይገኝላችኋል፤ ብትተውት ግን፣ ይተዋችኋል።

3 እስራኤል ያለ እውነተኛ አምላክ፣ ያለ አስተማሪ ካህንና ያለ ሕግ ብዙ ዘመን አሳልፈዋል።

4 በመከራቸው ጊዜ ግን፣ ወደ እስራኤልአምላክወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው።

5 በዚያን ዘመን በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ዘንድ ታላቅ ሁከት ስለ ነበር፣ በሰላም ወጥቶ መግባት አስተማማኝ አልነበረም።

6 እግዚአብሔር በተለያየ መከራ ያስጨንቃቸው ስለ ነበር፣ አንዱ መንግሥት በሌላው መንግሥት፣ አንዱም ከተማ በሌላው ከተማ ይደመሰስ ነበር።

7 እናንተ ግን የድካማችሁን ዋጋ ስለምታገኙ በርቱ፤ እጃችሁም አይላላ።”

8 አሳ ይህን ቃልና የነቢዩን የዖዴድን ልጅየዓዛርያስን ትንቢት በሰማ ጊዜ በረታ። ከመላው ይሁዳና ከብንያም ምድር፣ በኤፍሬምም ኰረብታዎች ላይ ከያዛቸው ከተሞች አስጸያፊዎቹን ጣዖታት አስወገደ።ከእግዚአብሔርመቅደስ ሰበሰብ ፊት ለፊት የነበረውንምየእግዚአብሔርመሠዊያ አደሰ።

9 አምላኩእግዚአብሔር ከእርሱ ጋር መሆኑን ባዩ ጊዜ፣ ከእስራኤል ብዙ ሰዎች እርሱን ተጠግተው ነበር፤ እርሱም ይሁዳንና ብንያምን እንዲሁም ከኤፍሬም፣ ከምናሴና ከስምዖን መጥተው ከእነርሱ ጋር የተቀመጡትን ሰበሰበ።

10 እነርሱም በአሳ ዘመነ መንግሥት በዐሥራ አምስተኛው ዓመት፣ በሦስተኛው ወር በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ።

11 በዚያን ጊዜ በምርኮ ካመጡት ውስጥ ሰባት መቶ በሬ፣ ሰባት ሺ በግና ፍየልለእግዚአብሔርሠዉ።

12 የአባቶቻቸውንምአምላክእግዚአብሔርን በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው ይሹ ዘንድ ቃል ኪዳን አደረጉ።

13 የእስራኤልንአምላክእግዚአብሔርን የማይፈልግ ሁሉ ግን፣ ትንሽም ሆነ ትልቅ፣ ወንድም ሆነ ሴት እንዲገደል አደረጉ።

14 ይህንንም በታላቅ ድምፅ፣ በእልልታ፣ በእምቢልታና በመለከት ድምፅለእግዚአብሔርማሉ።

15 በፍጹም ልባቸው ስለማሉም የይሁዳ ሕዝብ በመሐላው ደስ ተሰኙ። እግዚአብሔርን ከልብ ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው፤ ስለዚህእግዚአብሔርበሁሉም አቅጣጫ ዕረፍት ሰጣቸው።

16 እንዲሁም ንጉሥ አሳ አያቱን ማዓካን ለአስጸያፊዋ የአሼራ ጣዖት ዐምድ ስላቆመች ከእቴጌነት ክብሯ ሻራት። አሳም ዐምዱን ቈርጦ በመሰባበር በቄድሮን ሸለቆ አቃጠለው።

17 ምንም እንኳ ማምለኪያ ኰረብታዎችን ሙሉ በሙሉ ከእስራኤል ባያስወግድም፣ የአሳ ልብ በዘመኑ ሁሉ ፈጽሞለእግዚአብሔርየተገዛ ነበር።

18 እርሱና አባቱ የቀደሱትን ብሩን፣ ወርቁንና ልዩ ልዩ ዕቃ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገባ።

19 እስከ ሠላሳ አምስተኛው የአሳ ዘመነ መንግሥት ድረስ ምንም ዐይነት ጦርነት አልነበረም።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *