2 ዜና መዋዕል 5

1 ሰሎሞንለእግዚአብሔርቤተ መቅደስ የሠራው ሥራ ሁሉ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ አባቱ ዳዊት የቀደሰውን ብሩንና ወርቁን፣ ዕቃዎቹንም ሁሉ አምጥቶ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት አኖራቸው።

ታቦቱ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ

2 ከዚያ በኋላ ሰሎሞንየእግዚአብሔርንየኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን እንዲያመጡ፣ የእስራኤልን ሽማግሌዎች፣ የየነገዱን መሪዎች ሁሉና የእስራኤላውያንን የቤተ ሰብ አለቆች በኢየሩሳሌም ሰበሰበ።

3 የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ የሰባተኛው ወር በዓል በሚከበርበት ጊዜ፣ በንጉሡ ፊት ተሰበሰቡ።

4 የእስራኤል ሽማግሌዎች በተሰበሰቡም ጊዜ ሌዋውያኑ ታቦቱን አነሡት፤

5 ታቦቱን፣ የመገናኛ ድንኳኑንና በውስጡ ያሉትን የተቀደሱ ዕቃዎች ሁሉ ይዘው ወደ ላይ ወጡ፤ ሌዋውያን የሆኑ ካህናትም ተሸከሟቸው።

6 ንጉሥ ሰሎሞንና በአጠገቡ የተሰበሰበው መላው የእስራኤል ጉባኤ ስፍር ቊጥር የሌላቸውን በጎችና በሬዎች በታቦቱ ፊት ሠዉ።

7 ካህናቱምየእግዚአብሔርንየኪዳኑን ታቦት የቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል ወደ ሆነው ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ አግብተው ከኪሩቤል ክንፍ በታች ባለው ስፍራው አኖሩት።

8 ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ከታቦቱ በላይ ባለው ስፍራ ላይ ዘርግተው፣ ታቦቱንና መሎጊያዎቹን ሸፈኑ።

9 መሎጊያዎቹም በጣም ረጃጅም ከመሆናቸው የተነሣ፣ ታቦቱ እስካለበት ድረስ ያሉት ጫፎቻቸው ከቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት ይታዩ ነበር፤ ከመቅደሱ ውጭ ግን አይታዩም ነበር፤ ዛሬም እዚያው ቦታ ይገኛሉ።

10 እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ ከእነርሱ ጋር ኪዳን ባደረገ ጊዜ፣ ሙሴ በኮሬብ ተራራ በውስጡ ካስቀመጣቸው ከሁለቱ ጽላቶች በቀር በታቦቱ ውስጥ ምንም አልነበረም።

11 ካህናቱም ከቤተ መቅደሱ ወጡ፤ እዚያ የነበሩት ካህናት በምድባቸው መሰረት ባይሆንም፣ ሁሉም ራሳቸውን ቀድሰው ነበር።

12 መዘምራን የነበሩት ሌዋውያን ሁሉ፣ አሳፍ፣ ኤማን፣ ሄማንና ኤዶታም፣ ወንዶች ልጆቻቸውና የሥጋ ዘመዶቻቸው ሁሉ ያማረ ቀጭን በፍታ ለብሰው፣ ከመሠዊያው በስተ ምሥራቅ በኩል ቆመው ጸናጽል ይጸነጽሉ፣ በገና ይደረድሩና መሰንቆ ይመቱ ነበር፤ እነርሱም መለከት በሚነፉ አንድ መቶ ሃያ ካህናት ታጅበው ነበር።

13 መለከት ነፊዎችና ዘማሪዎችም በአንድነት አንድ ድምፅ ሆነውለእግዚአብሔርውዳሴና ምስጋና አቀረቡ፤ በመለከት፣ በጸናጽልና በሌሎች መሣሪያዎች ታጅበውም ድምፃቸውን ከፍ በማድረግእግዚአብሔርንእያወደሱ፣

“እርሱ ቸር ነው፣

ፍቅሩም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”

እያሉ ዘመሩ።

ከዚያምየእግዚአብሔርቤተ መቅደስ በደመና ተሞላ።

14 የእግዚአብሔርክብር የአምላክን ቤተ መቅደስ ሞልቶት ስለ ነበር፣ ከደመናው የተነሣ ካህናቱ አገልግሎታቸውን ማከናወን አልቻሉም።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *