1 ዜና መዋዕል 23

ሌዋውያን

1 ዳዊት በሸመገለና ዕድሜው በገፋ ጊዜ፣ ልጁን ሰሎሞንን በእስራኤል ላይ አነገሠው።

2 እንዲሁም መላውን የእስራኤልን መሪዎች፣ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ሁሉ በአንድነት ሰበሰበ።

3 ዕድሜያቸው ሠላሳና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቈጠሩ፤ ቊጥራቸውም በጠቅላላው ሠላሳ ስምንት ሺህ ነበረ።

4 ዳዊትም እንዲህ አለ፤ “ከእነዚህ መካከል ሃያ አራቱ ሺህየእግዚአብሔርንቤተ መቅደስ ሥራ ይቈጣጠሩ፤ ስድስቱ ሺህ ደግሞ ሹሞችና ዳኞች ይሁኑ፤

5 አራቱ ሺህ የቅጥሩ በር ጠባቂዎች ይሁኑ፤ አራቱ ሺህ ደግሞ ለዚሁ ብዬ ባዘጋጀሁት የዜማ መሣሪያእግዚአብሔርንያመስግኑ”።

6 ዳዊትም ሌዋውያኑን በሌዊ ልጆች በጌድሶን፣ በቀዓትና በሜራሪ በየጐሣቸው መደባቸው።

ጌድሶናውያን

7 ከጌድሶናውያን ወገን፤

ለአዳን፣ ሰሜኢ።

8 የለአዳን ወንዶች ልጆች፤

የመጀመሪያው ይሒኤል፣ ዜቶም፣ ኢዮኤል፤ ባጠቃላይ ሦስት ናቸው።

9 የሰሜኢ ወንዶች ልጆች፤

ሰሎሚት፣ ሐዝኤል፣ ሐራን፤ ባጠቃላይ ሦስት ናቸው።

እነዚህ የለአዳን ቤተ ሰብ አለቆች ናቸው።

10 የሰሜኢ ወንዶች ልጆች፤

ኢኢት፣ ዚዛ፣ የዑስ፣ በሪዓ፤ እነዚህ

አራቱ የሰሜኢ ልጆች ናቸው።

11 የመጀመሪያው ኢኢት፣ ሁለተኛው ደግሞ ዚዛነበረ፤ የዑስና በሪዓ ግን ብዙ ወንዶች ልጆች አልነበሯቸውም፤ ስለዚህ የተቈጠሩት በሥራ መደብ እንደ አንድ ቤተ ሰብ ሆነው ነው።

ቀዓታውያን

12 የቀዓት ወንዶች ልጆች፤

እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል፤ ባጠቃላይ አራት ናቸው።

13 የእንበረም ወንዶች ልጆች፤

አሮን፣ ሙሴ።

አሮን የተቀደሰ እንዲሆን ተለየ፤ እርሱና ዘሮቹ ለዘላለም ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች እንዲቀድሱ፣በእግዚአብሔርፊት መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፣ በፊቱ እንዲያገለግሉና በስሙም ለዘላለም እንዲባርኩ ተለዩ።

14 የእግዚአብሔርሰው የሙሴ ወንዶች ልጆችም እንደ ሌዊ ነገድ ሆነው ተቈጠሩ።

15 የሙሴ ወንዶች ልጆች፤

ጌርሳም፣ አልዓዛር።

16 የጌርሳም ዘሮች፤

ሱባኤል።

17 የአልዓዛር ዘሮች፤

የመጀመሪያው ረዓብያ ነበረ።

አልዓዛር ሌሎች ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ የረዓብያ ወንዶች ልጆች ግን እጅግ ብዙ ነበሩ።

18 የይስዓር ወንዶች ልጆች፤

የመጀመሪያው ሰሎሚት።

19 የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤

የመጀመሪያው ይሪያ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛው ይቅምዓም ነበሩ።

20 የዑዝኤል ወንዶች ልጆች፤

የመጀመሪያው ሚካ፣ ሁለተኛው ይሺያ ነበሩ።

ሜራሪያውያን

21 የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤

ሞሖሊ፣ ሙሲ።

የሞሐሊ ወንዶች ልጆች፤

አልዓዛርና ቂስ ነበሩ።

22 አልዓዛር ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤ ልጆቹ ሴቶች ብቻ ነበሩ፤ እነርሱንም የአጎታቸው የቂስ ልጆች አገቡአቸው።

23 የሙሲ ወንዶች ልጆች፤

ሞሖሊ፣ ዔደር፣ ኢያሪሙት ባጠቃላይ ሦስት ናቸው።

24 እንግዲህ እነዚህ የቤተ ሰቡ አለቆች ሆነው እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተመዝግበው የተቈጠሩት የሌዊ ዘሮች ናቸው፤ ዕድሜአቸውም ሃያና ከዚያ በላይ የሆናቸውበእግዚአብሔርቤተ መቅደስ ውስጥ የሚያገለግሉ ነበሩ።

25 ዳዊት እንዲህ ብሎ ነበርና፣ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ዕረፍት ሰጥቷል፤ በኢየሩሳሌምም ለዘላለም ለመኖር መጥቷል፤

26 ሌዋውያን ከእንግዲህ ወዲህ ድንኳኑን ወይም የመገልገያ ዕቃውን ሁሉ መሸከም የለባቸውም።”

27 ዳዊት በሰጠው የመጨረሻ መመሪያ መሠረት የተቈጠሩት ሌዋውያን ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ ነበረ።

28 የሌዋውያኑ ተግባርበእግዚአብሔርቤተ መቅደስ አገልግሎት የአሮንን ዘሮች መርዳት፣ የቤተ መቅደሱን ቅጥር ግቢና ክፍሎች መንከባከብ፣ የተቀደሱ ዕቃዎችን ሁሉ ማንጻትና በእግዚአብሔር ቤት ያሉትን ሌሎች ተግባሮች ማከናወን ነበር።

29 እንዲሁም መባ ሆኖ የሚቀርበውን ኅብስተ ገጽ፣ የእህል ቍርባኑን ዱቄት፣ ያለ እርሾ የሚጋገረውን ቂጣ የሚጋግሩ፣ የሚያቦኩና የሚሰፈረውንም ሆነ የሚለካውን ሁሉ በኀላፊነት የሚቈጣጠሩ እነርሱ ነበሩ።

30 በየዕለቱምእግዚአብሔርንለማመስገንና ለመወደስ ጠዋት ጠዋት ይቆሙ ነበር፤ ይህንንም ማታ ማታ

31 እንዲሁም በየሰንበቱ፣ በወር መባቻ በዓልና በተደነገጉት በዓላት ሁሉ ይፈጽሙ ነበር፤ በተወሰነላቸው ቊጥርና በተሰጠውም መመሪያ መሠረት ዘወትርበእግዚአብሔርፊት ያገለግሉ ነበር።

32 ስለዚህ ሌዋውያኑ ለመገናኛው ድንኳንና ለመቅደሱ እንዲሁም በወንድሞቻቸው በአሮን ዘሮች ሥር ሆነውለእግዚአብሔርቤተ መቅደስ ያለባቸውን ኀላፊነት ያከናውኑ ነበር።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *