ዳዊት ተዋጊ ሰራዊቱን ቈጠረ
1 ሰይጣን በእስራኤል ላይ ተነሥቶ ዳዊት የእስራኤልን ሕዝብ እንዲቈጥር አነሣሣው።
2 ዳዊትም ኢዮአብንና የሰራዊቱን አዛዦች፣ “ሄዳችሁ ከቤርሳቤህ እስከ ዳን ያሉትን እስራኤላውያን ቍጠሩ፤ ከዚያም ምን ያህል እንደሆኑ አውቅ ዘንድ ንገሩኝ” አላቸው።
3 ኢዮአብ ግን፣ “እግዚአብሔርየእስራኤልን ሰራዊት አሁን ካለው በላይ በመቶ እጥፍ ያብዛው፤ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ ሁሉስ ቢሆኑ የጌታዬ ተገዢዎች አይደሉምን? ታዲያ ጌታዬ ይህን ማድረግ ለምን አስፈለገው? ለምንስ በእስራኤል ላይ በደል ያመጣል?” አለ።
4 ይሁን እንጂ የንጉሡ ቃል ኢዮአብን አሸነፈው፤ ስለዚህ ኢዮአብ ወጣ፤ በመላው እስራኤል ከተዘዋወረ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
5 ኢዮአብም የተዋጊዎቹን ሰዎች ቍጥር ለዳዊት አቀረበ፤ እነዚህም በመላው እስራኤል አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ፣ በይሁዳ ደግሞ አራት መቶ ሰባ ሺህ ሲሆኑ፣ ሁሉም ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ነበሩ።
6 ኢዮአብ ግን የንጉሡ ትእዛዝ አስጸያፊ ነበረና፣ የሌዊንና የብንያምን ነገድ ጨምሮ አልቈጠረም።
7 ይህ ትእዛዝ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነበር፤ ስለዚህ እግዚአብሔር እስራኤልን ቀጣ።
8 ከዚያም ዳዊት እግዚአብሔርን፣ “ይህን በማድረጌ እጅግ በድያለሁ፤ የፈጸምሁትም የስንፍና ሥራ ስለ ሆነ፣ የባሪያህን በደል እንድታስወግድ እለምንሃለሁ” አለ።
9 እግዚአብሔርምየዳዊት ባለ ራእይ የሆነውን ጋድን እንዲህ አለው፤
10 “ሂድና ለዳዊት እንዲህ ብለው ንገረው፤‘እግዚአብሔርየሚለው ይህን ነው፤ እነሆ፣ ሦስት ምርጫ ሰጥቼሃለሁ፤ በአንተ ላይ እንዳደርስብህ አንዱን ምረጥ።’ ”
11 ስለዚህ ጋድ ወደ ዳዊት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔርየሚለው ይህን ነው፤ ‘በል እንግዲህ አንዱን ምረጥ፤
12 የሦስት ዓመት ራብ ወይስ የጠላቶችህ ሰይፍ ለሦስት ወር አይሎብህ መጥፋት ወይስ ሦስት ቀንየእግዚአብሔርሰይፍ መቅሠፍት በምድሪቱ ላይ ወርዶየእግዚአብሔርመልአክ እስራኤልን ሁሉ ያጥፋ?’ ለላከኝ ምን እንደምመልስ ቍርጡን ንገረኝ።”
13 ዳዊትም ጋድን፣ “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ መሕረቱ ታላቅ ስለ ሆነበእግዚአብሔርእጅ መውደቅ ይሻለኛል፤ በሰው እጅስ አልውደቅ” አለ።
14 ስለዚህእግዚአብሔርበእስራኤል ላይ መቅሠፍት ላከ፤ ከእስራኤልም ሰባ ሺህ ሰው ዐለቀ።
15 እንዲሁም እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን እንዲያጠፉ መልአክ ላከ፤ መልአኩ ሊያጠፋትም ሲልእግዚአብሔርአይቶ ስለሚደርሰው ጥፋት አዘነ፤ ሕዝቡን የሚያጠፋውንም መልአክ፣ “እጅህን መልስ” አለው።የእግዚአብሔርምመልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።
16 ዳዊት ቀና ብሎ ሲመለከት፣የእግዚአብሔርመልአክ በሰማይና በምድር መካከል ቆሞ አየ፤ መልአኩም በኢየሩሳሌም ላይ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ ነበር፤ ከዚያም ዳዊትና ሽማግሌዎቹ ማቅ እንደ ለበሱ በግምባራቸው ተደፉ።
17 ዳዊት እግዚአብሔርን፣ “ተዋጊዎቹ እንዲቈጠሩ ያዘዝሁ እኔ አይደለሁምን? ኀጢአት የሠራሁትም ሆነ የበደልሁት እኔ ነኝ፤ እነዚህ እኮ በጎች ናቸው፤ ታዲያ እነርሱ ምን አደረጉ?እግዚአብሔርአምላኬ ሆይ፤ እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን እንጂ፣ መቅሠፍቱ በሕዝብህ ላይ አይውረድ” አለ።
18 ከዚያምየእግዚአብሔርመልአክ ዳዊት ወጥቶ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ላይለእግዚአብሔርመሠዊያ ይሠራ ዘንድ እንዲነግረው ጋድን አዘዘው።
19 ዳዊትም ጋድበእግዚአብሔርስም በነገረው ቃል መሠረት ለመፈጸም ወጣ።
20 ኦርና ስንዴ በመውቃት ላይ ሳለ ዘወር ሲል መልአኩን አየ፤ አብረውት የነበሩት አራት ወንዶች ልጆቹም ተሸሸጉ።
21 ዳዊት ወደ እርሱ እየቀረበ መጣ፤ ኦርና ቀና ብሎ ሲመለከት፣ ዳዊትን አየው፤ ከዐውድማውም ወጥቶ መሬት ላይ ለጥ ብሎ በመደፋት ለዳዊት እጅ ነሣ።
22 ዳዊትም፣ “በሕዝቡ ላይ የወረደው መቅሠፍት እንዲወገድለእግዚአብሔርመሠዊያ እሠራ ዘንድ ዐውድማህን ልውሰደው፤ ሙሉውን ዋጋ እከፍልሃለሁ” አለው።
23 ኦርናም ዳዊትን፣ “እንዲሁ ውሰደው፤ ጌታዬ ንጉሥ ደስ ያለውን ያድርግ፤ እነሆ፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎቹን፣ መውቂያ በትሮቹን ለማቀጣጠያ ዕንጨት፣ ስንዴውን ደግሞ ለእህል ቍርባን እንዲሆን እሰጣለሁ፤ ሁሉንም እኔ እሰጣለሁ።” አለ።
24 ንጉሥ ዳዊት ግን ለኦርና “አይደረግም፤ ሙሉውን ዋጋ እኔ እከፍላለሁ፤ የአንተ የሆነውንለእግዚአብሔርለማቅረብ አልፈልግም፤ ዋጋ ያልከፈልሁበትንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ አላቀርብም” ሲል መለሰለት።
25 ስለዚህ ዳዊት ለኦርና የቦታውን ዋጋ ስድስት መቶ ሰቅልወርቅ ከፈለ።
26 ዳዊትም በዚያለእግዚአብሔርመሠዊያ ሠርቶ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕትአቀረበ።እግዚአብሔርንምጠራ፤እግዚአብሔርምየሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ከሰማይ በእሳት መለሰለት።
27 ከዚያምእግዚአብሔርለመልአኩ ተናገረ፤ መልአኩም ሰይፉን ወደ አፎቱ መለሰ።
28 በዚያን ጊዜ ዳዊት፣እግዚአብሔርበኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ላይ እንደ መለሰለት ሲያይ፣ በዚያው ቦታ መሥዋዕት ማቅረብ ጀመረ።
29 ሙሴ በምድረ በዳ የሠራውየእግዚአብሔርማደሪያ ድንኳንና የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበት መሠዊያ በዚያ ጊዜ በገባዖን ኮረብታ ላይ ነበረ።
30 ዳዊት የእግዚአብሔርን መልአክ ሰይፍ ስለ ፈራ ወደዚያ ሄዶእግዚአብሔርንለመጠየቅ አልቻለም።