1 ነገሥት 17

ኤልያስን ቊራዎች መገቡት

1 በዚህ ጊዜ ከገለዓድ ነዋሪዎች አንዱ የሆነው ቴስብያዊው ኤልያስ አክዓብን፣ “የማመልከው ሕያውእግዚአብሔርን፣ በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር፣ በሚቀጥሉት ዓመታት ዝናብ ወይም ጠል አይኖርም” አለው።

2 ከዚያም እንዲህ የሚልየእግዚአብሔርቃል ለኤልያስ መጣለት፤

3 “ከዚህ ተነሥተህ ወደ ምሥራቅ ሂድ፤ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ባለው በኮራት ወንዝ ተሸሸግ።

4 ውሃ ከወንዙ ትጠጣለህ፤ ቊራዎችም እዚያው እንዲመግቡህ አዝዣለሁ።”

5 ስለዚህእግዚአብሔርያዘዘውን ፈጸመ፤ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ወዳለው ወደ ኮራት ወንዝ ሄዶ በዚያ ተቀመጠ።

6 ቊራዎችም ጧትና ማታ እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፤ ውሃም ከወንዙ ይጠጣ ነበር።

የሰራፕታዪቱ መበለት

7 በምድሪቱ ላይ ዝናብ ባለመጣሉ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወንዙ ደረቀ።

8 ከዚያም እንዲህ የሚልየእግዚአብሔርቃል ወደ ኤልያስ መጣ፤

9 “ተነሥና ሲዶና ውስጥ ወዳለችው ወደ ሰራፕታ ሄደህ ተቀመጥ፤ በዚያም አንዲት መበለት እንድትመግብህ አዝዣለሁ።”

10 ስለዚህ ተነሥቶ ወደ ሰራፕታ ሄደ። ወደ ከተማዪቱ በር እንደ ደረሰም፣ አንዲት መበለት ጭራሮ ስትለቃቅም አገኛት፤ ጠርቶም፣ “የምጠጣው ውሃ በዕቃ ታመጪልኛለሽን?” ሲል ለመናት።

11 ልታመጣለት ስትሄድ አሁንም ጠራትና፣ “እባክሽን፣ ቊራሽ እንጀራም ይዘሽልኝ ነይ” አላት።

12 እርሷም መልሳ፣ “አምላክህን ሕያውእግዚአብሔርን! በማድጋ ካለው ዕፍኝ ዱቄትና በማሰሮ ካለው ጥቂት ዘይት በቀር ምንም የለኝም። እነሆ፤ ለራሴና ለልጄ ምግብ አዘጋጅቼ በልተን እንድንሞት ጭራሮ ለቃቅሜ ወደ ቤት ልወስድ ነው” አለችው።

13 ኤልያስም መልሶ እንዲህ አላት፤ “አይዞሽ አትፍሪ፤ ወደ ቤት ገብተሽ እንዳልሽው አድርጊ፤ በመጀመሪያ ግን ከዚያችው ካለችሽ ትንሽ እንጎቻ ጋግረሽ አምጪልኝ፤ ከዚያም ለራስሽና ለልጅሽ ጋግሪ፤

14 የእስራኤል አምላክእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ ‘እግዚአብሔርለምድሪቱ ዝናብ እስከሚሰጥበት ዕለት ድረስ፤ ከማድጋው ዱቄት አይጠፋም፤ ከማሰሮውም ዘይት አያልቅም።’ ”

15 እርሷም ሄዳ ኤልያስ እንደ ነገራት አደረገች፤ በዚህ ሁኔታም ኤልያስ፣ መበለቲቱና ቤተ ሰቧ ብዙ ቀን ተመገቡ፤

16 በኤልያስ በተነገረውየእግዚአብሔርቃል መሠረት ከማድጋው ዱቄት አልጠፋም፤ ከማሰሮውም ዘይት አላለቀም ነበርና።

17 ከጥቂት ጊዜ በኋላም የባለቤቲቱ ልጅ ታመመ፤ ሕመሙ እየጠናበት ሄደ፣ በመጨረሻም ትንፋሹ ቀጥ አለ።

18 እርሷም ኤልያስን፤ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ እኔ ምን አደረግሁህ? እዚህ የመጣኸው ኀጢአቴን አስታውሰህ ልጄን ለመግደል ነውን?” አለችው።

19 ኤልያስም መልሶ፣ “ልጅሽን ስጪኝ” አላት፤ ልጁንም ከዕቅፏ ወስዶ እርሱ ወደሚኖርበት ሰገነት በማውጣት በዐልጋው ላይ አስተኛው።

20 ከዚያም፣ “አምላኬእግዚአብሔርሆይ፤ ልጇን እንዲሞት በማድረግ ተቀብላ በምታስተናግደኝ በዚህች መበለት ላይም መከራ ታመጣባታለህን?” ብሎ ወደእግዚአብሔርጮኸ።

21 በልጁም ላይ ሦስት ጊዜ ተዘርግቶ፣ “አምላኬእግዚአብሔርሆይ፤ የዚህ ልጅ ነፍስ ትመለስለት” ብሎ ወደእግዚአብሔርጮኸ።

22 እግዚአብሔርምየኤልያስን ጩኸት ሰማ፤ የልጁም ነፍስ ተመለሰችለት፤ እርሱም ዳነ።

23 ከዚያም ኤልያስ ልጁን አስነሥቶ ከሰገነቱ ወደ ምድር ቤት አወረደው፤ ለእናቱም ልጅሽ ይኸውልሽ፤ ድኖልሻል!” ብሎ ሰጣት።

24 ከዚያም ሴቲቱ ኤልያስን፣ “አሁን የእግዚአብሔር ሰው መሆንህን፣ ከአንደበትህም የወጣውየእግዚአብሔርቃል እውነት መሆኑን ዐወቅሁ” አለችው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *