ዳዊት የተቀዳጃቸው ድሎች
1 ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው፤ በቍጥጥሩም ሥር አዋላቸው፣ ሜቴግ አማ የተባለችውንም ከተማ ከፍልስጥኤማውያን ቍጥጥር ነጻ አደረጋት።
2 እንዲሁም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረገ፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፣ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር። ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት ተገዦች ሆኑ፤ ገበሩለትም።
3 ከዚህም በቀር ዳዊት በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ያለውን ግዛት መልሶ ለመያዝ በሄደ ጊዜ፣ የሱባን ንጉሥ የረአብን ልጅ አድርአዛርን ወጋው።
4 ዳዊትም አንድ ሺህ ሠረገሎች፣ ሰባት ሺህ ፈረሰኞችናሃያ ሺህ እግረኞች ማረከበት። ቊጥራቸው መቶ የሆነ የሠረገላ ፈረሶች ብቻ ሲቀሩ ሌሎቹን በሙሉ ቋንጃቸውን ቈረጠ።
5 የደማስቆዎቹ ሶርያውያን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ለመርዳት በመጡ ጊዜ ዳዊት ሃያ ሁለት ሺህ ሰው ገደለባቸው።
6 ከዚያም የደማስቆ ክፍል በሆነው የሶርያውያን ግዛት የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ። ሶርያውያን ተገዙለት፤ ገበሩለትም።እግዚአብሔርምዳዊት በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው።
7 ዳዊት የአድርአዛር ሹማምንት ያነገቧቸውን የወርቅ ጋሻዎች ወስዶ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣቸው።
8 ንጉሡ ዳዊት ቤጣህናቤሮታይ ከተባሉ ከአድርአዛር ከተሞችም እጅግ ብዙ ናስ አጋዘ።
9 የሐማት ንጉሥ ቶዑ ዳዊት መላውን የአድርአዛርን ሰራዊት ማሸነፉን በሰማ ጊዜ፣
10 ቶዑ ከአድርአዛር ጋር ሁል ጊዜ ይዋጋ ስለ ነበር፣ ሰላምታና በአድርአዛር ላይ ሰለተቀዳጀውም ድል የደስታ መግለጫ እንዲያቀርብለት፣ ልጁን ዮራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ እርሱም የብር፣ የወርቅና የናስ ዕቃ ይዞ መጣ።
11 ንጉሥ ዳዊትም፣ ቀድሞ ካስገበራቸው መንግሥታት ሁሉ በገባለት ብርና ወርቅ እንዳደረገው እነዚህንም ዕቃዎችለእግዚአብሔርቀደሳቸው።
12 የገበሩትም መንግሥታት ኤዶምናሞዓብ፣ አሞናውያን፣ ፍልስጥኤማውያንና አማሌቃውያን ነበሩ። እንዲሁም ከሱባ ንጉሥ ከረአብ ልጅ ከአድርአዛር የወሰደውን ምርኮለእግዚአብሔርቀደሰ።
13 ዳዊት የጨው ሸለቆ በተባለው ስፍራ ዐሥራ ስምንት ሺህ ኤዶማውያንንገድሎ ከተመለሰ በኋላ ስሙ ገነነ።
14 በመላው ኤዶም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ኤዶማውያን ሁሉ ለዳዊት ተገዙ፤እግዚአብሔርምዳዊት በሄደበት ስፍራ ሁሉ ድልን ሰጠው።
የዳዊት ሹማምት
15 ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፤ ለሕዝቡም ሁሉ ፍትሕና ርትዕ አሰፈነላቸው።
16 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የሰራዊቱ አለቃ ሲሆን፣ የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥም ታሪክ ጸሓፊ ነበረ።
17 እንዲሁም የአኪጦብ ልጅ ሳዶቅና የአብያታር ልጅ አቢሜሌክ ካህናት ሲሆኑ፣ ሠራያ ጸሓፊ ነበረ፤
18 የዮዳሔ ልጅ በናያስ የከሪታውያንና የፈሊታውያን አለቃ ሲሆን፣ የዳዊት ወንዶች ልጆች ደግሞ የቤተ መንግሥት አማካሪዎችነበሩ።