ዘዳግም 23

ከእግዚአብሔር ጉባኤ መለየት

1 ብልቱ የተቀጠቀጠ ወይም የተቈረጠ ማናቸውም ሰው ወደእግዚአብሔር(ያህዌ)ጉባኤ አይግባ።

2 ዲቃላም ይሁን የዲቃላው ዘር የሆነ ሁሉ፣ እስከ ዐሥር ትውልድ ድረስ እንኳን ቢሆን ወደእግዚአብሔር(ያህዌ)ጉባኤ አይግባ።

3 አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወይም ማናቸውም የእርሱ ዘር፣ እስከ ዐሥር ትውልድ እንኳ ቢሆን ወደእግዚአብሔር(ያህዌ)ጉባኤ አይግባ።

4 ምክንያቱም ከግብፅ ከወጣችሁ በኋላ በጒዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እህል ውሃ ይዘው አልተቀበሏችሁም፤ በመስጴጦምያ በምትገኘው በፐቶርይኖር የነበረውን የቢዖርን ልጅ በለዓምም አንተን እንዲረግም በገንዘብ ገዙት።

5 ይሁን እንጂ አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በለዓምን አልሰማውም፤ አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ስለሚወድህ ርግማኑን በረከት አደረገልህ።

6 በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ሰላምን ለእነርሱ አትመኝ።

7 ወንድምህ ስለ ሆነ ኤዶማዊውን አትጸየፈው፤ መጻተኛ ሆነህ በአገሩ ኖረሃልና ግብፃዊውን አትጥላው።

8 ለእነርሱ የተወለዱላቸው የሦስተኛው ትውልድ ልጆች ወደእግዚአብሔር(ያህዌ)ጉባኤ መግባት ይችላሉ።

የጦር ሰፈር ንጽሕና አጠባበቅ

9 ጠላትህን ለመውጋት ወጥተህ በሰፈርህ ጊዜ፤ ከማናቸውም ርኵሰት ራስህን ጠብቅ።

10 ከመካከላችሁ ሌሊት ዘር በማፍሰስ የረከሰ ሰው ቢኖር ከሰፈር ወጥቶ እዚያው ይቈይ።

11 እየመሸ ሲመጣ ግን ገላውን ይታጠብ፤ ፀሓይ ስትጠልቅም ወደ ሰፈሩ ይመለስ።

12 ለመጸዳጃ የሚሆንህን ቦታ ከሰፈር ውጭ አዘጋጅ።

13 ከትጥቅህም ጋር መቈፈሪያ ያዝ፤ በምትጸዳዳበት ጊዜ ዐፈር ቈፍረህ በዐይነ ምድርህ ላይ መልስበት።

14 አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ሊጠብቅህ ጠላቶችህንም በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥህ በሰፈር ውስጥ ስለሚዘዋወር፣ በመካከልህ አንዳች ነውር አይቶ ከአንተ እንዳይመለስ፣ ሰፈርህ የተቀደሰ ይሁን።

ልዩ ልዩ ሕጎች

15 አንድ ባሪያ ከአሳዳሪው ኰብልሎ ወደ አንተ ቢመጣ፣ ለአሳዳሪው አሳልፈህ አትስጠው።

16 ደስ በሚያሰኘው ቦታና ራሱ በመረጠው ከተማ በመካከልህ ይኑር፤ አንተም አታስጨንቀው።

17 ወንድ ወይም ሴት እስራኤላዊ የቤተ ጣዖት አመንዝራ አይሁን።

18 ለዝሙት አዳሪ ሴት ወይም ለወንደቃየተከፈለውን ዋጋ ለማናቸውም ስእለት አድርገህ ለመስጠት ወደ አምላክህ ወደእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ቤት አታምጣ፤ አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ሁለቱንም ይጸየፋቸዋልና።

19 የገንዘብ፣ የእህል ወይም የማንኛውንም ነገር ወለድ ለማግኘት ለወንድምህ በወለድ አታበድር።

20 ባዕድ ለሆነ ሰው ወለድ ማበደር ትችላለህ፤ ነገር ግን ልትወርሳት በምትገባባት ምድር እጅህ በሚነካው በማናቸውም ነገር አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)እንዲባርክህ ለእስራኤላዊ ወንድምህ በወለድ አታበድረው።

21 ለአምላክህለእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)ስእለት ከተሳልህ፣ አምላክህእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)አጥብቆ ከአንተ ይሻዋልና፣ ኀጢአት እንዳይሆንብህ ለመክፈል አትዘግይ።

22 ሳትሳል ብትቀር ግን በደለኛ አትሆንም።

23 በአንደበትህ የተናገርኸውን ሁሉ ለመፈጸም ጠንቃቃ ሁን፤ ለአምላክህለእግዚአብሔር(ኤሎሂም ያህዌ)በገዛ አንደበትህ ፈቅደህ ስእለት ተስለሃልና።

24 ወደ ባልንጀራህ የወይን ተክል ቦታ በምትገባበት ጊዜ፣ ያሰኘህን ያህል መብላት ትችላለህ፤ ነገር ግን አንዳችም በዕቃህ አትያዝ።

25 ወደ ባልንጀራህ ዕርሻ በምትገባበት ጊዜ፣ እሸት መቅጠፍ ትችላለህ፤ በሰብሉ ላይ ግን ማጭድ አታሳርፍበት።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *