ዘሌዋውያን 2

የእህል ቊርባን

1 “ ‘ማንኛውም ሰው የእህል ቊርባንለእግዚአብሔር(ያህዌ)በሚያቀርብበት ጊዜ፣ ዱቄቱ የላመ ይሁን፤ ዘይት ያፍስበት፤ ዕጣንም ይጨምርበት፤

2 ወደ ካህናቱም ወደ አሮን ልጆች ያምጣው። ካህኑ ከላመው ዱቄትና ከዘይቱ አንድ እፍኝ ሙሉ ያንሣለት፤ ዕጣኑንም ሁሉ ይውሰደው፤ ይህንም በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውምእግዚአብሔርን(ያህዌ)ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት አድርጎ ለመታሰቢያ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው።

3 የተረፈውም የእህሉ ቊርባን ለአሮንና ለልጆቹ ይሰጥ፤ ይህምለእግዚአብሔር(ያህዌ)በእሳት ከሚቀርበው ቊርባን እጅግ የተቀደሰ ክፍል ነው።

4 “ ‘በማብሰያ ምድጃ የተጋገረ የእህል ቊርባን በምታቀርብበት ጊዜ፣ ከላመ ዱቄት ተዘጋጅቶ እርሾ ሳይገባበት በዘይት ተለውሶ የተጋገረ ኅብስት ይሁን፤ አለዚያምያለ እርሾ በስሱ ተጋግሮ ዘይት የተቀባ ቂጣ ይሁን።

5 የእህል ቊርባንህ በምጣድ የሚጋገር ከሆነ፣ እርሾ ሳይገባበት በዘይት ከተለወሰ ከላመ ዱቄት ይዘጋጅ።

6 ቈራርሰህ ዘይት አፍስበት፤ ይህ የእህል ቊርባን ነው።

7 የእህል ቊርባንህ በመጥበሻ የሚበስል ከሆነ፣ ከላመ ዱቄትና ከዘይት ይዘጋጅ።

8 በዚህ ሁኔታ የተዘጋጀውን የእህል ቊርባን ወደእግዚአብሔር(ያህዌ)አምጥተህ ለካህኑ አስረክብ፤ ካህኑም ወደ መሠዊያው ይወስደዋል፤

9 ከእህሉም ቊርባን ላይ ለመታሰቢያ የሚሆነውን ክፍል ያነሣና በእሳት የሚቃጠል፣ ሽታውምእግዚአብሔርን(ያህዌ)ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።

10 የተረፈውም ቊርባን ለአሮንና ለልጆቹ ይሰጥ፤ ይህምለእግዚአብሔር(ያህዌ)በእሳት ከሚቀርበው ቊርባን እጅግ የተቀደሰ ክፍል ነው።

11 “ ‘ለእግዚአብሔር(ያህዌ)በእሳት በምታቀርቡት ቊርባን ውስጥ እርሾ ወይም ማር ጨምራችሁ ማቃጠል ስለማይገባችሁ፣ በምታቀርቡት በማንኛውም የእህል ቊርባን እርሾ አይኑርበት።

12 እነዚህን የበኵራት ቊርባን አድርጋችሁለእግዚአብሔር(ያህዌ)ማቅረብ ትችላላችሁ፤ ነገር ግን ሽታው ደስ የሚያሰኝ ቊርባን ሆነው በመሠዊያ ላይ ለመቃጠል አይቀርቡም።

13 የምታቀርበውን የእህል ቊርባን ሁሉ በጨው ቀምመው፤ የአምላክህ(ኤሎሂም)የቃል ኪዳን ጨው ከእህል ቊርባንህ አይታጣ፤ በቊርባንህም ላይ ጨው ጨምርበት።

14 “ ‘የእህል በኵራት ቊርባንለእግዚአብሔር(ያህዌ)በምታመጣበት ጊዜ፣ የተፈተገና በእሳት የተጠበሰ እሸት አቅርብ።

15 ዘይት ጨምርበት፤ ዕጣንም በላዩ አስቀምጥ፤ ይህ የእህል ቊርባን ነው።

16 ካህኑም ከተፈተገው እህልና ከዘይቱ ወስዶ፣ ከዕጣኑ ሁሉ ጋርለእግዚአብሔር(ያህዌ)በእሳት የሚቀርብ መታሰቢያ አድርጎ ያቃጥል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *