ሶፎንያስ 1

1 በይሁዳ ንጉሥ በአሞጽ ልጅ በኢዮስያስ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ፣ ወደ አማርያ ልጅ፣ ወደ ጎዶልያስ ልጅ፣ ወደ ኵሲ ልጅ ወደ ሶፎንያስ የመጣየእግዚአብሔርቃል ይህ ነው፤

ስለሚመጣው ጥፋት የተሰጠ ማስጠንቀቂያ

2 “ማንኛውንም ነገር፣

ከምድር ገጽ አጠፋለሁ”

ይላልእግዚአብሔር።

3 “ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤

የሰማይን ወፎች፣

የባሕርንም ዓሦች አጠፋለሁ፤

ሰውን ከምድር ገጽ በማስወግድበት ጊዜ፣

ክፉዎች የፍርስራሽክምር ይሆናሉ”

ይላልእግዚአብሔር።

በይሁዳ ላይ የተነገረ ጥፋት

4 “እጄን በይሁዳ፣

በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ አነሣለሁ፤

የበኣልን ትሩፍ፣

የጣዖታቱንና የአመንዝራ ካህናቱን ስም ሁሉ ከዚህ ስፍራ አጠፋለሁ፤

5 የሰማይን ሰራዊት ለማምለክ፣

በሰገነት ላይ ወጥተው የሚሰግዱትን፣

ለእግዚአብሔርእየሰገዱ፣ በስሙም እየማሉ፣

በሚልኮምምደግሞ የሚምሉትን፣

6 እግዚአብሔርንከመከተል ወደ ኋላ የሚመለሱትን፣

እግዚአብሔርን የማይፈልጉትን፣ እንዲረዳቸውም የማይጠይቁትን አጠፋለሁ።

7 በልዑልእግዚአብሔርፊት ዝም በሉ፤

የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና።

እግዚአብሔርመሥዋዕት አዘጋጅቶአል፤

የጠራቸውንም ቀድሶአል።

8 በእግዚአብሔርየመሥዋዕት ቀን፣

መሳፍንቱንና የንጉሡን ልጆች፣

እንግዳ ልብስ የሚለብሱትን ሁሉ እቀጣለሁ።

9 በዚያን ቀን፣

በመድረኩ ላይ የሚዘሉትን ሁሉ፣

የአማልክቶቻቸውን ቤት፣

በዐመፅና በማጭበርበር የሚሞሉትን እቀጣለሁ።

10 እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤

“በዚያ ቀን ‘ከዓሣ በር’ ጩኸት

በሁለተኛው አደባባይ ዋይታ፣

ከኰረብቶችም ታላቅ ሽብር ይሰማል።

11 እናንት በመክቴሽገበያ የምትኖሩ ዋይ በሉ፤

ነጋዴዎቻችሁ ሁሉ ይደመሰሳሉ፤

በብር የሚነግዱትም ሁሉ ይሞታሉ።

12 በዚያ ዘመን ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤

ተንደላቀው የሚኖሩትን፣

በዝቃጩ ላይ እንደ ቀረ የወይን ጠጅ የሆኑትን፣

‘ክፉም ይሁን መልካም፣

እግዚአብሔርምንም አያደርግም’ የሚሉትን ቸልተኞች እቀጣለሁ።

13 ሀብታቸው ይዘረፋል፤

ቤታቸው ይፈራርሳል፤

ቤቶች ይሠራሉ፤

ነገር ግን አይኖሩባቸውም፤

ወይን ይተክላሉ፤

ጠጁን ግን አይጠጡም።

ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን

14 “ታላቁየእግዚአብሔርቀን ቅርብ ነው፤

ቅርብ ነው ፈጥኖም ይመጣል፤

በእግዚአብሔርቀን የሚሰማው ልቅሶ መራራ ነው፤

በዚያ ጦረኛውም ምርር ብሎ ይጮኻል፤

15 ያ ቀን የመዓት ቀን፣

የመከራና የጭንቀት ቀን፣

የሁከትና የጥፋት ቀን፣

የጨለማና የጭጋግ ቀን፣

የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ይሆናል፤

16 ያ ቀን በተመሸጉ ከተሞችና፣

በረጃጅም ግንቦች ላይ፣

የመለከት ድምፅና የጦርነት ጩኸት የሚሰማበት ቀን ይሆናል።

17 እንደ ዕውር እንዲራመዱ፣

በሰዎች ላይ ጭንቀት አመጣባቸዋለሁ፤

በእግዚአብሔርላይ ኀጢአትን ሠርተዋልና።

ደማቸው እንደ ትቢያ፣

ሥጋቸውም እንደ ጒድፍ ይጣላል።

18 በእግዚአብሔርየቊጣ ቀን፣

ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው፣

ሊያድናቸው አይችልም፤

መላዪቱ ምድር፣

በቅናቱ ትበላለች፤

በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ፣

ድንገተኛ ፍጻሜ ያመጣባቸዋልና።”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *