ዮናስ 1

ዮናስ ከእግዚአብሔር ኰበለለ

1 የእግዚአብሔርቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ፤

2 “ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሄደህ፣ በእርሷ ላይ ስበክ፤ ክፋቷ በእኔ ፊት ወጥቶአልና።”

3 ዮናስ ግንከእግዚአብሔርፊት ኰበለለ፤ ወደ ተርሴስም ለመሄድ ተነሣ። ወደ ኢዮጴ ወረደ፣ ወደዚያው ወደ ተርሴስ የምትሄድ መርከብም አገኘ። የጒዞውንም ዋጋ ከከፈለ በኋላ፣ከእግዚአብሔርፊት ወደ ተርሴስ ለመኰብለል በመርከቢቱ ተሳፈረ።

4 እግዚአብሔርምበባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን ላከ፤ ከባድ ማዕበልም ተነሥቶ መርከቢቱን አንገላታት፤ ልትሰበርም ተቃረበች።

5 መርከበኞቹ ሁሉ ፈሩ፤ እያንዳንዱም ሰው ወደ አምላኩ ጮኸ፤ የመርከቢቱም ክብደት እንዲቀል፣ በውስጧ የነበረውን ዕቃ ወደ ባሕሩ ጣሉት።

ዮናስ ግን ወደ መርከቢቱ ታችኛ ክፍል ወርዶ ተኛ፤ በከባድም እንቅልፍ ላይ ነበር።

6 የመርከቢቱም አዛዥ ወደ እርሱ ሄዶ፣ “እንዴት ትተኛለህ? ተነሥና አምላክህን ጥራ እንጂ፤ ምናልባትም ያስበንና ከጥፋት ያድነን ይሆናል” አለው።

7 ከዚያም መርከበኞቹ እርስ በርሳቸው፣ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንደ መጣብን ለማወቅ፣ ኑ፣ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ።

8 ከዚያም፣ “ይህ ሁሉ አስጨናቂ ነገር በማን ምክንያት እንደ መጣብን ንገረን፤ ሥራህ ምንድን ነው? ከወዴትስ መጣህ? አገርህስ የት ነው? ከየትኛውስ ሕዝብ ነህ?” አሉት።

9 እርሱም፣ “እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ የብስንና ባሕርን የፈጠረውን፣ የሰማይን አምላክእግዚአብሔርንአመልካለሁ” አለ።

10 እርሱ አስቀድሞ ነግሮአቸው ስለ ነበር፣ከእግዚአብሔርእንደ ኰበለለ ዐወቁ፣ ስለዚህም በሁኔታው በመደንገጥ፣ “ይህ ያደረግኸው ምንድን ነው?” አሉት።

11 የባሕሩም ማዕበል እጅግ እየበረታ ስለሄደ፣ “ባሕሩ ጸጥ እንዲልልን በአንተ ላይ ምን ብናደርግ ይሻላል?” አሉት።

12 እርሱም፣ “ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንደ መጣባችሁ ዐውቃለሁ፤ አንሥታችሁ ወደ ባሕሩ ጣሉኝ፤ ባሕሩም ጸጥ ይላል” አላቸው።

13 ሰዎቹ ግን ባላቸው ኀይል እየቀዘፉ ወደ የብስ ለመጠጋት ሞከሩ፤ ይሁን እንጂ አልቻሉም፤ ባሕሩ የባሰ ይናወጥ ነበርና።

14 “እግዚአብሔርሆይ፤ እባክህ በዚህ ሰው ነፍስ ምክንያት አታጥፋን፤ የዚህ ንጹሕ ሰው ደምም በእኛ ላይ አይሁን፤እግዚአብሔርሆይ፤ አንተ የወደድኸውን አድርገሃልና” ብለው ወደእግዚአብሔርጮኹ።

15 ከዚያም ዮናስን ይዘው ወደ ባሕሩ ጣሉት፤ ባሕሩም ከመናወጥ ጸጥ አለ።

16 ሰዎቹምእግዚአብሔርንእጅግ ፈሩ፤ለእግዚአብሔርመሥዋዕትም አቀረቡ፤ ለእርሱም ስእለትን ተሳሉ።

17 እግዚአብሔርግን ዮናስን የሚውጥ ትልቅ ዓሣ አዘጋጀ፤ ዮናስም በዓሣው ሆድ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አደረ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *