አሞጽ 7

አንበጣ፣ እሳትና ቱንቢ

1 ጌታእግዚአብሔርይህን አሳየኝ፤ የንጉሡ የመከር እህል ከተሰበሰበ በኋላ ገቦው መብቀል በጀመረ ጊዜ፣ እርሱ የአንበጣ መንጋ እንዲፈለፈል አደረገ።

2 አንበጦች የምድሩን ሣር ግጠው ከጨረሱት በኋላ፣ “ጌታእግዚአብሔርሆይ፤ ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፤ ያዕቆብ ይህን እንዴት ሊቋቋመው ይችላል? ታናሽ ነው እኮ!” አልሁ።

3 እግዚአብሔርምስለዚህ ነገር ተጸጸተ፤እግዚአብሔርምይህ አይፈጸምም አለ።

4 ጌታእግዚአብሔርይህንም አሳየኝ፤ ጌታእግዚአብሔርበእሳት ሊፈርድ ተዘጋጀ፤ እሳቱም ታላቁን ጥልቅ አደረቀ፤ ምድሪቱንም በላ።

5 ከዚያም በኋላ፣ “ጌታእግዚአብሔርሆይ፤ እንድትተወው እለምንሃለሁ፤ ያዕቆብ ይህን እንዴት ሊቋቋመው ይችላል? ታናሽ ነው እኮ! አልሁ።

6 እግዚአብሔርስለዚህ ነገር ተጸጸተ፤ ጌታእግዚአብሔር፣ “ይህም ደግሞ አይፈጸምም” አለ።

7 ይህንም ደግሞ አሳየኝ፤ ጌታ በእጁ ቱምቢ ይዞ በቱምቢ በተሠራ ቅጥር አጠገብ ቆሞ ነበር።

8 እግዚአብሔር፣ “አሞጽ፣ የምታየው ምንድ ነው?” አለኝ።

እኔም፣ “ቱምቢ” አልሁ።

ጌታም እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል ቱምቢ እዘረጋለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ አልምራቸውም።

9 “የይስሐቅ ማምለኪያ ኮረብታዎች ባድማ ይሆናሉ፤

የእስራኤል መቅደሶች ይፈርሳሉ፤

በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሰይፌ እነሣለሁ።”

አሞጽና አሜስያስ

10 ከዚህ በኋላ የቤቴል ካህን አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፤ “አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል በአንተ ላይ እያሤረ ነው፤ ምድሪቱም ቃሉን ሁሉ ልትሸከም አትችልም፤

11 አሞጽ እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበርና፤

“ ‘ኢዮርብዓም በሰይፍ ይሞታል፤

እስራኤልም በእርግጥ ከትውልድ አገሩ

ተማርኮ ይሄዳል።”

12 አሜስያስም፣ አሞጽን እንዲህ አለው፤ “አንተ ባለ ራእይ ከዚህ ሂድ! ከይሁዳ ምድር ሽሽ፤ እዚያም እንጀራህን ብላ፤ በዚያም ትንቢት ተናገር።

13 ከእንግዲህ ወዲያ ግን በቤቴል ትንቢት አትናገር፤ የንጉሡ መቅደስ፣ የመንግሥቱም መኖሪያ ነውና።”

14 አሞጽም ለአሜስያስ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ እረኛና የባሉጥ ፍሬ ለቃሚ ነኝ እንጂ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም፤

15 እግዚአብሔርግን የበግ መንጋ ከምጠብቅበት ቦታ ወስዶ፣ ‘ሂድና ለሕዝቤ ለእስራኤል ትንቢት ተናገር’ አለኝ፤

16 እንግዲህየእግዚአብሔርንቃል ስማ።

አንተ፣ “ ‘በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፤

በይስሐቅም ቤት ላይ አትስበክ’ ትላለህ።

17 “ስለዚህእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤”

‘ሚስትህ በከተማዪቱ ውስጥ ጋለሞታ ትሆናለች፤

ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፤

ምድርህም እየተለካ ይከፋፈላል፤

አንተ ራስህ በረከሰምድር ትሞታለህ፤

እስራኤልም ከትውልድ አገሩ፣

ተማርኮ ይሄዳል።’ ”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *