አሞጽ 6

ተዘልላ ላለችው እስራኤል የተሰጠ ማስጠንቀቂያ

1 በጽዮን ተዘልላችሁ የምትቀመጡ፣

በሰማርያ ተራራ ያለ ሥጋት የምትኖሩ፣

የእስራኤልም ሕዝብ ለርዳታ ወደ እናንተ የሚመጡባችሁ፣

እናንት የአሕዛብ አለቆች ሆይ፤ ወዮላችሁ!

2 ወደ ካልኔ ሂዱ፤ እርሱንም ተመልከቱ፤

ከዚያም ወደ ታላቂቱ ሐማት ሂዱ፤

ወደ ፍልስጥኤም ከተማ ወደ ጌትም ውረዱ፤

እነዚህ ከሁለቱ መንግሥታቶቻችሁ ይሻላሉን?

የምድራቸውስ ስፋት ከእናንተ ይበልጣልን?

3 ክፉውን ቀን ለምታርቁ፣

የግፍንም ወንበር ለምታቀርቡ ወዮላችሁ!

4 በዝሆን ጥርስ ባጌጠ ዐልጋ ላይ ለምትተኙ፤

በድንክ ዐልጋችሁ ላይ ለምትዝናኑ፣

ከበጎች መንጋ ጠቦትን፣

ከጋጣም ጥጃን ለምትበሉ፤

5 ባልተቃኘ በገና ለምትዘፍኑ፣

በሙዚቃ መሣሪያ ለመጫወት ለምትሹ፣

6 በፋጋ የወይን ጠጅ ለምትጠጡ፣

ምርጥ ሽቱም ለምትቀቡ፣

ስለ ዮሴፍ መከራ ግን ለማታዝኑ ወዮላችሁ!

7 ስለዚህ እናንተ በመጀመሪያ በምርኮ ከሚወሰዱት መካከል ናቸሁ፤

መፈንጠዛችሁና መዝናናታችሁም ያበቃል።

እግዚአብሔር የእስራኤልን ትዕቢት ይጸየፋል

8 ጌታእግዚአብሔር“የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፤

ምሽጎቹንም ጠልቻለሁ፤

ከተማዪቱንና በውስጥዋ ያለውን ሁሉ፣

አሳልፌ እሰጣለሁ” ሲል በራሱ ምሎአል፤

ይላል የሰራዊት አምላክእግዚአብሔር።

9 በአንድ ቤት ውስጥ ዐሥር ሰዎች ቢቀሩ እነርሱም ይሞታሉ።

10 በድኖቹንም ከቤት አውጥቶ ማቃጠል ያለበት አንድ ዘመድ መጥቶ ተደብቆ ያለውን ሰው፣ “ከአንተ ጋር የቀረ ሌላ ሰው አለን?” ሲለው፣ እርሱም “የለም” ይለዋል፤ ከዚያም በኋላ፣ “ዝም በል፤የእግዚአብሔርንስም መጥራት አይገባንም” ይለዋል።

11 እነሆ፤እግዚአብሔርትእዛዝ ሰጥቶአልና፤

ታላላቅ ቤቶችን ያወድማቸዋል፤

ትንንሾቹንም ያደቅቃቸዋል።

12 ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይሮጣሉን?

ሰውስ እዚያ ላይ በበሬ ያርሳልን?

እናንተ ግን ፍትሕን ወደ መርዝነት፣

የጽድቅንም ፍሬ ወደ መራራነት ለወጣችሁ።

13 እናንተ ሎዶባርንበማሸነፋችሁ ደስ ያላችሁ፣

“ቃርናይምንበራሳችን ብርታት ይዘናል” የምትሉ፣

14 ሁሉን የሚገዛ አምላክእግዚአብሔርእንዲህ ይላልና፣

“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፤ እነሆ፤ እኔ ከሐማት መግቢያእስከ ዓረባ ሸለቆ ድረስ፣

የሚያስጨንቃችሁን ሕዝብ፣ በእናንተ

ላይ አስነሣለሁ።”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *