ኤርምያስ 49

ስለ አሞን የተነገረ መልእክት

1 ስለ አሞናውያን፤

እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤

“እስራኤል ወንዶች ልጆች አልወለደምን?

ወራሾችስ የሉትምን?

ታዲያ፣ ሚልኮምሸጋድን ለምን ወረሰ?

የእርሱ ሰዎች ለምን በከተሞቿ ይኖራሉ?

2 ስለዚህ በአሞናውያን ከተማ በረባት ላይ፣

የጦርነት ውካታ ድምፅ፣

የሚሰማበት ጊዜ ይመጣል፤”

ይላልእግዚአብሔር፤

“እርሷም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤

በዙሪያዋ ያሉት መንደሮችም ይቃጠላሉ፤

እስራኤልም ከአገሯ ያስወጧትን፣

ከአገሯ ታስወጣለች፤”

ይላልእግዚአብሔር፤

3 ሐሴቦን ሆይ፤ ጋይ ጠፍታለችና ዋይ በይ፤

የራባት ሴቶች ልጆች ሆይ ጩኹ፤

ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ፤

ሚልኮም ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋር፣

ተማርኮ ይወሰዳልና፣

በቅጥር ውስጥ ወዲያ ወዲህ ተሯሯጡ።

4 አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፣

በሸለቆችሽ ለምን ትመኪያለሽ?

ለምንስ በፍሬያማ ሸለቆሽ ትኵራሪያለሽ?

በብልጽግናሽ ተማምነሽ፣

‘ማን ሊነካኝ ይችላል?’ ትያለሽ።

5 በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ፣

ሽብር አመጣብሻለሁ፤”

ይላል የሰራዊት ጌታእግዚአብሔር፤

“እያንዳንዳችሁ ትሰደዳላችሁ፤

በሽሽት ላይ ያሉትንም የሚሰበስብ አይገኝም።

6 “ከዚያ በኋላ ግን፣ የአሞናውያንን ምርኮ እመልሳለሁ፣”

ይላልእግዚአብሔር።

ስለ ኤዶም የተነገረ መልእክት

7 ስለ ኤዶም፤

የሰራዊት ጌታእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤

“ጥበብ ከቴማን ጠፍቶአልን?

ምክር ከአስተዋዮች ርቆአልን?

ጥበባቸውስ ተሟጧልን?

8 ዔሳውን በምቀጣ ጊዜ፣

ጥፋት ስለማመጣበት፣

እናንተ በድዳን የምትኖሩ ሆይ፤

ወደ ኋላ ተመልሳችሁ ሽሹ፤ ጥልቅ ጒድጓድ ውስጥ ተደበቁ።

9 ወይን ለቃሚዎች ወዳንተ ቢመጡ፣

ጥቂት ወይን አያስቀሩምን?

ሌቦችስ በሌሊት ቢመጡ፣

የሚሰርቁት የሚፈልጉትን ብቻ አይደለምን?

10 እኔ ግን ዔሳውን አራቍተዋለሁ፤

መደበቅም እንዳይችል፣

መሸሸጊያ ስፍራዎቹን እገልጣለሁ፤

ልጆቹ፣ ዘመዶቹና ጎረቤቶቹ ይጠፋሉ፤

እርሱም ራሱ አይኖርም።

11 ወላጆች የሌላቸውን ልጆችህን ተዋቸው፤ እኔ ለሕይወታቸው እጠነቀቃለሁ፤ መበለቶቻችሁም በእኔ ይታመኑ።”

12 እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ “ከጽዋው መጠጣት የማይገባቸው ሊጠጡ ግድ ከሆነ፣ አንተ እንዴት ሳትቀጣ ትቀራለህ? መቀጣትህ አይቀርም፤ መጠጣት ይገባሃል።

13 ባሶራ ፈራርሳ የድንጋጤ፣ የመዘባበቻና የርግማን ምልክት እንደምትሆን በራሴ ምያለሁ” ይላልእግዚአብሔር፤ “ከተሞቿም ሁሉ ለዘላለም ባድማ ይሆናሉ።”

14 ከእግዚአብሔርዘንድ መልእክት ሰምቻለሁ፤

“እርሷን ለመውጋት ተሰብሰቡ፤

ለጦርነትም ውጡ”

የሚል መልእክተኛ ወደ ሕዝቦች ተልኮአል።

15 “እነሆ፤ በሕዝቦች መካከል ታናሽ፣

በሰዎችም ዘንድ የተናቅህ አደርግሃለሁ።

16 አንተ በዐለት ንቃቃት ውስጥ የምትኖር፣

የተራራውንም ከፍታ የያዝህ ሆይ፤

የምትነዛው ሽብር፣

የልብህም ኵራት አታሎሃል፤

መኖሪያህን እንደ ንስር በከፍታ ቦታ ብትሠራም፣

ከዚያ ወደ ታች እጥልሃለሁ፤”

ይላልእግዚአብሔር።

17 “ኤዶም የድንጋጤ ምልክት ትሆናለች፤

ከቍስሎቿም ሁሉ የተነሣ፣

በዚያ የሚያልፍ ሁሉ በመደነቅ ያላግጥባታል።”

18 በዙሪያቸው ካሉት ከተሞች ጋር፣

ሰዶምና ገሞራ እንደ ተገለበጡ፣”

ይላልእግዚአብሔር፤

እንዲሁ ማንም በዚያ አይኖርም፤

አንድም ሰው አይቀመጥባትም።

19 “አንበሳ ከዮርዳኖስ ደኖች፣

ወደ ግጦሽ ሜዳ ብቅ እንደሚል፣

እኔም በኤዶም ላይ ድንገት እወጣለሁ፤ ከምድሩም አባርረዋለሁ።

የመረጥሁትን በእርሱ ላይ እሾማለሁ፤

እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ማንስ ሊገዳደረኝ ይችላል?

የትኛውስ እረኛ ሊቋቋመኝ ይችላል?

20 ስለዚህእግዚአብሔርበኤዶም ላይ ያለውን ዕቅድ፣

በቴማን በሚኖሩትም ላይ ያሰበውን አሳብ ስሙ፤

ታናናሹ መንጋ ተጐትቶ ይወሰዳል፤

በእነርሱም ምክንያት መሰማሪያቸውን ፈጽሞ ያጠፋል።

21 በውድቀታቸው ድምፅ ምድር ትናወጣለች፤

ጩኸታቸውም እስከ ቀይ ባሕርያስተጋባል።

22 እነሆ፤ እንደ ንስር ተወርውሮ ይወርድባታል፤

ክንፎቹንም በባሶራ ላይ ይዘረጋል፤

በዚያን ቀን የኤዶም ጦረኞች ልብ፣

በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ልብ ይሆናል።

ስለ ደማስቆ የተነገረ መልእክት

23 ስለ ደማስቆ፤

“ክፉ ወሬ ሰምተዋልና፣

ሐማትና አርፋድ ደንግጠዋል፤

እንደተናወጠ ባሕርም ታውከዋል፤

ልባቸውም ቀልጦአል።

24 ደማስቆ ተዳከመች፤

ትሸሽም ዘንድ ወደ ኋላ ተመለሰች፤

ብርክ ያዛት፣

ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣

ጭንቅና መከራ ዋጣት።

25 ደስ የምሰኝባት፣

የታወቀችው ከተማ እንዴት ተተወች?

26 በርግጥ ወንዶች ወጣቶቿ በየአደባባዩ ይረግፋሉ፤

በዚያ ቀን ወታደሮቿ ሁሉ ይወድቃሉ፤”

ይላል የሰራዊት ጌታእግዚአብሔር፤

27 “በደማስቆ ቅጥር ላይ እሳት እለኵሳለሁ፤

የወልደ አዴርንም ዐምባ ይበላል።”

ስለ ቄዳርና ስለ ሐጾር የተነገረ መልእክት

28 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ ወጋቸው ስለ ቄዳርና ስለ ሐጾር መንግሥታት የተነገረ፤እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤

“ተነሡ፣ ቄዳርን ውጉ፤

የምሥራቅንም ሕዝብ ደምስሱ።

29 ድንኳኖቻቸውና መንጎቻቸው ይወሰዳሉ፤

መጠለያቸውና ግመሎቻቸው ሳይቀሩ፣

ከነዕቃዎቸው ይነጠቃሉ፤

ሰዎች፣ ‘ሽብር በሽብር ላይ መጥቶባቸዋል፤’

እያሉ ይጮኹባቸዋል።

30 በሐጾር የምትኖሩ ሆይ፣

በጥድፊያ ሽሹ በጥልቅ ጒድጓድ ተሸሸጉ፤”

ይላልእግዚአብሔር፤

የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በእናንተ ላይ መክሮአልና፣

ወረራም ዶልቶባችኋል።

31 “ተነሡ፣ ተዘልሎ የተቀመጠውን፣

በራሱ ተማምኖ የሚኖረውን ሕዝብ ውጉ፤”

ይላልእግዚአብሔር፤

“መዝጊያና መቀርቀሪያ በሌለው፤

ለብቻው በሚኖረው ሕዝብ ላይ ዝመቱ።

32 ግመሎቻቸው ይዘረፋሉ፤

ከብቶቻቸውንም አንጋግተው ይነዱባቸዋል፤

ጠጒሩን የሚቀነብበውን ወገን

እበትናለሁ ከየአቅጣጫው መዓት

ይላልእግዚአብሔር፤

33 “ሐጾር የቀበሮዎች መፈንጫ፣

ለዘላለም ባድማ ትሆናለች፤

ማንም በዚያ አይኖርም፤

የሚቀመጥባትም አይገኝም።”

ስለ ኤላም የተነገረ መልእክት

34 በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ ላይ ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣውየእግዚአብሔርቃል ይህ ነው፤

35 የሰራዊት ጌታእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤

“እነሆ፤ የኀያልነቷን መሠረት፣

የኤላምን ቀስት እሰብራለሁ።

36 ከአራቱ የሰማይ ማእዘናት፣

በኤላም ላይ አራቱን ነፋሳት አመጣለሁ፤

ወደ አራቱም ነፋሳት እበትናቸዋለሁ፤

ከኤላም የሚማረኩት የማይደርሱበት፣

አገር አይገኝም።

37 ነፍሳቸውን በሚሹ ጠላቶቻቸው ፊት፣

ኤላምን አርበደብዳለሁ፤

በላያቸው ላይ መዓትን፣

ይኸውም ቍጣዬን አመጣባቸዋለሁ፤”

ይላልእግዚአብሔር፤

“ፈጽሜ አስካጠፋቸውም ድረስ፣

በሰይፍ አሳድዳቸዋለሁ።

38 ዙፋኔን በኤላም እዘረጋለሁ፤

ነገሥታቷንና መኳንንቷን አጠፋለሁ፤”

ይላልእግዚአብሔር፤

39 “ነገር ግን የኋላ ኋላ፣

የኤላምን ምርኮ እመልሳለሁ፤”

ይላልእግዚአብሔር።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *