ለባሮክ የተነገረ መልእክት
1 በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት በአራተኛው ዓመት፣ ኤርምያስ በቃል የነገረውን ባሮክ በብራና ላይ ከጻፈ በኋላ፣ ነቢዩ ኤርምያስ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ የተናገረው ይህ ነው፤
2 “ባሮክ ሆይ፤ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታእግዚአብሔርእንዲህ ይልሃል፤
3 አንተ፣ ‘እግዚአብሔርበሕመሜ ላይ ሐዘን ጨምሮብኛልና ወዮልኝ፤ ከልቅሶዬ ብዛት የተነሣ ደክሜያለሁ፤ ዕረፍትም የለኝም’ ብለሃል።”
4 እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ “እንዲህ በለው፤ ‘እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ በምድር ሁሉ የገነባሁትን አፈርሳለሁ፤ የተከልሁትን እነቅላለሁ።
5 ታዲያ፣ ለራስህ ታላቅ ነገር ትሻለህን? በሰው ልጆች ሁሉ ላይ ጥፋት አመጣለሁና አትፈልገው፤ ይላልእግዚአብሔር፤ ነገር ግን በሄድህበት ሁሉ ሕይወትህ እንዲተርፍልህ አደርጋለሁ።’ ”