1 የቃሬያን ልጅ ዮሐናንና የሆሻያን ልጅ ያእዛንያንጨምሮ፣ የጦር መኰንኖች ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡ ሁሉ ከትንሹ እስከ ትልቁ ቀርበው፣
2 ነቢዩ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፤ “ቀድሞ ብዙዎች ነበርን አሁን እንደምታየን ግን የቀረነው ጥቂት ነን፤ ስለዚህ እባክህ ልመናችንን ስማ፤ ለዚህ ለተረፈው ሕዝብ ሁሉ ወደ አምላክህ ወደእግዚአብሔርጸልይ።
3 አምላክህእግዚአብሔርወዴት መሄድ እንዳለብንና ምን ማድረግ እንደሚገባን እንዲነግረን ጸልይልን።”
4 ነቢዩ ኤርምያስም፣ “ሰምቻችኋለሁ፤ እንዳላችሁት ወደ አምላካችሁ ወደእግዚአብሔርበእርግጥ እጸልያለሁ፤እግዚአብሔርያለኝን ሁሉ አንዳች ሳላስቀር እነግራችኋለሁ” አላቸው።
5 እነርሱም ኤርምያስን እንዲህ አሉት፤ “እግዚአብሔርአምላክህ በአንተ በኩል የሚለውን ነገር ሁሉ ባናደርግ፣እግዚአብሔርራሱ በእኛ ላይ እውነተኛና ታማኝ ምስክር ይሁን።
6 አምላካችንንእግዚአብሔርንበመታዘዝ መልካም ይሆንልን ዘንድ ነገሩ ቢስ ማማንም ባይስማማንም፣ አንተን ወደ እርሱ የምንልክህን አምላካችንንእግዚአብሔርንእንታዘዛለን።”
7 ከዐሥር ቀን በኋላየእግዚአብሔርቃል ወደ ኤርምያስ መጣ።
8 ስለዚህ የቃሬያን ልጅ ዮሐናንንና፣ ከእርሱም ጋር የነበሩትን የጦር መኰንኖች ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡን ሁሉ ከትንሽ እስከ ትልቅ ጠርቶ፤
9 እንዲህ አላቸው፤ “ልመናችሁን በፊቱ እንዳቀርብ ወደ እርሱ የላካችሁኝ የእስራኤል አምላክእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤
10 ‘ባመጣሁባችሁ ጥፋት አዝኛለሁና በዚህች ምድር ብትቀመጡ እሠራችኋለሁ እንጂ አላፈርሳችሁም፤ እተክላችኋለሁ እንጂ አልነቅላችሁም።
11 አሁን የሚያስፈራችሁን የባቢሎንን ንጉሥ አትፍሩ፤ አድናችሁ ዘንድ ከእጁም አስጥላችሁ ዘንድ፤ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና አትፍሩ ይላልእግዚአብሔር፤
12 እርሱ እንዲምራችሁና ወደ አገራችሁ እንዲመልሳችሁ እኔ እምራችኋለሁ።’
13 “እናንተ ግን፤ ‘በዚህች ምድር አንቀመጥም’ ብትሉና አምላካችሁንእግዚአብሔርንባትታዘዙ፣
14 ደግሞም፣ ‘ጦርነት ወደማናይበት፣ የመለከት ድምፅ ወደማንሰማበትና ወደማንራብበት ወደ ግብፅ ምድር ሄደን በዚያ እንኖራለንጰ ብትሉ፣
15 እንግዲህ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ፤የእግዚአብሔርንቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ ‘ወደ ግብፅ ለመሄድ ወስናችሁ እዚያ ለመቀመጥ ብትሄዱ፣
16 የፈራችሁት ሰይፍ በዚያ ያገኛችኋል፤ የሠጋችሁበት ራብ እስከ ግብፅ ድረስ ተከትሎአችሁ ይመጣል፤ በዚያም ትሞታላችሁ።
17 በዚያም ለመኖር ወደ ግብፅ ለመሄድ የወሰኑ ሁሉ በሰይፍ፣ በራብና በቸነፈር በእርግጥ ይሞታሉ፤ ከማመጣባቸውም ጥፋት አንድ እንኳ የሚተርፍ ወይም የሚያመልጥ አይገኝም።’
18 የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፦ ‘ቍጣዬና መዓቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩት ሁሉ ላይ እንደ ፈሰሰ፣ እንዲሁ ወደ ግብፅ በገባችሁ ጊዜ መዓቴ በእናንተ ላይ ይፈሳል፤ እናንተም የመነቀፊያና የድንጋጤ፣ የመረገሚያና የመዘባበቻ ምልክት ትሆናላችሁ፤ ይህንም ስፍራ ዳግመኛ አታዩም።’
19 “እናንተ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ፤እግዚብሔር፤ ‘ወደ ግብፅ አትሂዱ’ ብሎአችኋል፤ እኔም ዛሬ እንዳስጠነቀቅኋችሁ በእርግጥ ዕወቁ፤
20 ‘ወደ አምላካችን ወደእግዚአብሔርጸልይልን፤ እርሱ ያለህን ሁሉ ንገረን፤ እኛም እንታዘዛለን’ ብላችሁ ወደ አምላካችሁ ወደእግዚአብሔርበላካችሁኝ ጊዜ ሕይወታችሁን የሚያጠፋ ስሕተትፈጸማችሁ።
21 እነሆ፤ ዛሬ በግልጥ ነገርኋችሁ፤ እናንተ ግንእግዚአብሔርአምላካችሁ ልኮኝ የነገርኋችሁን ሁሉ አሁንም አልታዘዛችሁም፤
22 እንግዲህ ሄዳችሁ ልትኖሩበት በፈለጋችሁት ስፍራ በሰይፍ፣ በራብና በቸነፈር እንደምትሞቱ በርግጥ ዕወቁ።”