ጻድቁ ቅርንጫፍ
1 “በማሰማሪያ ቦታዬ ያሉትን በጎቼን ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው!” ይላልእግዚአብሔር።
2 ስለዚህ የእስራኤል አምላክእግዚአብሔርሕዝቤን ስለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፤ “መንጋዬን ስለ በተናችሁ፣ ስላባረራችሁና ተገቢውን ጥንቃቄ ስላላደረጋችሁላቸው፣ ለክፋታችሁ ተገቢውን ቅጣት አመጣባችኋለሁ” ይላልእግዚአብሔር፤
3 “የመንጋዬንም ቅሬታ ካባረርሁባቸው አገሮች ሁሉ እኔ ራሴ ሰብስቤ፣ ወደ መሰማሪያቸው እመልሳቸዋለሁ፤ በዚያም ፍሬያማ ይሆናሉ፤ ይበዛሉም።
4 የሚጠብቋቸውን እረኞች አስነሣላቸዋለሁ፤ ከእንግዲህም አይፈሩም፤ አይደነግጡም ከእነርሱም አንድ እንኳ አይጐድልም” ይላልእግዚአብሔር።
5 “እነሆ፤ ለዳዊት፣
ጻድቅ ቅርንጫፍ የማስነሣበት ጊዜ ይመጣል፤
እርሱም ፍትሕንና ጽድቅን የሚያደርግ፣
በጥበብ የሚገዛ ንጉሥ ይሆናል” ይላልእግዚአብሔር።
6 በእርሱም ዘመን ይሁዳ ይድናል፤
እስራኤልም በሰላም ይኖራል፤
የሚጠራበትም ስም፣
‘እግዚአብሔርጽድቃችን’ የሚል ነው።
7 “ስለዚህ ሰዎች፣ ‘እስራኤላውያንን ከግብፅ ምድር ያወጣ ሕያውእግዚአብሔርን!’ ብለው ከእንግዲህ የማይምሉበት ዘመን ይመጣል” ይላልእግዚአብሔር፤
8 ነገር ግን፣ ‘እስራኤልን ከሰሜን ምድርና እነርሱን ከበተነባቸው ከሌሎች አገሮች ያወጣ ሕያውእግዚአብሔርን’ ይላሉ፤ ከዚያ በኋላ በገዛ ምድራቸው ይኖራሉ።
ሐሰተኛ ነቢያት
9 ስለ ነቢያት፣
ልቤ በውስጤ ተሰብሮአል፤
ዐጥንቶቼም ተብረክርከዋል፤
ከእግዚአብሔርየተነሣ፣
ከቅዱስ ቃሉም የተነሣ፣
የወይን ጠጅ እንዳሸነፈው፣
እንደ ሰካራም ሰው ሆኛለሁ።
10 ምድሪቱ በአመንዝሮች ተሞልታለች፤
ከርግማን የተነሣምድሪቱ ታለቅሳለች፤
በምድረ በዳ ያሉት መሰማሪያዎች ደርቀዋል።
ነቢያቱም ጠማማ መንገድ ተከትለዋል፤
ሥልጣናቸውን ያለ አግባብ ተጠቅመዋል።
11 “ነቢዩም፣ ካህኑም በጽድቅ መንገድ የማይሄዱ ናቸው፤
በቤተ መቅደሴ እንኳ ሳይቀር ክፋታቸውን አይቻለሁ።”
ይላልእግዚአብሔር።
12 “ስለዚህ መንገዳቸው ድጥ ይሆናል፤
ወደ ጨለማ ይጣላሉ፤
ተፍገምግመውም ይወድቃሉ፤
በሚቀጡበትም ዓመት፣
መዓት አመጣባቸዋለሁ፤”
ይላልእግዚአብሔር።
13 “በሰማርያ ባሉ ነቢያት ላይ፣
ደስ የማያሰኝ ነገር አይቻለሁ፤
በበኣል ስም ትንቢት ተናገሩ፤
ሕዝቤን እስራኤልን አሳቱ።
14 በኢየሩሳሌም ባሉ ነቢያትም ላይ፣
የሚዘገንን ነገር አይቻለሁ፤
ያመነዝራሉ፤ በመዋሸትም ይኖራሉ፤
ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ፣
የክፉዎችን እጅ ያበረታሉ፤
በእኔ ዘንድ ሁሉም እንደ ሰዶም፣
ነዋሪዎቿም እንደ ገሞራ ናቸው።”
15 ስለዚህ የሰራዊት ጌታእግዚአብሔርስለ እነዚህ ነቢያት እንዲህ ይላል፤
“ከኢየሩሳሌም ነቢያት፣
በምድሪቱ ሁሉ ርኵሰት ተሠራጭቶአልና፤
መራራ ምግብ አበላቸዋለሁ፤
የተመረዘም ውሃ አጠጣቸዋለሁ።”
16 የሰራዊት ጌታእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤
“እነዚህ ነቢያት የሚተነብዩላችሁን አትስሙ፤
በባዶ ተስፋ ይሞሏችኋል፤
ከእግዚአብሔርአፍ የወጣ ሳይሆን፣
ከገዛ ልባቸው የሆነውን ራእይ ይናገራሉ።
17 እኔን ለሚንቁኝ፣
‘እግዚአብሔርሰላም ይሆንላችኋል ብሏል’ ይላሉ፤
የልባቸውን እልኸኝነት ለሚከተሉም ሁሉ፣
‘ክፉ ነገር አይነካችሁም’ ይሏቸዋል።
18 ቃሉን ለማየትና ለመስማት፣
እነማንየእግዚአብሔርምክር ባለበት ቆመዋል?
ቃሉን ያደመጠ፣ የሰማስ ማን ነው?
19 እነሆ፤የእግዚአብሔርዐውሎ ነፋስ፣
በቍጣ ይነሣል፤
ብርቱም ማዕበል፣
የክፉዎችን ራስ ይመታል።
20 እግዚአብሔርየልቡን ሐሳብ፣
ሙሉ በሙሉ ሳይፈጽም፣
ቍጣው እንዲሁ አይመለስም፤
በኋለኛው ዘመን፣
ይህን በግልጽ ትረዳላችሁ።
21 እኔ እነዚህን ነቢያት አልላክኋቸውም፤
እነርሱ ግን ለራሳቸው መልእክታቸውን ይዘው ሮጡ፣
ሳልናገራቸውም፣
ትንቢት ተናገሩ።
22 ምክሬ ባለበት ቢቆሙ ኖሮ፣
ቃሌን ለሕዝቤ ባሰሙ ነበር፤
ከክፉ መንገዳቸው፣
ከክፉ ሥራቸውም በመለሷቸው ነበር።
23 “እኔ የቅርብ አምላክ ብቻ ነኝን?
ይላልእግዚአብሔር፤
“የሩቅስ አምላክ አይደለሁምን?
24 እኔ እንዳላየው፣
በስውር ቦታ ሊሸሸግ የሚችል አለን?”
ይላልእግዚአብሔር።
“ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን”
ይላልእግዚአብሔር።
25 “ ‘ሕልም አለምሁ ሕልም አለምሁ’ እያሉ በስሜ የሐሰት ትንቢት የሚናገሩትን የነቢያትን ቃል ሰምቻለሁ፤
26 ይህ ነገር፣ የገዛ ልባቸውን ሽንገላ በሚተነብዩ በሐሰተኞች ነቢያት ልብ ውስጥ የሚቈየው እስከ መቼ ነው?
27 አባቶቻቸው በኣልን በማምለክ ስሜን እንደ ረሱ፣ እነርሱ በሚነጋገሩት ሕልም፣ ሕዝቤ ስሜን እንዲረሳ ያደረጉ ይመስላቸዋል።
28 ሕልመኛ ነቢይ ሕልሙን ያውራ፤ ቃሌ ያለው ግን በታማኝነት ይናገር፤ ገለባና እህል ምን አንድ አድርጎአቸው!” ይላልእግዚአብሔር።
29 “ቃሌ እንደ እሳት፣ ድንጋይንም እንደሚያደቅ መዶሻ አይደለምን?” ይላልእግዚአብሔር።
30 “ስለዚህ ቃሌን እርስ በእርስ በመሰራረቅ ከእኔ እንደ ተቀበሉ አድርገው የሚናገሩትን ነቢያት እቃወማለሁ” ይላልእግዚአብሔር።
31 “አፈጮሌነታቸውን በመጠቀም፣ ‘እግዚአብሔርእንዲህ ይላል’ የሚሉትን ነቢያት እቃወማለሁ” ይላልእግዚአብሔር፤
32 “እነሆ፤ ሐሰተኛ ሕልም ተመርኵዘው ትንቢት የሚናገሩትን ነቢያት እቃወማለሁ” ይላልእግዚአብሔር፤ እኔ ሳልልካቸው ወይም ሳልሾማቸው ደፍረው ውሸት ይናገራሉ፤ ሕዝቤንም ያስታሉ፤ ለዚህም ሕዝብ አንዳች አይረቡትም” ይላልእግዚአብሔር።
የእግዚአብሔር ሸክም ምንድ ነው?
33 “ይህ ሕዝብ ወይም ነቢይ ወይም ካህን፣ ‘የእግዚአብሔርሸክም ምንድን ነው?’ ብለው ቢጠይቁ፣ ‘ሸክሙ እናንተ ናችሁ፤እወረውራችኋለሁ ይላልእግዚአብሔር’ ብለህ መልስላቸው።
34 ነቢይ ወይም ካህን ወይም ማንኛውም ሰው፣ ‘የእግዚአብሔርሸክም’ እያለ ቢናገር፣ ያን ሰውና ቤቱን እቀጣለሁ።
35 እያንዳንዱ ለባልንጀራው ወይም ለዘመዱ፣ ‘እግዚአብሔርምን መልስ ሰጠ?’ ወይም፣ ‘እግዚአብሔርምን ተናገረ?’ ማለት ይገባዋል።
36 ከእንግዲህ ግን፣ ‘የእግዚአብሔርሸክም’ ብላችሁ መናገር አይገባችሁም፤ ምክንያቱም ለሰው ሁሉ የገዛ ራሱ ቃል ሸክሙ ስለሚሆን፣ የአምላካችንን የሰራዊት ጌታየእግዚአብሔርን፣ የሕያው አምላክን ቃል ታጣምማላችሁ።
37 ስለዚህ ለነቢዩ፣ ‘እግዚአብሔርምን መልስ ሰጠህ’ ወይም፣ ‘እግዚአብሔርምን ተናገረህ?’ ትለዋለህ፤
38 ‘የእግዚአብሔርሸክም’ ብትሉ እንኳ፣እግዚአብሔርግን እንዲህ ይላል፤ ‘እኔ፣ “የእግዚአብሔርሸክም” አትበሉ ብዬ ብነግራችሁም፣ እናንተ፣ “የእግዚአብሔርሸክም” ብላችኋል፤
39 ስለዚህ እናንተን፣ እንዲሁም ለእናንተና ለአባቶቻችሁ የሰጠኋትን ከተማ ጭምር ፈጽሜ እተዋችኋለሁ፤ ከፊቴ እጥላችኋለሁ፤
40 ለዘላለም የማይረሳ ዕፍረት፣ የዘላለምም ውርደት አመጣባችኋለሁ።