ኢሳይያስ 23

ስለ ጢሮስ የተነገረ ትንቢት

1 ስለ ጢሮስ የተነገረ ንግር፤

የተርሴስ መርከቦች ሆይ፤ ዋይ በሉ፤

ጢሮስ ተደምስሳለችና፤

ያለ ቤትና ያለ ወደብ ቀርታለች።

ከቆጵሮስ ምድር፣

ዜናው ወጥቶላቸዋል።

2 እናንት የባሕር ተጓዦች ያበለጠጓችሁ፣

በደሴቲቱ የምትኖሩ፣

የሲዶና ነጋዴዎችም ጸጥ በሉ።

3 በታላላቅ ውሆች ላይ፣

ለጢሮስ የሺሖር እህል ይመጣላት ነበር፤

የዐባይ መከርገቢዋ ነበር፤

እርሷም የመንግሥታቱ የንግድ መናኸሪያ ሆነች።

4 አንቺ ሲዶና ሆይ፣

አንቺ የባሕር ምሽግ ሆይ፣ ዕፈሪ፤

ባሕሩ፣ “አላማጥሁም፤ አልወለድሁም፤

ወንዶችና ሴቶች ልጆችን አላሳደግሁም” ብሎአልና።

5 ከጢሮስ የሚመጣው ዜና፣

በግብፅ በሚሰማበት ጊዜ ጭንቅ ይይዛቸዋል።

6 እናንት በደሴቲቱ የምትኖሩ፣ በዋይታ አልቅሱ፤

ወደ ተርሴስም ተሻገሩ፤

7 እግሮቿ ሩቅ አገር የወሰዷት፣

በዚያም እንድትሰፍር ያደረጓት፣

ጥንታዊቷ የድሮ ከተማ፣

የተድላ የደስ ከተማችሁ ይህች ናትን?

8 አክሊል በምታቀዳጀዋ፣

ነጋዴዎቿ መሳፍንት በሆኑ፣

በምድር የከበሩ ሻጮችና ለዋጮች በነበሯት፣

በጢሮስ ላይ ይህን ያሰበ ማን ነበር?

9 የክብርን ሁሉ ትዕቢት ሊያዋርድ፣

በምድር ከፍ ከፍ ያለውንም ሁሉ ዝቅ ሊያደርግ፣

የሰራዊት ጌታእግዚአብሔርወስኖአል።

10 የተርሴስ ልጅ ሆይ፤

ከእንግዲህ የሚከለክልሽ የለምና

እንደ ዐባይ ወንዝ ምድርሽን አጥለቅልቂ።

11 እግዚአብሔርእጁን በባሕር ላይ ዘረጋ፤

መንግሥታቷንም አስደነገጠ፤

የከነዓንምምሽጎች እንዲፈርሱ፣

ትእዛዝ ሰጠ፤

12 እንዲህም አለ፤ “አንቺ የተቀጠቀጥሽ የሲዶን ድንግል ሆይ!

ከእንግዲህ ደስ አይበልሽ፤

“ተነሺ ወደ ቆጵሮስ ተሻገሪ፤

በዚያም እንኳ ሰላም አታገኚም።”

13 እነሆ፤ የባቢሎናውያንንምድር ተመልከቱ፤

ሕዝቡ ከንቱ ሆኖአል።

አሦራውያን የምድረ በዳ አራዊት

መፈንጪያ አደረጓት፤

የግንብ ማማቸውን ሠሩባት፤

ምሽጎቿን አወደሙ፤

የፍርስራሽ ክምር አደረጓት።

14 እናንት የተርሴስ መርከቦች፣ ዋይ በሉ፤

ምሽጋችሁ ፈርሶአል።

15 በዚያ ጊዜ ጢሮስ፣ የአንድ ንጉሥ የሕይወት ዘመን ያህል፣ ለሰባ ዓመታት ትረሳለች። ከሰባ ዓመት በኋላ ግን፣ ስለ ጋለሞታዪቱ የተዘፈነው በጢሮስ ላይ ይሆናል፤

16 “አንች የተረሳሽ ጋለሞታ፤

በገና አንሺ፤ በከተማዪቱ ውስጥ ዙሪ፤

እንድትታወሽም፣

በገናሽን አሳምረሽ ምቺ፤ ብዙ ዘፈን ዝፈኚ።”

17 ሰባው ዓመት ካለፈ በኋላእግዚአብሔርጢሮስን ይጐበኛታል፤ ወደ ቀድሞው የግልሙትና ሥራዋ ተመልሳ፣ በምድር ላይ ካሉት የዓለም መንግሥታት ሁሉ ጋር በንግዷ ትገለሙታለች።

18 ያም ሆኖ ትርፏና ያገኘችው ሁሉለእግዚአብሔርየተለየ ይሆናል፤ አይከማችም፤ አይጠራቀምም። ትርፏምበእግዚአብሔርፊት ለሚኖሩት የተትረፈረፈ ምግብና ጥሩ ልብስ ይሆናል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *