መክብብ 1

ሁሉም ነገር ከንቱ ነው 1 በኢየሩሳሌም የነገሠው፣ የዳዊት ልጅ፣ የሰባኪው ቃል፤ 2 ሰባኪው፣ “ከንቱ፣ ከንቱ፣ የከንቱ ከንቱ፤ ሁሉም ነገር ከንቱ ነው” ይላል። 3 ከፀሓይ በታች ከሚለፋበት ተግባር ሁሉ፣ ሰው ምን ትርፍ ያገኛል? 4 ትውልድ ይሄዳል፤…

መክብብ 2

ምድራዊ ደስታ ከንቱ ነው 1 እኔም በልቤ፣ “መልካም የሆነውን ለማወቅ፣ በተድላ ደስታ እፈትንሃለሁ” አልሁ፤ ነገር ግን ያም ከንቱ ነበረ። 2 ደግሞም፣ “ሣቅ ሞኝነት ነው፤ ተድላ ደስታስ ምን ይጠቅማል?” አልሁ። 3 አሁንም አእምሮዬ በጥበብ እየመራኝ ራሴን…

መክብብ 3

ለሁሉም ጊዜ አለው 1 ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ ከሰማይ በታች ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ወቅት አለው፤ 2 ለመወለድ ጊዜ አለው፤ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፤ ለመንቀልም ጊዜ አለው፤ 3 ለመግደል ጊዜ አለው፤ ለማዳንም ጊዜ አለው፤…

መክብብ 4

ግፍ፣ ጥረት፣ ብቸኝነት 1 እንደ ገና ከፀሓይ በታች የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ አስተዋልሁም፤ የተገፉትን ሰዎች እንባ ተመለከትሁ፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፤ ኀይል በሚገፏቸው ሰዎች እጅ ነበረ፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም። 2 እኔም የቀድሞ ሙታን፣ ዛሬ በሕይወት ካሉት ሕያዋን ይልቅ፣…

መክብብ 5

እግዚአብሔርን ፍራ 1 ወደ እግዚአብሔር ቤት ስትሄድ እግርህን ጠብቅ። ለመስማት መቅረብ የሰነፎችን መሥዋዕት ከማቅረብ ይበልጣል፤ እነርሱ ክፉ እንደሚሠሩ አያውቁምና። 2 በአፍህ አትፍጠን፤ በእግዚአብሔርም ፊት ማንኛውንም ነገር ለመናገር፣ በልብህ አትቸኵል፤ እግዚአብሔር በሰማይ፣ አንተ ደግሞ በምድር ነህ፤…

መክብብ 6

1 ከፀሓይ በታች ሌላ ክፉ ነገር አየሁ፤ እርሱም ለሰዎች እጅግ የሚከብድ ነው፤ 2 ሰው ልቡ የሚሻውን እንዳያጣ፣ እግዚአብሔር ባለጠግነትን፣ ሀብትንና ክብርን ይሰጠዋል፤ እግዚአብሔር ግን እንዲደሰትበት ሥልጣን አልሰጠውም፤ ይልቁን ባዕድ ይደሰትበታል። ይህም ከንቱ፣ እጅግም ክፉ ነገር…

መክብብ 7

ጥበብ 1 መልካም ስም ከመልካም ሽቱ ይበልጣል፤ ከልደትም ቀን የሞት ቀን ይሻላል። 2 ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ፣ ወደ ሐዘን ቤት መሄድ ይሻላል፤ ሞት የሰው ሁሉ ፍጻሜ ነውና፤ ሕያው የሆነም ይህን ልብ ማለት ይገባዋል። 3 ሐዘን…

መክብብ 8

1 ነገሮችን መግለጽ የሚችል፣ እንደ ጠቢብ ያለ ሰው ማን ነው? ጥበብ የሰውን ፊት ታበራለች፤ የከበደ ገጽታውንም ትለውጣለች። ንጉሥን ታዘዝ 2 በእግዚአብሔር ፊት መሐላ ስለፈጸምህ፣ የንጉሥን ትእዛዝ አክብር እልሃለሁ። 3 ከንጉሥ ፊት ተጣድፈህ አትውጣ፤ የወደደውንም ማድረግ…

መክብብ 9

የሁሉም የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ 1 ስለዚህ ይህን ሁሉ በልቤ አስቤ እንዲህ አልሁ፤ ጻድቃንና ጠቢባን የሚሠሩትም ሥራ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ነገር ግን ፍቅር ይሁን ወይም ጥላቻ የሚጠብቀውን ማንም አያውቅም። 2 ጻድቃንና ኀጥአን፣ ደጎችና ክፉዎች፣ ንጹሓንና ርኩሳን፣…

መክብብ 10

1 የሞቱ ዝንቦች ሽቶን እንደሚያገሙ፣ ትንሽ ሞኝነትም ጥበብንና ክብርን ያቀላል። 2 የጠቢብ ልብ ወደ ቀኝ፣ የሞኝ ልብ ግን ወደ ግራ ያዘነብላል። 3 ሞኝ በጐዳና ሲሄድ ማስተዋል ይጐድለዋል፤ ጅል መሆኑንም ለማንም ይገልጻል። 4 የገዥ ቊጣ በተነሣብህ…