መዝሙር 1

ሁለቱ መንገዶች 1 በክፉዎች ምክር የማይሄድ፣ በኀጢአተኞች መንገድ የማይቆም፣ በፌዘኞችም ወንበር የማይቀመጥ፣ ሰው ብፁዕ ነው። 2 ነገር ግን ደስ የሚሰኘውበእግዚአብሔርሕግ ነው፤ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያሰላስለዋል። 3 እርሱም በወራጅ ውሃ ዳር እንደ ተተከለች፣ ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፣…

መዝሙር 2

መሢሓዊ ትዕይንት 1 ሕዝቦች ለምን ያሤራሉ? ሰዎችስ ለምን ከንቱ ነገር ያውጠነጥናሉ? 2 የምድር ነገሥታት ተነሡ፤ ገዦችምበእግዚአብሔርናበመሢሑላይ፣ ሊመክሩ ተሰበሰቡ፤ 3 “ሰንሰለታቸውን እንበጥስ፣ የእግር ብረታቸውንም አውልቀን እንጣል” አሉ። 4 በሰማይ ዙፋን ላይ የተቀመጠው ይሥቃል፤ ጌታም ይሣለቅባቸዋል። 5…

መዝሙር 3

የመከራ ተቀባዩ የጧት ጸሎት ዳዊት ከልጁ ከአቤሰሎም በሸሸ ጊዜ የዘመረው መዝሙር 1 እግዚአብሔርሆይ፤ ጠላቶቼ ምንኛ በዙ ስንቱስ በእኔ ላይ ተነሣ! 2 ብዙዎች ነፍሴን፣ “እግዚአብሔር አይታደግሽም” አሏት።ሴላ 3 እግዚአብሔርሆይ፤ አንተ ግን ዙሪያዬን የምትከልል ጋሻ ነህ፤ ክብሬና፣…

መዝሙር 4

የሠርክ ጸሎት ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች የሚዜም የዳዊት መዝሙር 1 የጽድቄ አምላክ ሆይ፤ በጠራሁህ ጊዜ መልስልኝ፤ ከጭንቀቴ አሳርፈኝ፤ ማረኝ፤ ጸሎቴንም ስማ። 2 ሰዎች ሆይ፤ እስከ መቼ ድረስ ክብሬን ዝቅታደርጋላችሁ? እስከ መቼስ ድረስ ከንቱ ነገርን ትወዳላችሁ? ሐሰትንስትሻላችሁ?ሴላ…

መዝሙር 5

የጧት ጸሎት ለመዘምራን አለቃ፤ በዋሽንት የሚዘመር፣ የዳዊት መዝሙር 1 እግዚአብሔርሆይ፤ ቃሌን አድምጥ፤ መቃተቴንም ቸል አትበል። 2 ንጉሤና አምላኬ ሆይ፤ ወደ አንተ እጸልያለሁና፣ ድረስልኝ ብዬ ስጮህ ስማኝ። 3 እግዚአብሔርሆይ፤ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፤ በማለዳ ልመናዬን በፊትህ አቀርባለሁ፤…

መዝሙር 6

በጭንቅ ጊዜ የቀረበ ጸሎት ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች የሚዘመር፤ የዳዊት መዝሙር በሸሚኒት 1 እግዚአብሔርሆይ፤ በቍጣህ አትገሥጸኝ፤ በመዓትህም አትቅጣኝ። 2 እግዚአብሔርሆይ፤ ዐቅመ ቢስ ነኝና ማረኝ፤ እግዚአብሔርሆይ፤ ዐጥንቶቼ ተናግተዋልና ፈውሰኝ። 3 ነፍሴ እጅግ ታውካለች፤ እስከ መቼ፤ አንተእግዚአብሔርሆይ፤ ይህ…

መዝሙር 7

በስደት ጊዜ የጻድቁ ሰው ጸሎት ዳዊት በብንያማዊው በኩዝ ምክንያት ለእግዚአብሔር የዘመረው መዝሙር 1 እግዚአብሔርአምላኬ ሆይ፤ አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝ፤ ታደገኝም፤ 2 አለበለዚያ እንደ አንበሳ ይዘነጣጥሉኛል፤ የሚያድነኝ በሌለበትም ይቦጫጭቁኛል። 3 እግዚአብሔርአምላኬ ሆይ፤ ይህን አድርጌ…

መዝሙር 8

የፈጣሪ ግርማ በፍጥረቱ ላይ ለመዘምራን አለቃ፣ በዋሽንት የሚዜም፤ የዳዊት መዝሙር 1 እግዚአብሔርአምላካችን ሆይ፤ ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊ ነው! ክብርህ ከሰማያት በላይ፣ ከፍ ከፍ ብሎአል። 2 ከልጆችና ጡት ከሚጠቡ ሕፃናት አፍ፣ ምስጋናንአዘጋጀህ፤ ከጠላትህ የተነሣ፣…

መዝሙር 9

በክፉ ላይ ፍርድ ለመዘምራን አለቃ፤ በሙትላቤን ቅኝት፤ የዳዊት መዝሙር 1 እግዚአብሔርሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ ስለ ድንቅ ሥራዎችህም ሁሉ እናገራለሁ። 2 በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም አደርጋለሁ፤ ልዑል ሆይ፤ ስምህን በመዝሙር እወድሳለሁ። 3 ጠላቶቼ ወደ ኋላ በተመለሱ…

መዝሙር 10

ለፍትሕ የቀረበ ልመና 1 እግዚአብሔርሆይ፤ ለምን እንዲህ ርቀህ ቆምህ? በመከራ ጊዜስ ለምን ድምፅህን አጠፋህ? 2 ክፉዎች የተጨነቀውን በእብሪት ያሳድዳሉ፤ በወጠኑት ተንኰል ይጠመዱ። 3 ክፉ ሰው በልቡ ምኞት ይኵራራል፤ ስግብግቡን ይባርካል፤እግዚአብሔርንምይዳፈራል። 4 ክፉ ሰው ከትዕቢቱ የተነሣ…