መዝሙር 91

የእግዚአብሔር ጥበቃ 1 በልዑል መጠጊያ የሚኖር፣ ሁሉን በሚችል አምላክጥላ ሥር ያድራል። 2 እግዚአብሔርን፣“መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣ የምታመንብህ አምላኬ” እለዋለሁ። 3 እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ፣ ከአሰቃቂ ቸነፈር ያድንሃልና። 4 በላባዎቹ ይጋርድሃል፤ በክንፎቹ ሥር መሸሸጊያ ታገኛለህ፤ ታማኝነቱ ጋሻና መከታ ይሆንሃል።…

መዝሙር 92

ጻድቅ ሰው ሲደሰት በሰንበት ቀን የሚዘመር መዝሙር፤ ማሕሌት 1 እግዚአብሔርንማመስገን መልካም ነው፤ ልዑል ሆይ፤ ለስምህ መዘመር ጥሩ ነው፤ 2 ምሕረትህን በማለዳ፣ ታማኝነትህንም በሌሊት ማወጅ መልካም ነው፤ 3 ዐሥር አውታር ባለው በገና፣ በመሰንቆም ቅኝት ታጅቦ ማወጅ…

መዝሙር 93

የእግዚአብሔር ግርማ 1 እግዚአብሔርነገሠ፤ ግርማንም ተጐናጸፈ፤ እግዚአብሔርግርማን ለበሰ፤ ብርታትንም ታጠቀ፤ ዓለም እንዳትናወጥ ጸንታለች፤ ማንም አይነቀንቃትም። 2 ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፤ አንተም ከዘላለም እስከ ዘላለም አለህ። 3 እግዚአብሔርሆይ፤ ወንዞች ከፍ አደረጉ፤ ወንዞች ድምፃቸውን ከፍ አደረጉ፤…

መዝሙር 94

የእግዚአብሔር ፍትሕ 1 የበቀል አምላክ፣ አንተእግዚአብሔርሆይ፤ የበቀል አምላክ ሆይ፤ ደምቀህ ተገለጥ። 2 አንተ የምድር ዳኛ ሆይ፤ ተነሥ፤ ለትዕቢተኞች የእጃቸውን ስጣቸው። 3 ክፉዎች እስከ መቼእግዚአብሔርሆይ፤ ክፉዎች እስከ መቼ ይፈነጫሉ? 4 የእብሪት ቃላት ያዥጐደጒዳሉ፤ ክፉ አድራጊዎች ሁሉ…

መዝሙር 95

የየዕለቱ መዝሙር 1 ኑ፤ ደስ እያለንለእግዚአብሔርእንዘምር፤ በድነታችንም ዐለት እልል እንበል። 2 ምስጋና ይዘን ፊቱ እንቅረብ፤ በዝማሬም እናወድሰው። 3 እግዚአብሔርታላቅ አምላክ ነውና፤ ከአማልክትም ሁሉ በላይ ታላቅ ንጉሥ ነው። 4 የምድር ጥልቆች በእጁ ናቸው፤ የተራራ ጫፎችም የእርሱ…

መዝሙር 96

እግዚአብሔር፤ ንጉሥም ዳኛም 1 ለእግዚአብሔርአዲስ ዝማሬ ዘምሩ፤ ምድር ሁሉ፤ለእግዚአብሔርዘምሩ። 2 ለእግዚአብሔርዘምሩ፤ ስሙንም ባርኩ፤ ማዳኑንም ነጋ ጠባ አውሩ። 3 ክብሩን በሕዝቦች መካከል፣ ድንቅ ሥራውንም በሰዎች ሁሉ ፊት ተናገሩ። 4 እግዚአብሔርታላቅ ነውና፤ ውዳሴም የሚገባው ነው፤ ከአማልክትም ሁሉ…

መዝሙር 97

የእግዚአብሔር ድል አድራጊነት 1 እግዚአብሔርነገሠ፤ ምድር ደስ ይበላት፤ በሩቅ ያሉ የባሕር ጠረፎች ሐሤት ያድርጉ። 2 ደመናና ጥቅጥቅ ያለ ጭጋግ በዙሪያው አለ፤ ጽድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው። 3 እሳት በፊቱ ይሄዳል፤ በዙሪያው ያሉትንም ጠላቶቹን ይፈጃል። 4…

መዝሙር 98

የዓለም ሁሉ ዳኛ መዝሙር 1 ለእግዚአብሔርአዲስ ዝማሬ አቅርቡ፤ እርሱ ድንቅ ነገሮችን አድርጎአልና፤ ቀኝ እጁ፣ ቅዱስ ክንዱም፣ ማዳንን አድርገውለታል። 2 እግዚአብሔርማዳኑን አሳወቀ፤ ጽድቁንም በሕዝቦች ፊት ገለጠ። 3 ለእስራኤል ቤት ምሕረቱን፣ ታማኝነቱንም አሰበ፤ የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ፣ የአምላካችንን…

መዝሙር 99

ጻድቅና ቅዱስ አምላክ 1 እግዚአብሔርነገሠ፤ ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ፤ በኪሩቤል ላይ በዙፋን ተቀምጦአል፤ ምድር ትናወጥ። 2 እግዚአብሔርበጽዮን ታላቅ ነው፤ ከሕዝቦችም ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ብሎአል። 3 ታላቁንና አስፈሪውን ስምህን ይወድሱ፤ እርሱ ቅዱስ ነው። 4 ፍትሕን የምትወድ፣ ኀያል…

መዝሙር 100

እግዚአብሔርን ለማመስገን የቀረበ ግብዣ የምስጋና መዝሙር 1 ምድር ሁሉለእግዚአብሔርእልል በሉ፤ 2 እግዚአብሔርንበደስታ አገልግሉት፤ በፍስሓ ዝማሬ ፊቱ ቅረቡ። 3 እግዚአብሔርአምላክ መሆኑን ዕወቁ፤ እርሱ ፈጠረን፤ እኛም የእርሱ ነን፤ እኛ ሕዝቡ የማሰማሪያው በጎች ነን። 4 በምስጋና ወደ ደጆቹ፣…