መዝሙር 131

በእግዚአብሔር መታመን የዳዊት መዝሙረ መዓርግ 1 እግዚአብሔርሆይ፤ ልቤ አልታበየም፤ ዐይኔ ከፍ ከፍ አላለም፤ ሐሳቤ ለዐጒል ትልቅነት አልተነሣሣም፤ ከዐቅሜም በላይ አልተንጠራራሁም። 2 ነገር ግን ነፍሴን ጸጥ፣ ዝም አሰኘኋት፤ ጡት የጣለ ልጅ ዐርፎ እናቱ ላይ እንደሚቀመጥ፣ ነፍሴ…

መዝሙር 132

የክብረ በዓል መዝሙር መዝሙረ መዓርግ 1 እግዚአብሔርሆይ፤ ዳዊትን፣ የታገሠውንም መከራ ሁሉ ዐስብ፤ 2 እርሱለእግዚአብሔርማለ፤ ለያዕቆብም ኀያል አምላክ እንዲህ ሲል ተሳለ፤ 3 “ወደ ቤቴ አልገባም፤ ዐልጋዬም ላይ አልወጣም፤ 4 ለዐይኖቼ እንቅልፍን፣ ለሽፋሽፍቶቼም ሸለብታ አልሰጥም፤ 5 ለእግዚአብሔርስፍራን፣…

መዝሙር 133

የወንድማማች ፍቅር የዳዊት መዝሙረ መዓርግ 1 ወንድሞች ተስማምተው በአንድነት ሲኖሩ፣ እንዴት መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል! 2 በራስ ላይ ፈሶ፣ እስከ ጢም እንደሚዘልቅ፣ እስከ አሮን ጢም እንደሚወርድ፣ እስከ ልብሱም ዐንገትጌ እንደሚደርስ ውድ ሽቱ ነው። 3…

መዝሙር 134

የሠርክ መዝሙር መዝሙረ መዓርግ 1 እናንት በሌሊት ቆማችሁበእግዚአብሔርቤት የምታገለግሉ፣ የእግዚአብሔርባሪያዎች ሁላችሁ፤እግዚአብሔርንባርኩ። 2 በመቅደሱ ውስጥ እጆቻችሁን አንሡ፤ እግዚአብሔርንምባርኩ። 3 ሰማይንና ምድርን የሠራእግዚአብሔር፣ ከጽዮን ይባርክህ።

መዝሙር 135

የምስጋና መዝሙር 1 ሃሌ ሉያ። የእግዚአብሔርንስም ወድሱ፤ እናንትየእግዚአብሔርአገልጋዮች ሆይ፤ አመስግኑት፤ 2 በእግዚአብሔርቤት፣ በአምላካችን ቤት አደባባይ የምትቆሙ አመስግኑት። 3 እግዚአብሔርቸር ነውናእግዚአብሔርንአመስግኑ፤ መልካም ነውና፣ ለስሙ ዘምሩ፤ 4 እግዚአብሔርያዕቆብን ለራሱ፣ እስራኤልንም ውድ ንብረቱ አድርጎ መርጦአልና። 5 እግዚአብሔርታላቅ እንደሆነ፣…

መዝሙር 136

ምስጋና በቅብብሎሽ መዝሙር 1 እግዚአብሔርንአመስግኑ፤ ቸር ነውና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። 2 የአማልክትን አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። 3 የጌቶችን ጌታ አመሰግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። 4 እርሱ ብቻውን ታላላቅ ታምራትን የሚያደርግ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ 5 ሰማያትን…

መዝሙር 137

የግዞተኞች ቅኔ 1 በባቢሎን ወንዞች አጠገብ፣ በዚያ ተቀምጠን ሳለን፣ ጽዮን ትዝ ባለችን ጊዜ አለቀስን። 2 እዚያም በአኻያ ዛፎች ላይ፣ በገናዎቻችንን ሰቀልን። 3 የማረኩን በዚያ እንድንዘምርላቸው ጠየቁን፤ የሚያሠቃዩን የደስታ ዜማ ፈለጉብን፤ ደግሞም፣ “ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን”…

መዝሙር 138

የምስጋና መዝሙር የዳዊት መዝሙር 1 እግዚአብሔር ሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ በአማልክት ፊት በመዝሙር እወድስሃለሁ። 2 ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤ ስለ ምሕረትህና ስለ ታማኝነትህ፣ ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ፤ ስምህንና ቃልህን፣ ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ አድርገሃልና። 3 በጠራሁህ…

መዝሙር 139

ሁሉን ዐዋቂ አምላክ ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር 1 እግዚአብሔርሆይ፤ መረመርኸኝ፤ ደግሞም ዐወቅኸኝ። 2 አንተ መቀመጤንና መነሣቴን ታውቃለህ፤ የልቤንም ሐሳብ ገና ከሩቁ ታስተውላለህ። 3 መሄድ መተኛቴን አጥርተህ ታውቃለህ፤ መንገዶቼንም ሁሉ ተረድተሃቸዋል። 4 እግዚአብሔርሆይ፤ ገና ቃል ከአንደበቴ…

መዝሙር 140

በክፉዎች ላይ የቀረበ ጸሎት ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር 1 እግዚአብሔርሆይ፤ ከክፉ ሰዎች አድነኝ፤ ከዐመፀኞችም ሰዎች ጠብቀኝ፤ 2 እነርሱ በልባቸው ክፉ ነገር ያውጠነጥናሉ፤ በየዕለቱም ጦርነት ይጭራሉ። 3 ምላሳቸውን እንደ እባብ ያሾላሉ፤ ከከንፈራቸውም በታች የእፉኝት መርዝ አለ።ሴላ…