መዝሙር 141

የክፉዎችን ድሎት ላለመመኘት የቀረበ ጸሎት 1 እግዚአብሔርሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ፈጥነህ ድረስልኝ፤ ወደ አንተ ስጣራም ድምፄን ስማ። 2 ጸሎቴ በፊትህ እንደ ዕጣን ትቈጠርልኝ፤ እጄን ማንሣቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን። 3 እግዚአብሔርሆይ፤ ለአፌ ጠባቂ አድርግ፤ የከንፈሮቼንም…

መዝሙር 142

የሚታደን ሰው ጸሎት ዋሻ ውስጥ በነበረ ጊዜ፤ የዳዊት ትምህርት፤ ጸሎት 1 ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደእግዚአብሔርእጮኻለሁ፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደእግዚአብሔርልመና አቀርባለሁ። 2 ብሶቴን በፊቱ አፈስሳለሁ፤ ችግሬንም በፊቱ እናገራለሁ። 3 መንፈሴ በውስጤ ሲዝል፣ መንገዴን የምታውቅ አንተ ነህ፤…

መዝሙር 143

ትሑት ልመና የዳዊት መዝሙር 1 እግዚአብሔርሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ ልመናዬን አድምጥ፤ በታማኝነትህና በጽድቅህም፣ ሰምተህ መልስልኝ። 2 ሰው ሆኖ በፊትህ ጻድቅ የለምና፣ ባሪያህን ወደ ፍርድ አታቅርበው። 3 ጠላት እስከ ሞት አሳዶኛል፤ ሕይወቴንም አድቅቆ ከዐፈር ቀላቅሎአል፤ ቀደም ብለው…

መዝሙር 144

የጦርነት መዝሙር የዳዊት መዝሙር 1 እጆቼን ለጦርነት፣ ጣቶቼን ለውጊያ የሚያሠለጥን፣ እግዚአብሔርዐለቴ ይባረክ። 2 እርሱ አፍቃሪ አምላኬና ጽኑ ዐምባዬ ነው፤ ምሽጌና ታዳጊዬ፣ የምከለልበትም ጋሻዬ ነው፤ ሕዝቤን የሚያስገዛልኝምእርሱ ነው። 3 እግዚአብሔርሆይ፤ ይህን ያህል በልብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ…

መዝሙር 145

ምስጋና ለንጉሡ ለእግዚአብሔር የዳዊት የምስጋና መዝሙር 1 አምላኬና ንጉሤ ሆይ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህን ከዘላለም እስከ ዘላለም እባርካለሁ። 2 በየቀኑ እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ከዘላለም እስከ ዘላለም አመሰግናለሁ። 3 እግዚአብሔርታላቅ ነው፤ እጅግ ሊመሰገንም ይገባዋል፤ ታላቅነቱም አይመረመርም። 4…

መዝሙር 146

ለረድኤት አምላክ ምስጋና 1 ሃሌ ሉያ። ነፍሴ ሆይ፤እግዚአብሔርንባርኪ። 2 በምኖርበት ዘመን ሁሉእግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ በሕይወትም እስካለሁ ለአምላኬ እዘምራለሁ። 3 በገዦች አትታመኑ፤ ማዳን በማይችሉ ሥጋ ለባሾችም አትመኩ። 4 መንፈሳቸው ትወጣለች፤ ወደ መሬታቸውም ይመለሳሉ፤ ያን ጊዜም ዕቅዳቸው እንዳልነበር…

መዝሙር 147

መዝሙር ለሁሉን ቻይ አምላክ 1 ሃሌ ሉያ። አምላካችንን በመዝሙር ማወደስ እንዴት መልካም ነው፤ እርሱን ማመስገን ደስ ያሰኛል፤ ይህ ተገቢም ነው። 2 እግዚአብሔርኢየሩሳሌምን መልሶ ይሠራታል፤ ከእስራኤል የተበተኑትን ይሰበስባል። 3 ልባቸው የተሰበረውን ይፈውሳል፤ ቍስላቸውንም ይጠግናል። 4 የከዋክብትን…

መዝሙር 148

ፍጥረተ ዓለም ሁሉ ያመስግን 1 ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርንከሰማያት አመስግኑት፤ በላይ በአርያም አመስግኑት። 2 መላእክቱ ሁሉ አመስግኑት፤ ሰራዊቱ ሁሉ አመስግኑት፤ 3 ፀሓይና ጨረቃ አመስግኑት፤ የምታበሩ ከዋክብት ሁሉ አመስግኑት። 4 ሰማየ ሰማያት አመስግኑት፤ ከሰማያትም በላይ ያላችሁ ውሆች…

መዝሙር 149

የድል መዝሙር 1 ሃሌ ሉያ። ለእግዚአብሔርአዲስ ቅኔ ተቀኙ፤ ምስጋናውንም በቅዱሳን ጉባኤ ዘምሩ። 2 እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው፤ የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤት ያድርጉ። 3 ስሙን በሽብሰባ ያመስግኑ፤ በከበሮና በመሰንቆ ይዘምሩለት። 4 እግዚአብሔርበሕዝቡ ደስ ይለዋልና፤ የዋሃንንም በማዳኑ…

መዝሙር 150

የምስጋና መዝሙር 1 ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርንበመቅደሱ አመስግኑት፤ በታላቅ ጠፈሩ አወድሱት። 2 ስለ ብርቱ ሥራው አመስግኑት፤ እጅግ ታላቅ ነውና ወድሱት። 3 በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ ወድሱት። 4 በከበሮና በሽብሸባ አመስግኑት፤ በባለ አውታር መሣሪያና በእምቢልታ አወድሱት።…