መዝሙር 61

የግዞተኛ ጸሎት ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች የሚዘመር፤ የዳዊት መዝሙር 1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጩኸቴን ስማ፤ ጸሎቴንም አድምጥ። 2 ልቤ በዛለ ጊዜ፣ ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ከእኔ ይልቅ ከፍ ወዳለው ዐለት ምራኝ። 3 አንተ መጠጊያዬ፣ ከጠላትም የምተገንብህ…

መዝሙር 62

ተስፋ በእግዚአብሔር ላይ ብቻ ለመዘምራን አለቃ፤ ለኤዶታም፤ የዳዊት መዝሙር 1 ነፍሴ ዕረፍት የምታገኘው በእግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ድነቴም የሚመጣልኝ ከእርሱ ዘንድ ነው። 2 ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤ መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ ከቶም አልናወጥም። 3 ሰውን የምታጠቁት…

መዝሙር 63

እግዚአብሔርን መፈለግ በይሁዳ ምድረ በዳ በነበረ ጊዜ፤ የዳዊት መዝሙር 1 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ከልብ እሻለሁ፤ ውሃ በሌለበት፣ በደረቅና በተራቈተ ምድር፣ ነፍሴ አንተን ተጠማች፤ ሥጋዬም አንተን ናፈቀች። 2 ስለዚህ በመቅደስ ውስጥ አየሁህ፤ ኀይልህንና…

መዝሙር 64

የተሳዳቢዎች ቅጣት ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር 1 አምላክ ሆይ፤ የብሶት ቃሌን ስማ፤ ሕይወቴንም ከሚያስፈራ የጠላት ዛቻ ከልላት። 2 ከክፉዎች አድማ ሰውረኝ፤ ከዐመፀኞችም ሸንጎ ጋርደኝ። 3 እነርሱ ምላሳቸውን እንደ ሰይፍ ይስላሉ፤ መርዘኛ ቃላቸውንም እንደ ፍላጻ ያነጣጥራሉ።…

መዝሙር 65

የምስጋና መዝሙር ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት የምስጋና መዝሙር 1 እግዚአብሔር ሆይ፤ በጽዮን ለአንተ ውዳሴ ይገባል፤ ለአንተ የተሳልነውን እንፈጽማለን። 2 ጸሎትን የምትሰማ ሆይ፤ የሰው ልጆች ሁሉ ወደ አንተ ይመጣሉ። 3 ኀጢአት ባጥለቀለቀን ጊዜ፣ አንተ መተላለፋችንን ይቅር አልህ።…

መዝሙር 66

የኅብረት ምስጋና ለመዘምራን አለቃ፤ ማኅሌት፤ መዝሙር 1 ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል ይበል! 2 ለስሙ ክብር ዘምሩ፤ ውዳሴውንም አድምቁ 3 እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፤ “ሥራህ እንዴት ግሩም ነው! ጠላቶችህ ከኀይልህ ታላቅነት የተነሣ፣ በፊትህ ይርዳሉ። 4 ምድር ሁሉ…

መዝሙር 67

የመከር ጊዜ መዝሙር ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች የሚዘመር፤ የዳዊት መዝሙር፤ ማኅሌት 1 እግዚአብሔር ይማረን፤ ይባርከን፤ ፊቱንም በላያችን ያብራ፤ሴላ 2 መንገድህ በምድር ላይ፣ ማዳንህም በሕዝቦች ሁሉ መካከል ይታወቅ ዘንድ። 3 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰዎች ያመስግኑህ፤ ሰዎች ሁሉ ምስጋና…

መዝሙር 68

ብሔራዊ የድል መዝሙር ለመዘምራን አለቃ የዳዊት መዝሙር፤ ማኅሌት 1 እግዚአብሔር ይነሣ፤ ጠላቶቹ ይበተኑ፤ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ። 2 ጢስ እንደሚበንን፣ እንዲሁ አብንናቸው። ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፣ ክፉዎችም እንዲሁ ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ። 3 ጻድቃን ግን ደስ ይበላቸው፤…

መዝሙር 69

እንጒርጒሮ ለመዘምራን አለቃ፤ በ“ጽጌረዳ” ዜማ፤ የዳዊት መዝሙር 1 አምላክ ሆይ፤ አድነኝ፤ ውሃ እስከ ዐንገቴ ደርሶብኛልና። 2 የእግር መቆሚያ በሌለው፣ በጥልቅ ረግረግ ውስጥ ሰጥሜአለሁ፤ ወደ ጥልቅ ውሃ ገባሁ፤ ሞገዱም አሰጠመኝ። 3 በጩኸት ደከምሁ፤ ጉሮሮዬም ደረቀ፤ አምላኬን…

መዝሙር 70

የጭንቀት ጩኸት ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር፤ ለመታሰቢያ 1 አምላክ ሆይ፤ ታድነኝ ዘንድ ዘንበል በል፤ እግዚአብሔርሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን። 2 ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ፣ ይፈሩ፤ ሁከትም ይምጣባቸው፤ የእኔን መጐዳት የሚመኙ፣ በውርደት ወደ ኋላቸው ይመለሱ። 3 በእኔ ላይ፣…