መዝሙር 71

የሽማግሌ ጸሎት 1 እግዚአብሔርሆይ፤ አንተን መጠጊያ አደረግሁ፤ ከቶም አልፈር። 2 በጽድቅህ ታደገኝ፤ አስጥለኝም፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ አድነኝም። 3 ምንጊዜም የምሸሽበት፣ መጠጊያ ዐለት ሁነኝ፤ አንተ ዐለቴ ምሽጌ ነህና፣ ታድነኝ ዘንድ ትእዛዝህ ይውጣ። 4 አምላኬ ሆይ፤…

መዝሙር 72

በተስፋ የሚጠባበቀው ንጉሥ ስለ ሰሎሞን 1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ፍትህን ለንጉሥ፣ ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ ዐድል፤ 2 እርሱም ሕዝብህን በጽድቅ ይዳኛል፤ ለተቸገሩትም በትክክል ይፈርዳል። 3 ተራሮች ብልጽግናን፣ ኰረብቶችም የጽድቅን ፍሬ ለሕዝቡ ያመጣሉ። 4 ለተቸገረው ሕዝብ ይሟገታል፤ የድኾችን…

መዝሙር 73

የፍትሕ አሸናፊነት የአሳፍ መዝሙር 1 እግዚአብሔር ልባቸው ንጹሕ ለሆነ፣ ለእስራኤል እንዴት ቸር ነው! 2 እኔ ግን እግሬ ሊሰናከል፣ አዳልጦኝም ልወድቅ ጥቂት ቀረኝ። 3 ክፉዎች ሲሳካላቸው አይቼ፣ በዐመፀኞች ቀንቼ ነበርና። 4 አንዳች ጣር የለባቸውም፤ ሰውነታቸውም ጤናማና…

መዝሙር 74

ስለ መቅደሱ መፍረስ የቀረበ ጸሎት የአሳፍ ትምህርት 1 አምላክ ሆይ፤ ለዘላለም የጣልኸን ለምንድን ነው? በማሰማሪያህ ባሉ በጎችህስ ላይ ቍጣህ ለምን ነደደ? 2 ጥንት ገንዘብህ ያደረግሃትን ጉባኤ፣ የዋጀሃትን የርስትህን ነገድ፣ መኖሪያህ ያደረግሃትን የጽዮን ተራራ አስብ። 3…

መዝሙር 75

ለመለኮታዊው ዳኛ የቀረበ ዝማሬ ለመዘምራን አለቃ፤ “አታጥፋ” በሚለው ቅኝት የሚዜም፤ የአሳፍ መዝሙር ማሕሌት 1 አምላክ ሆይ፤ ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ ስምህ ቅርብ ነውና ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ ሰዎችም ስለ ድንቅ ሥራህ ይናገራሉ። 2 አንተም እንዲህ አልህ፤ “ለይቼ በወሰንኋት ሰዓት፣…

መዝሙር 76

ግርማው ለሚያሰፈራው አምላክ የቀረበ ቅኔ ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች፤ የአሳፍ መዝሙር ማሕሌት 1 እግዚአብሔር በይሁዳ ታወቀ፤ ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው። 2 ድንኳኑ በሳሌም፣ ማደሪያውም በጽዮን ነው። 3 በዚያም ተወርዋሪውን ፍላጻ፣ ጋሻንና ሰይፍን፣ ጦርንም ሰበረ።ሴላ 4 አንተ…

መዝሙር 77

የእስራኤል ጥንተ ነገር አሰላስሎ ለመዘምራን አለቃ፤ ለኤዶታም፤ የአሳፍ መዝሙር 1 ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ ይሰማኝም ዘንድ ወደ አምላክ ጮኽሁ። 2 በመከራዬ ቀን እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤ በሌሊትም ያለ ድካም እጆቼን ዘረጋሁ፤ ነፍሴም አልጽናና አለች። 3…

መዝሙር 78

በእስራኤል የተገኘ ታሪክ የአሳፍ ትምህርት 1 ሕዝቤ ሆይ፤ ትምህርቴን ስማ፤ ጆሮህንም ወደ አንደበቴ ቃል አዘንብል። 2 አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ከጥንት በነበረ እንቈቅልሽ እናገራለሁ፤ 3 ይህም የሰማነውና ያወቅነው፣ አባቶቻችንም የነገሩን ነው። 4 እኛም ከልጆቻቸው አንደብቀውም፤ የእግዚአብሔርንምስጋና፣…

መዝሙር 79

ብሔራዊ ሰቆቃ የአሳፍ መዝሙር 1 አምላክ ሆይ፤ ሕዝቦች ርስትህን ወረሩ፤ የተቀደሰውን ቤተ መቅደስህን አረከሱ፤ ኢየሩሳሌምንም አፈራርሰው ጣሏት። 2 የባሪያዎችህን ሬሳ ለሰማይ ወፎች፣ የቅዱሳንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት፣ ምግብ አድርገው ሰጡ። 3 ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ፣ እንደ ውሃ…

መዝሙር 80

ለእስራኤል ተሐድሶ የቀረበ ጸሎት ለመዘምራን አለቃ፤ “የኪዳን ጽጌረዳ” በሚለው ቅኝት የሚዜም፤ የአሳፍ መዝሙር 1 ዮሴፍን እንደ በግ መንጋ የምትመራ፣ የእስራኤል እረኛ ሆይ፤ ስማን፤ በኪሩቤል ላይ በዙፋን የምትቀመጥ ሆይ፤ በብርሃንህ ተገለጥ፤ 2 በኤፍሬም፣ በብንያምና በምናሴ ፊት…