ማሕልየ መሓልይ 1

1 ከመዝሙር ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር። 2 በከንፈሩ መሳም ይሳመኝ ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ ደስ ያሰኛልና። 3 የሽቱህ መዐዛ ደስ ያሰኛል፤ ስምህ እንደሚፈስ ሽቱ ነው፤ ታዲያ ቈነጃጅት ቢወዱህ ምን ያስደንቃል 4 ይዘኸኝ ሂድ፤ እንፍጠን፤ ንጉሡ…

ማሕልየ መሓልይ 2

1 እኔ የሳሮን ጽጌረዳ፣ የሸለቆም አበባነኝ። 2 በእሾኽ መካከል እንዳለ ውብ አበባ፣ ውዴም በቈነጃጅት መካከል እንዲሁ ናት። 3 በዱር ዛፎች መካከል እንዳለ እንኰይ፣ ውዴም በጐልማሶች መካከል እንዲሁ ነው፤ በጥላው ሥር መቀመጥ ደስ ያሰኛል፤ የፍሬውም ጣፋጭነት…

ማሕልየ መሓልይ 3

1 ሌሊቱን ሙሉ በአልጋዬ ላይ ሆኜ፣ ውዴን ተመኘሁ፤ ተመኘሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም። 2 ተነሥቼ ወደ ከተማዪቱ እወጣለሁ፤ በዋና ዋና መንገዶችና በአደባባዮች እዘዋወራለሁ፤ ውዴንም እፈልገዋለሁ፤ ስለዚህም ፈለግሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም። 3 በከተማዪቱ ውስጥ ሲዘዋወሩ፣ የከተማዪቱ ጠባቂዎች…

ማሕልየ መሓልይ 4

1 ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነሽ! እንዴትስ ያለሽ ቈንጆ ነሽ ከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ዐይኖችሽ እንደ ርግብ ዐይኖች ናቸው፤ ጠጒርሽም ከገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ፣ የፍየል መንጋ ነው። 2 ጥርሶችሽ ወዲያው ተሸልተው፣ ከመታጠቢያ እንደ ወጡ የበግ መንጋ ናቸው፤…

ማሕልየ መሓልይ 5

1 እኅቴ ሙሽራዬ፣ ወደ አትክልት ቦታዬ መጥቻለሁ፤ ከርቤዬን ከቅመሜ ጋር ሰብስቤአለሁ፤ የማር እንጀራዬን ከነወለላው በልቻለሁ፤ ወይኔንና ወተቴንም ጠጥቻለሁ። ወዳጆች ሆይ፤ ብሉ፤ ጠጡ፤ እናንት ፍቅረኞች ሆይ፤ እስክትረኩ ጠጡ። 2 እኔ ተኝቻለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቶአል፤ ስሙ! ውዴ…

ማሕልየ መሓልይ 6

1 አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፤ ውድሽ ወዴት ሄደ? አብረንሽም እንድንፈልገው፣ ውድሽ የሄደው በየት በኩል ነው? 2 ውዴ መንጋውን ለማሰማራት፣ ውብ አበቦችንም ለመሰብሰብ፣ የቅመማ ቅመም መደቦቹ ወዳሉበት፣ ወደ አትክልት ቦታው ወርዶአል። 3 እኔ የውዴ ነኝ፤…

ማሕልየ መሓልይ 7

1 አንቺ የልዑል ልጅ ሆይ፤ ነጠላ ጫማ የተጫሙ እግሮችሽ እንዴት ያምራሉ ሞገስን የተጐናጸፉ ዳሌዎችሽ፣ ብልኅ አንጥረኛ የተጠበባቸውን የዕንቊ ሐብል ይመስላሉ። 2 ዕንብርትሽ ጥሩ የወይን ጠጅ እንደ ማይጐድልበት፣ እንደ ክብ ጽዋ ነው፤ ወገብሽ ዙሪያውን በውብ አበባ…

ማሕልየ መሓልይ 8

1 ምነው አንተ የእናቴን ጡት እንደ ጠባ፣ እንደ ወንድሜ በሆንህ! ከዚያም ውጭ ባገኝህ፣ እስምህ ነበር፤ ታዲያ ማንም ባልናቀኝ! 2 እኔም ወደ አስተማረችኝ፣ ወደ እናቴም ቤት፣ እጅህን ይዤ በወሰድሁህ ነበር፤ የምትጠጣውን ጣፋጭ የወይን ጠጅ፣ የሮማኔን ጭማቂም…