ምሳሌ 1
መግቢያ፤ የምሳሌዎቹ ዐላማና ጭብጥ 1 የእስራኤል ንጉሥ፣ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን ምሳሌዎች፤ 2 ጥበብንና ተግሣጽን ለመቀበል፤ ጥልቅ ሐሳብ የሚገልጡ ቃላትን ለማስተዋል፤ 3 ጽድቅን፣ ፍትሕንና ሚዛናዊ ብያኔን በማድረግ፣ የተገራ ጠቢብ ልቦናን ለማግኘት፤ 4 ብስለት ለሌላቸው አስተዋይነትን፣ በዕድሜ…
መግቢያ፤ የምሳሌዎቹ ዐላማና ጭብጥ 1 የእስራኤል ንጉሥ፣ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን ምሳሌዎች፤ 2 ጥበብንና ተግሣጽን ለመቀበል፤ ጥልቅ ሐሳብ የሚገልጡ ቃላትን ለማስተዋል፤ 3 ጽድቅን፣ ፍትሕንና ሚዛናዊ ብያኔን በማድረግ፣ የተገራ ጠቢብ ልቦናን ለማግኘት፤ 4 ብስለት ለሌላቸው አስተዋይነትን፣ በዕድሜ…
ከጥበብ የሚገኝ በረከት 1 ልጄ ሆይ፤ ቃሌን ብትቀበል፣ ትእዛዜንም በልብህ ብታኖር፣ 2 ጆሮህን ወደ ጥበብ ብታቀና፣ ልብህንም ወደ ማስተዋል ብትመልስ፣ 3 እንዲሁም የመለየት ጥበብን ብትማጠን፣ ድምፅህን ከፍ አድርገህ ማስተዋልን ብትጣራ፣ 4 እርሷንም እንደ ብር ብትፈልጋት፣…
ከጥበብ የሚገኝ ተጨማሪ በረከት 1 ልጄ ሆይ፤ ትምህርቴን አትርሳ፤ ትእዛዛቴን በልብህ ጠብቅ፤ 2 ቀኖችን ይጨምሩልሃል፤ ዓመቶችንም ያረዝሙልሃል፤ ሕይወት፣ ሀብትንና ሰላምን ያበዙልሃል። 3 ፍቅርና ታማኝነት ከቶ አይለዩህ፤ በዐንገትህ ዙሪያ እሰራቸው፤ በልብህም ጽላት ላይ ጻፋቸው። 4 በዚያን…
ጥበብ ከሁሉ በላይ መሆኗ 1 ልጆቼ ሆይ፤ የአባትን ምክር አድምጡ፤ ልብ ብላችሁ ስሙ፤ ማስተዋልንም ገንዘብ አድርጉ። 2 በጎ ትምህርት እሰጣችኋለሁ፤ ስለዚህ ትምህርቴን አትተዉ። 3 በአባቴ ቤት ገና ለግላጋ ወጣት፣ ለእናቴም አንድ ልጇ ብቻ በነበርሁ ጊዜ፣…
ከአመንዝራነት መጠንቀቅ 1 ልጄ ሆይ፤ ጥበቤን ልብ በል፤ የማስተዋል ቃሌንም በጥሞና አድምጥ፤ 2 ይህም ልባምነትን ገንዘብ እንድታደርግ፣ ከንፈሮችህም ዕውቀትን እንዲጠብቁ ነው። 3 የአመንዝራ ሴት ከንፈር ማር ያንጠባጥባልና፤ አንደበቷም ከቅቤ ይለሰልሳል፤ 4 በመጨረሻ ግን እንደ እሬት…
ከተላላነት መራቅ 1 ልጄ ሆይ፤ ለጎረቤትህ ዋስ ብትሆን፣ ስለ ሌላውም ሰው እጅ መትተህ ቃል ብትገባ፣ 2 በተናገርኸው ነገር ብትጠመድ፣ ከአፍህ በወጣውም ቃል ብትያዝ፣ 3 ልጄ ሆይ፤ ራስህን ለማዳን ይህን አድርግ፤ በጎረቤትህ እጅ ስለ ወደቅህ፣ ሄደህ…
ከአመንዝራ ሴት መራቅ 1 ልጄ ሆይ፤ ቃሌን ጠብቅ፤ ትእዛዜንም በውስጥህ አኑር። 2 ትእዛዜን ጠብቅ፤ በሕይወት ትኖራለህ፤ ትምህርቴንም እንደ ዐይንህ ብሌን ተንከባከበው። 3 በጣትህ ላይ እሰረው፤ በልብህ ጽላት ላይ ጻፈው። 4 ጥበብን፣ “እኅቴ ነሽ” በላት፤ ማስተዋልንም፣…
የጥበብ ጥሪ 1 ጥበብ ጮኻ አትጣራምን? ማስተዋልስ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ አታሰማምን? 2 በመንገድ አጠገብ ባሉ ኰረብቶች፣ መንገዶቹ በሚገናኙበትም ላይ ትቆማለች፤ 3 ወደ ከተማዪቱ በሚያስገቡት በሮች አጠገብ፣ በመግቢያዎቹ ላይ፣ ድምጿን ከፍ አድርጋ እንዲህ ስትል ትጮኻለች፤ 4…
ጠቢብነትና ተላላነት 1 ጥበብ ቤቷን ሠራች፤ ሰባቱን ምሰሶዎቿንም ጠርባ አቆመች፤ 2 ፍሪዳዋን አረደች፤ የወይን ጠጇን ጠመቀች፤ ማእዷንም አዘጋጀች። 3 ሴት አገልጋዮቿንም ላከች፤ ከከተማዪቱም ከፍተኛ ቦታ ተጣራች። 4 እርሷም ማመዛዘን ለጐደላቸው፣ “ማስተዋል የሌላችሁ ሁሉ ወደዚህ ኑ”…
1 የሰሎሞን ምሳሌዎች፤ ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ተላላ ልጅ ግን ለእናቱ ሐዘንን ያተርፋል። 2 ያላግባብ የተገኘ ሀብት አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ይታደጋል። 3 እግዚአብሔርጻድቁ እንዲራብ አያደርግም፤ የክፉዎችን ምኞት ግን ያጨናግፋል። 4 ሰነፍ እጆች ሰውን…