ነህምያ 1

የነህምያ ጸሎት 1 የሐካልያ ልጅ የነህምያ ቃል፤ በሃያኛው ዓመት ካሴሉ በተባለው ወር በሱሳ ግንብ ሳለሁ፣ 2 ከወንድሞቼ አንዱ የሆነው አናኒ፣ ከሌሎች ጥቂት ሰዎች ጋር ከይሁዳ መጣ፤ እኔም ከምርኮ ስለተረፉት የአይሁድ ቅሬታዎችና ስለ ኢየሩሳሌም ጠየቅኋቸው። 3…

ነህምያ 2

አርጤክስስ ነህምያን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ ፈቀደለት 1 በንጉሡ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት በሃያኛው ዓመት ኒሳን ተብሎ በሚጠራው ወር የወይን ጠጅ በመጣለት ጊዜ፣ የወይን ጠጁን አንሥቼ ለንጉሡ ሰጠሁት። ቀድሞ በፊቱ ዐዝኜ አላውቅም ነበር፤ 2 ስለዚህ ንጉሡ፣ “ሳትታመም…

ነህምያ 3

የቅጥሩ ሠራተኞች 1 ሊቀ ካህናቱ ኤልያሴብና ወንድሞቹ ካህናት ለሥራ ተነሡ፤ የበጎች በር የተባለውንም እንደ ገና ሠሩ። ቀደሱት፤ መዝጊያዎቹንም በየቦታቸው ላይ አቆሙ። መቶ ማማ እስከሚባለው ግንብና ሐናንኤል ማማ ተብሎ እስከሚጠራው ድረስ ሠርተው ቀደሱት፤ 2 ቀጥሎ ያለውንም…

ነህምያ 4

ቅጥሩ እንዳይሠራ የተደረገ ተቃውሞ 1 ሰንባላጥ ቅጥሩን እንደምንሠራ በሰማ ጊዜ ተቈጣ፤ እጅግም ተበሳጨ። በአይሁድም ላይ ተሣለቀ፤ 2 በተባባሪዎቹና በሰማርያ ሰራዊት ፊት፣ “እነዚህ ደካማ አይሁድ ምን እያደረጉ ነው? ቅጥራቸውን መልሰው ሊሠሩ ነውን? መሥዋዕት ሊያቀርቡ ነውን? በአንዲት…

ነህምያ 5

ነህምያ ድኾችን ረዳ 1 በዚህ ጊዜ ወንዶቹና ሚስቶቻቸው አይሁድ ወንድሞቻቸውን በመቃወም ብርቱ ጩኸት አሰሙ፤ 2 አንዳንዶቹ፣ “እኛም ሆን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን በቍጥር ብዙ ነን፤ ታዲያ ለመብላትም ሆነ በሕይወት ለመቈየት እህል ማግኘት አለብን” አሉ። 3 ሌሎቹ፣…

ነህምያ 6

በቅጥሩ ሥራ ላይ የተነሣ ሌላ ታቃውሞ 1 እስከዚያች ጊዜ ድረስ ለበሮቹ መዝጊያ ባልገጥምላቸውም እንኳ፣ ቅጥሩን መሥራቴንና የቀረ ክፍት ቦታ አለመኖሩን ሰንባላጥ፣ ጦብያ፣ ዓረባዊው ጌሳምና የቀሩትም ጠላቶቻችን በሰሙ ጊዜ፣ 2 ሰንባላጥና ጌሳም፣ “ናና በኦኖ ሜዳ ከሚገኙት…

ነህምያ 7

1 ቅጥሩ እንደ ገና ከተሠራና መዝጊያዎቹንም በየቦታቸው ከገጠምሁ በኋላ፣ በር ጠባቂዎች፣ መዘምራንና ሌዋውያን ተመደቡ። 2 በኢየሩሳሌምም ላይ ወንድሜን አናኒን እንዲሁም ፍጹም ታማኝና ከሌሎች ሰዎች ይልቅ እግዚአብሔርን ይበልጥ የሚፈራውን የግንቡን አዛዥ ሐናንያን ኀላፊ አደረግኋቸው። 3 ለእነርሱም፣…

ነህምያ 8

1 ሕዝቡ ሁሉ “ከውሃ በር” ፊት ለፊት በሚገኘው አደባባይ ላይ እንደ አንድ ሰው ተሰበሰቡ፤ ከዚያም እግዚአብሔር ለእስራኤል ያዘዘውን የሙሴ ሕግ መጽሐፍ እንዲያመጣ ለጸሓፊው ለዕዝራ ነገሩት። 2 ስለዚህ ካህኑ ዕዝራ በሰባተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን ወንዶች፣ ሴቶችና…

ነህምያ 9

እስራኤላውያን ኀጢአታቸውን ተናዘዙ 1 በዚያኑ ወር ሃያ አራተኛ ቀን እስራኤላውያን ጾመው፣ ማቅ ለብሰው፣ በራሳቸው ላይ ትቢያ ነስንሰው በአንድነት ተሰበሰቡ። 2 የእስራኤላውያን ዘር የሆኑትም ራሳቸውን ከባዕዳን ሁሉ ለዩ። ቆመውም ኀጢአታቸውንና የአባቶቻቸውን በደል ተናዘዙ። 3 በያሉበትም ቦታ…

ነህምያ 10

1 ያተሙትም እነዚህ ናቸው፤ የሐካልያ ልጅ አገረ ገዡ ነህምያ፣ ሴዴቅያስ፣ 2 ሠራያ፣ ዓዛርያስ፣ ኤርምያስ፣ 3 ፋስኮር፣ አማርያ፣ መልክያ፣ 4 ሐጡስ፣ ሰበንያ፣ መሉክ፣ 5 ካሪም፣ ሜሪሞት፣ አብድዩ፣ 6 ዳንኤል፣ ጌንቶን፣ ባሮክ፣ 7 ሜሱላም፣ አብያ፣ ሚያሚን፣ 8…