አስቴር 1
ንግሥት አስጢን ከክብሯ ወረደች 1 ከህንድ ጀምሮ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ ያሉትን አንድ መቶ ሃያ ሰባት አገሮች ይገዛ በነበረው በጠረክሲስ ዘመነ መንግሥት እንዲህ ሆነ፤ 2 በዚያን ዘመን ንጉሡ ጠረክሲስ የገዛው በሱሳ ግንብ ባለው ንጉሣዊ ዙፋኑ ሆኖ…
ንግሥት አስጢን ከክብሯ ወረደች 1 ከህንድ ጀምሮ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ ያሉትን አንድ መቶ ሃያ ሰባት አገሮች ይገዛ በነበረው በጠረክሲስ ዘመነ መንግሥት እንዲህ ሆነ፤ 2 በዚያን ዘመን ንጉሡ ጠረክሲስ የገዛው በሱሳ ግንብ ባለው ንጉሣዊ ዙፋኑ ሆኖ…
አስቴር ንግሥት ሆነች 1 ከዚህ በኋላ ንጉሡ ጠረክሲስ ቊጣው ሲበርድለት አስጢንን፣ ያደረገችውን ነገርና በእርሷም ላይ ያስተላለፈውን ዐዋጅ ዐሰበ። 2 ከዚያም የንጉሡ የቅርብ አገልጋዮች እንዲህ የሚል ሐሳብ አቀረቡ፤ “ለንጉሡ ቈንጆ ልጃገረዶች ይፈለጉለት፤ 3 እነዚህን ሁሉ ቈንጆ…
ሐማ አይሁድን ለማጥፋት የሸረበው ሤራ 1 ከዚህም ነገር በኋላ ንጉሥ ጠረክሲስ የአጋጋዊውን የሐመዳቱን ልጅ ሐማን ከፍ ከፍ አደረገው፤ ከሌሎቹም መኳንንት ሁሉ ከፍተኛውን ሥልጣን በመስጠት አከበረው። 2 ንጉሡ ስለ እርሱ ይህ እንዲደረግለት አዞ ስለ ነበር፣ በንጉሡ…
መርዶክዮስ የአስቴርን ርዳታ ጠየቀ 1 መርዶክዮስ የተደረገውን ሁሉ ባወቀ ጊዜ፣ ልብሱን ቀደደ፤ ከዚያም ማቅ ለብሶ፣ በራሱ ላይ ዐመድ ነስንሶ ድምፁን ከፍ በማድረግ አምርሮ እየጮኸ ወደ ከተማዪቱ መካከል ወጣ። 2 ማቅ የለበሰ እንዲገባ ስለማይፈቀድለት፣ የሄደው እስከ…
አስቴር ለንጉሡ ያቀረበችው ልመና 1 በሦስተኛው ቀን አስቴር የክብር ልብሷን ለብሳ በንጉሡ አዳራሽ ፊት ለፊት ባለው በቤተ መንግሥቱ ውስጠኛ አደባባይ ገብታ ቆመች። ንጉሡም አዳራሹ ውስጥ በመግቢያው ትይዩ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ነበር። 2 ንግሥት አስቴር በአደባባዩ…
መርዶክዮስ ከፍ ከፍ አለ 1 በዚያች ሌሊት ንጉሡ እንቅልፍ መተኛት አልቻለም። ስለዚህ በዘመነ መንግሥቱ የተመዘገበው የታሪክ መጽሐፍ ቀርቦ እንዲነበብለት አዘዘ። 2 በዚያም በሩን ከሚጠብቁት ከንጉሡ የጦር አዛዦች ሁለቱ፣ ገበታና ታራ ንጉሥ ጠረክሲስን ለመግደል አሢረው እንደ…
ሐማ ተሰቀለ 1 ስለዚህ ንጉሡና ሐማ ከንግሥት አስቴር ጋር ለመጋበዝ ሄዱ፤ 2 በሁለተኛውም ቀን የወይን ጠጅ እየጠጡ ሳለ፣ ንጉሡ እንደ ገና፣ “ንግሥት አስቴር ሆይ፤ የምትለምኚው ምንድን ነው? ይሰጥሻል፤ የምትጠይቂውስ ምንድን ነው? እስከ መንግሥቴ እኩሌታ እንኳ…
ንጉሡ በአይሁድ ስም የተናገረው ዐዋጅ 1 በዚያኑ ዕለት ንጉሥ ጠረክሲስ የአይሁድን ጠላት የሐማን ቤት ንብረት ለንግሥት አስቴር ሰጣት፤ አስቴርም መርዶክዮስ እንዴት እንደሚዛመዳት ለንጉሡ ነግራው ስለ ነበር፣ መርዶክዮስ ወደ ንጉሡ ዘንድ ቀረበ። 2 ንጉሡ ከሐማ መልሶ…
የአይሁድ ድል ማድረግ 1 አዳር በተባለው በዐሥራ ሁለተኛው ወር ዐሥራ ሦስተኛ ቀን፣ በንጉሡ ትእዛዝ የወጣው ዐዋጅ የሚፈጸምበት ዕለት ነበር። በዚህም ዕለት የአይሁድ ጠላቶች የበላይነቱን እንደሚያገኙ ተማምነው ነበር፤ ሁኔታው ግን ተለወጠና አይሁድ በሚጠሏቸው ላይ የበላይነትን አገኙ።…
የመርዶክዮስ ታላቅነት 1 ንጉሥ ጠረክሲስ እስከ ባሕር ዳርቻ በሚዘልቀው ግዛቱ ሁሉ ላይ ግብር ጣለ። 2 የኀይሉና የብርታቱ ሥራ ሁሉ እንዲሁም ንጉሡ መርዶክዮስን ለዚህ የላቀ ማዕረግ እንዴት እንዳደረሰው የሚናገረው በሜዶንና በፋርስ የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? 3…