ኢሳይያስ 31
በግብጽ ለሚደገፉ ወዮውላቸው 1 ወደ እስራኤል ቅዱስ ለማይመለከቱ፣ ከእግዚአብሔርምርዳታን ለማይሹ፣ ነገር ግን፤ ለርዳታ ብለው ወደ ግብፅ ለሚወርዱ፣ በፈረሶች ለሚታመኑ፣ በሠረገሎቻቸው ብዛት፣ በፈረሶቻቸውም ታላቅ ብርታት ለሚመኩ ወዮላቸው! 2 እርሱም ግን ጠቢብ ነው፤ ጥፋትን ያመጣል፤ ቃሉን አያጥፍም።…
በግብጽ ለሚደገፉ ወዮውላቸው 1 ወደ እስራኤል ቅዱስ ለማይመለከቱ፣ ከእግዚአብሔርምርዳታን ለማይሹ፣ ነገር ግን፤ ለርዳታ ብለው ወደ ግብፅ ለሚወርዱ፣ በፈረሶች ለሚታመኑ፣ በሠረገሎቻቸው ብዛት፣ በፈረሶቻቸውም ታላቅ ብርታት ለሚመኩ ወዮላቸው! 2 እርሱም ግን ጠቢብ ነው፤ ጥፋትን ያመጣል፤ ቃሉን አያጥፍም።…
የጽድቅ መንግሥት 1 እነሆ፤ ንጉሥ በጽድቅ ይነግሣል፤ ገዦችም በፍትሕ ይገዛሉ። 2 እያንዳንዱ ሰው ከነፋስ መከለያ፣ ከወጀብም መጠጊያ ይሆናል። በበረሓም እንደ ውሃ ምንጭ፣ በተጠማም ምድር እንደ ትልቅ ቋጥኝ ጥላ ይሆናል። 3 የሚያዩ ሰዎች ዐይን ከእንግዲህ አይጨፈንም፤…
የጭንቅ ጊዜና ርዳታ 1 አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፣ አንት አጥፊ፣ ወዮልህ! አንተ ሳትካድ የምትክድ፣ አንት ከዳተኛ፣ ወዮልህ! ማጥፋትን በተውህ ጊዜ፣ ትጠፋለህ፤ ክሕደትህንም በተውህ ጊዜ ትከዳለህ። 2 እግዚአብሔርሆይ፤ ማረን፤ አንተን ተስፋ አድርገናል። በየማለዳው ብርታት፣ በጭንቅ ጊዜም ድነት…
ፍርድ በአሕዛብ ላይ 1 እናንት አሕዛብ ሆይ፤ ኑ አድምጡም፤ እናንተ ሰዎች ሆይ፤ አስተውሉ። ምድርና በውስጧ ያለ ሁሉ፣ ዓለምና ከእርሷ የሚበቅል ሁሉ ይስማ። 2 እግዚአብሔርአሕዛብን ሁሉ ተቈጥቶአል፤ ቍጣውም በሰራዊታቸው ሁሉ ላይ ነው፤ ፈጽሞ ያጠፋቸዋል፤ ለዕርድም አሳልፎ…
የተቤዠ ሕዝብ ደስታ 1 ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፤ በረሓው ሐሤት ያደርጋል፤ ይፈካል፤ እንደ አደይም ያብባል። 2 በደስታና በዝማሬ ሐሤት ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብር ይሰጠዋል፤ የቀርሜሎስንና የሳሮንን ግርማ ይለብሳል። የአምላካችንን ታላቅ ግርማ፣ የእግዚአብሔርንክብር ያያሉ። 3…
የሰናክሬም ዛቻ በኢየሩሳሌም ላይ 1 ንጉሥ ሕዝቅያስ በነገሠ በዐሥራ አራተኛው ዓመት፣ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም የተመሸጉትን የይሁዳ ከተሞች ሁሉ አጥቅቶ ያዛቸው። 2 የአሦርም ንጉሥ የጦር አዛዡን ከብዙ ሰራዊት ጋር ከለኪሶ፣ ንጉሡ ሕዝቅያስ ወዳለበት፣ ወደ ኢየሩሳሌም ላከው።…
የኢየሩሳሌም ዐርነት ታወጀ 1 ንጉሡ ሕዝቅያስ ይህን ሲሰማ፣ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅ ለበሰ፤ ወደእግዚአብሔርቤተ መቅደስ ገባ። 2 የቤተ መንግሥቱን አስተዳዳሪ ኤልያቄምንና ጸሓፊውን ሳምናስን እንዲሁም ከካህናቱ ዋና ዋናዎቹን ማቅ ለብሰው ሁሉም ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ…
የሕዝቅያስ መታመም 1 በዚያ ጊዜ ሕዝቅያስ ታመመ፤ ሞት አፋፍ ደረሰ፤ የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስም ወደ እርሱ መጥቶ፣“እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ ‘ከሕመምህ አትድንም፤ ትሞታለህና ቤትህን አሰናዳ’ ” አለው። 2 ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳ አዙሮ፣ እንዲህ ሲል ወደእግዚአብሔርጸለየ፤ 3 “እግዚአብሔርሆይ፤…
ከባቢሎን የመጡ መልእክተኞች 1 በዚያን ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ፣ የባልዳን ልጅ፣ መሮዳክ ባልዳን የሕዝቅያስን መታመምና መፈወስ ሰምቶ ስለ ነበር፣ ደብዳቤና ስጦታ ላከለት። 2 ሕዝቅያስም መልእክተኞቹን በደስታ ተቀበለ፤ ለእነርሱም በግምጃ ቤቱ ውስጥ ያለውን ብሩን፣ ወርቁን፣ ቅመማ ቅመሙን፣…
የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚያጽናና ቃል 1 አጽናኑ፤ ሕዝቤን አጽናኑ፤ ይላል አምላካችሁ። 2 ለኢየሩሳሌም አለዝባችሁ ንገሯት፤ ዐውጁላትም፤ በባርነት ያገለገለችበት ዘመን አብቅቶአል፤ የኀጢአቷም ዋጋ ተከፍሎአል፤ ስለ ኀጢአቷ ሁሉከእግዚአብሔርእጅ ሁለት ዕጥፍ ተቀብላለች። 3 የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እንዲህ ይላል፤ “የእግዚአብሔርንመንገድ፣…