ኢሳይያስ 51

የዘላለም ድነት ለጽዮን 1 “እናንት ጽድቅን የምትከታተሉ፣ እግዚአብሔርንየምትፈልጉ ስሙኝ፤ ተቈርጣችሁ የወጣችሁበትን ዐለት፣ ተቈፍራችሁ የወጣችሁባትንም ጒድጓድ ተመልከቱ። 2 ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፣ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሣራ ተመልከቱ፤ በጠራሁት ጊዜ አንድ ራሱን ብቻ ነበር፤ ባረክሁት፤ አበዛሁትም። 3…

ኢሳይያስ 52

1 ጽዮን ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ኀይልን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ! የክብር ልብስሽን ልበሺ፤ ያልተገረዘ የረከሰም ከእንግዲህ ወደ አንቺ አይገባም። 2 ትቢያሽን አራግፊ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ በዙፋንሽ ላይ ተቀመጪ፤ ምርኮኛዪቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ የዐንገትሽን የእስራት…

ኢሳይያስ 53

1 የሰማነውን ነገር ማን አመነ? የእግዚአብሔርስክንድ ለማን ተገለጠ? 2 በፊቱ እንደ ቡቃያ፣ ከደረቅም መሬት እንደ ወጣ ሥር በቀለ፤ የሚስብ ውበት ወይም ግርማ የለውም፤ እንድንወደውም የሚያደርግ መልክ አልነበረውም። 3 በሰዎች የተናቀና የተጠላ፣ የሕማም ሰውና ሥቃይ ያልተለየው…

ኢሳይያስ 54

የወደፊቱ የጽዮን ክብር 1 “አንቺ መካን ሴት፤ አንቺ ልጅ ወልደሽ የማታውቂ፤ ዘምሪ፤ እልል በዪ፤ በደስታ ጩኺ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፣ ባል ካላት ሴት ይልቅ፣ የፈቷ ልጆች ይበዛሉና” ይላልእግዚአብሔር። 2 “የድንኳንሽን ቦታ አስፊ፤ የድንኳንሽን መጋረጃዎች በትልቁ ዘርጊ፤…

ኢሳይያስ 55

ጥሪ ለተጠሙ 1 እናንት የተጠማችሁ ሁሉ ኑ፤ እናንት ገንዘብ የሌላችሁ፣ ወደ ውሆች ኑ፤ ኑና ግዙ፤ ብሉም፤ ኑና ያለ ገንዘብ፣ ያለ ዋጋ፣ የወይን ጠጅና ወተት ግዙ። 2 ገንዘባችሁን እንጀራ ባልሆነ ነገር ላይ ለምን ታጠፋላችሁ? በማያጠግብስ ነገር…

ኢሳይያስ 56

ለሌሎች የተሰጠ ድነት 1 እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ “ፍትሕን ጠብቁ፤ መልካሙን አድርጉ፤ ማዳኔ በቅርብ ነው፤ ጽድቄም ፈጥኖ ይገለጣልና። 2 ሰንበትን ሳያረክስ የሚያከብር፣ ክፉን ከማድረግ እጁን የሚሰበስብ፣ የሚገታ፣ እነዚህን የሚፈጽም ሰው የተባረከ ነው።” 3 ወደእግዚአብሔርየተጠጋ መጻተኛ፣ “እግዚአብሔር በርግጥ…

ኢሳይያስ 57

1 ጻድቅ ይሞታል፤ ይህን ግን ማንም ልብ አይልም፤ ለእግዚአብሔርያደሩ ሰዎች ይወሰዳሉ፤ ጻድቃን ከክፉ ይድኑ ዘንድ፣ መወሰዳቸውን፣ ማንም አያስተውልም። 2 በቅንነት የሚሄዱ፣ ሰላም ይሆንላቸዋል፤ መኝታቸው ላይ ያርፋሉ። 3 “እናንት የአስማተኛዪቱ ልጆች ግን፣ እናንት የአመንዝራውና የጋለሞታዪቱ ዘር፤…

ኢሳይያስ 58

እውነተኛ ጾም 1 “በኀይል ጩኽ፤ ምንም አታስቀር፤ ድምፅህን እንደ መለከት አሰማ፤ ለሕዝቤ ዐመፃቸውን፣ ለያዕቆብም ቤት ኀጢአታቸውን ተናገር። 2 ዕለት በዕለት ይፈልጉኛል፤ መንገዴን ለማወቅ የሚጓጉ ይመስላሉ፤ ትክክለኛውን ነገር እንደሚያደርግ፣ የአምላኩንም ትእዛዝ እንዳልተወ ሕዝብ ሁሉ፣ ተገቢ የሆነ…

ኢሳይያስ 59

ኀጢአት፣ ንስሓና መበዤት 1 እነሆ፤የእግዚአብሔርእጅ ከማዳን አላጠረችም፤ ጆሮውም መስማት አልተሳናትም 2 ነገር ግን በደላችሁ ከአምላካችሁ ለይቶአችኋል፤ ኀጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል፤ በዚህም ምክንያት አይሰማም። 3 እጆቻችሁ በደም፣ ጣቶቻችሁ በበደል ተነክረዋል፤ ከንፈሮቻችሁ ሐሰትን ተናገሩ፤ ምላሶቻችሁ ክፉ ነገርን…

ኢሳይያስ 60

የጽዮን ክብር 1 “ብርሃንሽ መጥቶአልና ተነሺ አብሪ፤ የእግዚአብሔርምክብር ወጥቶልሻል። 2 እነሆ፤ ጨለማ ምድርን፣ ድቅድቅ ጨለማም ሕዝቦችን ይሸፍናል፤ ነገር ግንእግዚአብሔርወጥቶልሻል፤ ክብሩንም ይገልጥልሻል። 3 ሕዝቦች ወደ ብርሃንሽ፣ ነገሥታትም ወደ ንጋትሽ ጸዳል ይመጣሉ። 4 “ቀና በዪ፤ ዙሪያሽን ተመልከቺ፤…