ኢሳይያስ 61
የተወደደው የእግዚአብሔር ዓመት 1 የጌታየእግዚአብሔርመንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድኾች የምሥራች እንድሰብክ፣ እግዚአብሔርቀብቶኛል። ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣ ለምርኮኞች ነጻነትን፣ ለእስረኞች መፈታትን እንዳውጅልኮኛል፤ 2 የተወደደውንየእግዚአብሔርንዓመት፣ የአምላካችንንም የበቀል ቀን እንዳውጅ፣ የሚያለቅሱትን ሁሉ እንዳጽናና ልኮኛል፤ 3 በጽዮን ያዘኑትን እንዳረጋጋ፣ በዐመድ…