ኢዮብ 31

1 “ወደ ኰረዳዪቱ ላለመመልከት፣ ከዐይኔ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ። 2 ከላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሰው ዕድል ፈንታው፣ ከአርያም ሁሉን ከሚችል አምላክስ ዘንድ ቅርሱ ምንድ ነው? 3 ለኀጢአተኞች ጥፋት፣ ክፉ ለሚያደርጉም መቅሠፍት አይደለምን? 4 እርሱ መንገዴን አያይምን?…

ኢዮብ 32

ኤሊሁ 1 ኢዮብ በበኩሉ ራሱን እንደ ጻድቅ ቈጥሮ ስለ ነበር፣ እነዚህ ሦስት ሰዎች ለእርሱ መልስ መስጠታቸውን ተዉ። 2 ከራም ወገን የሆነው፣ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ግን ኢዮብ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን ጻድቅ ስላደረገ፣ እጅግ ተቈጣው። 3…

ኢዮብ 33

1 “አሁን ግን ኢዮብ ሆይ፣ ንግግሬን ስማ፤ የምለውንም ሁሉ አድምጥ። 2 እንግዲህ አፌን እከፍታለሁ፤ አንደበቴም ይናገራል። 3 ቃሌ ከቅን ልብ ይወጣል፤ ከንፈሬም የማውቀውን በትክክል ይናገራል። 4 የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጥሮኛል፤ ሁሉን የሚችለውም አምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጥቶኛል።…

ኢዮብ 34

1 ኤሊሁ በመቀጠል እንዲህ አለ፤ 2 “እናንት ጠቢባን፣ ቃሌን ስሙ፤ ዐዋቂዎችም አድምጡኝ። 3 ምላስ ምግብን አጣጥሞ እንደሚለይ፣ ጆሮም የንግግርን ለዛ ለይቶ ያውቃል። 4 የሚበጀንን እንምረጥ፣ መልካሙንም አብረን እንወቅ። 5 “ኢዮብ እንዲህ ይላል፤ ‘እኔ ንጹሕ ነኝ፤…

ኢዮብ 35

1 ኤሊሁ ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ 2 “ ‘በእግዚአብሔር ፊት ንጹሕ ነኝ’ማለትህ፣ ትክክል ይመስልሃልን? 3 ደግሞ ‘ያገኘሁትጥቅም ምንድን ነው? ኀጢአት ባለ መሥራቴስ ምን አተረፍሁ?’ ብለህ ጠይቀኸዋል። 4 “ለአንተና አብረውህ ላሉት ባልንጀሮችህ፣ መልስ መስጠት እፈልጋለሁ። 5 ቀና…

ኢዮብ 36

1 ኤሊሁ በመቀጠል እንዲህ አለ፤ 2 “በእግዚአብሔር ፈንታ ሆኜ የምለው አለኝ፤ ጥቂት ታገሠኝና እነግርሃለሁ። 3 ዕውቀቴን ከሩቅ አመጣለሁ፤ ፈጣሪዬ ጻድቅ እንደሆነ እገልጻለሁ። 4 ቃሌ ሐሰት እንዳልሆነ አረጋግጣለሁ፤ በዕውቀቱ ፍጹም የሆነ ሰው ከአንተ ጋር ነው። 5…

ኢዮብ 37

1 ልቤ በዚህ በኀይል ይመታል፤ ከስፍራውም ዘለል ዘለል ይላል። 2 ስሙ! የድምፁን ጩኸት ስሙ፤ ከአፉ የሚወጣውን ጒርምርምታ አድምጡ። 3 መብረቁን ከሰማይ ሁሉ በታች ያባርቃል፤ ወደ ምድርም ዳርቻ ይልካል። 4 ከዚያም በኋላ የድምፁ ጩኸት ይመጣል፤ በድምፁም…

ኢዮብ 38

እግዚአብሔር ተናገረ 1 እግዚአብሔርምበዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ለኢዮብ መለሰለት፤ እንዲህም አለው፤ 2 “ዕውቀት በጐደለው ቃል፣ ዕቅዴን የሚያጨልም ይህ ማን ነው? 3 እስቲ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤ እኔ ልጠይቅህ፣ አንተም መልስልኝ። 4 “ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ…

ኢዮብ 39

1 “የበረሃ ፍየል የምትወልድበትን ጊዜ ታውቃለህን? ዋልያ ስታምጥስ ተከታትለህ አይተሃል? 2 የእርግዝናቸው ወራት ምን ያህል እንደሆነ ትቈጥራለህን? የሚወልዱበትንስ ጊዜ ታውቃለህን? 3 ተንበርክከው ይወልዳሉ፤ ከምጣቸውም ጣር ይገላገላሉ። 4 ግልገሎቻቸውም ይጠነክራሉ፤ በሜዳም ያድጋሉ፤ ተለይተው ይሄዳሉ፤ ወደ እነርሱም…

ኢዮብ 40

1 እግዚአብሔርምኢዮብን እንዲህ አለው፤ 2 “ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር ተከራክሮ የሚረታው አለን? እግዚአብሔርን የሚወቅስ እርሱ መልስ ይስጥ!” 3 ኢዮብም ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰ፤ 4 “እኔ ከንቱ ሰው፣ ምን እመልስልሃለሁ? እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ። 5 አንድ…