ኤርምያስ 1

1 የኬልቅያስ ልጅ፣ ኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ አባቱ በብንያም አገር በዓናቶት ከሚገኙት ካህናት አንዱ ነበረ። 2 የእግዚአብሔርቃል የይሁዳ ንጉሥ፣ የአሞን ልጅ ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ሦስተኛው ዓመት ወደ ኤርምያስ መጣ፤ 3 ደግሞም በይሁዳ ንጉሥ፣ በኢዮስያስ…

ኤርምያስ 2

የእስራኤል ሕዝብ አምላኩን መተው 1 የእግዚአብሔርቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 2 “ሂድና ጮኸህ ይህን ለኢየሩሳሌም ጆሮ አሰማ፤ “እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ ‘በወጣትነትሽ ጊዜ የነበረሽን ታማኝነት፣ በሙሽርነትሽም ወራት እንዴት እንደ ወደድሽኝ፣ በምድረ በዳ ዘር በማይዘራበት ምድር፣ እንዴት…

ኤርምያስ 3

1 “ሰው ሚስቱን ቢፈታ፣ እርሷም ሄዳ ሌላ ሰው ብታገባ፣ ወደ እርሷ ይመለሳልን? ምድሪቱስ ፈጽማ አትረክስምን? አንቺ ግን ከብዙ ወዳጆችሽ ጋር አመንዝረሻል፤ ታዲያ አሁን ወደ እኔ መመለስ ትፈልጊያለሽን?” ይላልእግዚአብሔር። 2 “እስቲ ቀና ብለሽ ጭር ያሉትን ኰረብቶች…

ኤርምያስ 4

1 “እስራኤል ሆይ፤ ብትመለስ፣ ወደ እኔ ብትመለስ፤” ይላልእግዚአብሔር፤ “አስጸያፊ ነገሮችህን ከፊቴ ብታስወግድ፣ ባትናወጥ ብትቆምም፣ 2 በእውነት፣ በቅንነትና በጽድቅ፣ ‘ሕያውእግዚአብሔርን!’ ብለህ ብትምል፣ አሕዛብ በእርሱ ይባረካሉ፤ በእርሱም ይከበራሉ።” 3 እግዚአብሔርለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሰዎች እንዲህ ያላል፤ “ዕዳሪውን መሬት ዕረሱ፤…

ኤርምያስ 5

ቅን ሰው አለመገኘቱ 1 “በኢየሩሳሌም መንገዶች እስቲ ውጡ፤ ወደ ላይ ወደታችም ውረዱ፤ ዙሪያውን ተመልከቱ ቃኙ፤ በአደባባይዋም ፈልጉ፤ እውነትን የሚሻና በቅንነት የሚሄድ፣ አንድ ሰው እንኳ ብታገኙ፣ እኔ ይህቺን ከተማ እምራታለሁ። 2 ‘ሕያውእግዚአብሔርን! ቢሉም፣ የሚምሉት በሐሰት ነው።”…

ኤርምያስ 6

የኢየሩሳሌም መከበብ 1 “እናንት የብንያም ልጆች፤ ክፉ ነገር፣ ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ድንገት ይመጣልና፣ ከኢየሩሳሌም ሸሽታችሁ አምልጡ፤ በቴቁሔ መለከትን ንፉ፤ በቤትሐካሪም ላይ ምልክት ከፍ አድርጋችሁ አሳዩ። 2 ውብና ሽሙንሙን የሆነችዋን፣ የጽዮንን ሴት ልጅ አጠፋታለሁ። 3 እረኞች…

ኤርምያስ 7

ዋጋ ቢስ አምልኮ 1 ከእግዚአብሔርወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፤ 2 “በእግዚአብሔርቤት በር ቁም፤ በዚያም ይህን መልእክት ዐውጅ፤ “ ‘እግዚአብሔርንለማምለክ፣ በእነዚህ በሮች የምትገቡ የይሁዳ ሕዝብ ሁላችሁ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። 3 የእስራኤል አምላክ፣ የሰራዊት ጌታእግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ “መንገዳችሁንና…

ኤርምያስ 8

1 “ ‘በዚያን ጊዜ፣ ይላልእግዚአብሔር፤ የይሁዳን ነገሥታትና መኳንንት ዐፅም፣ የካህናትና የነቢያት ዐፅም፣ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ዐፅም ከየመቃብራቸው ይወጣል። 2 በወደዷቸውና በአገለገሏቸው እንዲሁም በተከተሏቸው፣ ባማከሯቸውና ባመለኳቸው በፀሓይ፣ በጨረቃና በሰማያት ከዋክብት ሁሉ ፊት ይሰጣል፤ አይሰበሰብም ወይም አይቀበርም፤ ነገር ግን…

ኤርምያስ 9

1 ስለ ታረዱት ወገኖቼ፣ ቀንና ሌሊት አለቅስ ዘንድ፣ ምነው፣ ራሴ የውሃ ምንጭ በሆነ! ምነው ዐይኖቼ የእንባ መጒረፊያ በሆኑልኝ! 2 ሕዝቤን ትቼ፣ ርቄ እንድሄድ፣ በምድረ በዳ የእንግዶች ማደሪያ ማን በሰጠኝ! ሁሉም አመንዝሮች፣ የአታላዮች መንጋ ሆነዋላ! 3…

ኤርምያስ 10

ባዕድ አምልኮና እውነተኛው አምልኮ 1 የእስራኤል ቤት ሆይ፤እግዚአብሔርየሚላችሁን ስሙ። 2 እግዚአብሔርእንዲህ ይላል፤ “የአሕዛብን መንገድ አትከተሉ፤ እነርሱ በሰማይ ምልክቶች ይታወካሉ፣ እናንተ ግን በእነዚህ አትረበሹ። 3 የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከጫካ ይቈርጣሉ፤ አናጺም በመሣሪያው ቅርጽ ያበጅለታል፤…